በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ለምጽ ያለበት ሰው ተፈወሰ!

ለምጽ ያለበት ሰው ተፈወሰ!

ለታዳጊ ወጣቶች

ለምጽ ያለበት ሰው ተፈወሰ!

መመሪያ፦ ይህን መልመጃ ጸጥታ በሰፈነበት ቦታ ሆነህ ሥራ። ጥቅሶቹን ስታነብ በቦታው እንዳለህ አድርገህ አስብ። ሁኔታውን በዓይነ ሕሊናህ ለመሳል እንዲሁም በታሪኩ ውስጥ የተጠቀሱት ሰዎች ሲነጋገሩ ድምፃቸውን ለመስማትና ስሜታቸውን ለመረዳት ሞክር። ታሪኩ ሕያው እንዲሆንልህ አድርግ።

ዋነኞቹ ባለ ታሪኮች፦ ንዕማን፣ ኤልሳዕና ስሟ ያልተጠቀሰ እስራኤላዊት ልጃገረድ

ታሪኩ በአጭሩ፦ ንዕማን የሚባለው የሶርያ ሠራዊት አዛዥ አንዲት እስራኤላዊት ልጃገረድ ኤልሳዕ ጋ እንዲሄድ ከመከረችው በኋላ ከነበረበት አሰቃቂ በሽታ ተፈወሰ።

1 ሁኔታውን ለማስተዋል ሞክር።—2 ነገሥት 5:1-19ን አንብብ።

ይህች እስራኤላዊት ልጃገረድ አምላክን ከሚፈሩ ቤተሰቦቿ ተነጥላ የተወሰደች እንደመሆኗ መጠን ምን ተሰምቷት ሊሆን ይችላል?

․․․․․

ኃያል ሰው የነበረውና አቅም የሚያሳጣ በሽታ የያዘው ንዕማን ምን የተሰማው ይመስልሃል?

․․․․․

ከቁጥር 11 እስከ 13 ላይ በተገለጸው መሠረት ንዕማንና አገልጋዮቹ ሲነጋገሩ የነበራቸው ስሜት ምን ይመስላል?

․․․․․

ከቁጥር 15 ጀምሮ ንዕማን ምን የአመለካከት ለውጥ አድርጓል?

․․․․․

2 ጥልቅ ምርምር አድርግ።

ንዕማን ኩራት እንዲሰማው አስተዋጽኦ ያደረጉት ምን ነገሮች ሊሆኑ ይችላሉ? (ቁጥር 1⁠ን በድጋሚ አንብብ።)

․․․․․

ምርምር ማድረግ የምትችልባቸውን መሣሪያዎች በመጠቀም በጥንት ዘመን ስለነበረው የለምጽ ወይም የሥጋ ደዌ በሽታ ለማወቅ ምርምር አድርግ። * (ለምሳሌ፣ በሽታው ምን ያህል ከባድ ነበር? ተላላፊ ነበር? በዚህ በሽታ የተያዘ ሰው ምን ይደረግ ነበር?)

․․․․․

የንዕማን መፈወስ በትንሿ እስራኤላዊት ልጃገረድ ላይ ምን ውጤት አስከትሎ ሊሆን ይችላል?

․․․․․

ኤልሳዕ የሰጠው መልስ ለንዕማን በምን መንገድ ፈተና ሆኖበት ሊሆን ይችላል? (ቁጥር 10⁠ን ተመልከት።)

․․․․․

3 ከዚህ ታሪክ ያገኘኸውን ትምህርት ተግባራዊ አድርግ። ከዚህ በታች ስለተዘረዘሩት ነገሮች ምን ትምህርት እንዳገኘህ ጻፍ፦

ኩራት ስለሚያስከትላቸው አደጋዎች።

․․․․․

እምነትህን በተመለከተ በድፍረት ስለመናገር።

․․․․․

ይሖዋ ስላለው በሽታን የመፈወስ ችሎታ።

․․․․․

4 ከዚህ ታሪክ ውስጥ ይበልጥ ትምህርት ያገኘህበት ሐሳብ የትኛው ነው? ለምን እንዲህ አልክ?

․․․․․

በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረቱ ሌሎች ጽሑፎች ለማግኘት የይሖዋ ምሥክሮችን ጠይቅ ወይም www.watchtower.org ተመልከት።

[የግርጌ ማስታወሻ]

^ አን.18 በጥንት ዘመን ለምጽ ወይም ሥጋ ደዌ ይባል የነበረው የቆዳ በሽታ በዛሬ ጊዜ ሃንሰንስ ዲዚዝ ተብሎ የሚጠራውን በሽታም ያጠቃልላል።