በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የአልዓዛር ትንሣኤ

የአልዓዛር ትንሣኤ

ለወጣት አንባቢያን

የአልዓዛር ትንሣኤ

መመሪያ፦ ይህን መልመጃ ጸጥታ በሰፈነበት ቦታ ሆነህ ሥራ። ጥቅሶቹን ስታነብ በቦታው እንዳለህ አድርገህ አስብ። ሁኔታውን በዓይነ ሕሊናህ ለመሳል እንዲሁም በታሪኩ ውስጥ የተጠቀሱት ሰዎች ሲነጋገሩ ድምፃቸውን ለመስማትና ስሜታቸውን ለመረዳት ሞክር።

ሁኔታውን ለማስተዋል ሞክር።ዮሐንስ 11:1-45ን አንብብ።

ቁጥር 21⁠ንና 32⁠ን በምታነብበት ጊዜ በማርታና በማርያም ላይ ይነበብ ስለነበረው ስሜት ምን አስተዋልክ?

․․․․․

በቁጥር 3335 ላይ ኢየሱስ ስሜቱን የገለጸበትን ሁኔታ በዓይነ ሕሊናህ መሳል ትችላለህ?

․․․․․

በቁጥር 4344 ላይ ተመዝግቦ የሚገኘው ታሪክ በተፈጸመበት ወቅት ብትኖር ኖሮ ሁኔታዎቹ ምን ስሜት ሊያሳድሩብህ እንደሚችሉ ለማሰብ ሞክር። አልዓዛርን ብትሆን ኖሮ ምን ይሰማህ ነበር? በቦታው ከነበሩት ሰዎች መካከል አንዱ ብትሆን ኖሮስ?

ጥልቅ ምርምር አድርግ።

ኢየሱስ ከነበረበት ቦታ ተነስቶ ቢታንያ ለመድረስ የሚወስድበት ጊዜ ሁለት ቀን ነበር። ታዲያ ኢየሱስ መዘግየት የፈለገው ለምንድን ነው? (ቁጥር 6⁠ን በድጋሚ አንብብ።)

․․․․․

መጽሐፍ ቅዱስ ማርያምና ማርታ ለመንፈሳዊ ነገሮች ፍላጎት እንደነበራቸው የሚጠቁመው እንዴት ነው? (ሉቃስ 10:38, 39፤ ዮሐንስ 11:24)

․․․․․

ኢየሱስ እንደገና መሞታቸው ባይቀርም ሰዎችን ከሞት ያስነሳው ለምን ነበር? (ማርቆስ 1:41, 42፤ ዮሐንስ 5:28, 29፤ 11:45)

․․․․․

ከዚህ ታሪክ ያገኘኸውን ትምህርት ተግባራዊ አድርግ። ከዚህ በታች ስለተዘረዘሩት ነገሮች ምን ትምህርት እንዳገኘህ ጻፍ፦

ኢየሱስ ሙታንን ለማስነሳት ስላለው ችሎታና ስላሳየው የፈቃደኝነት መንፈስ።

․․․․․

ኢየሱስ ላዘኑ ሰዎች ስላለው ጥልቅ የሆነ የርኅራኄ ስሜት።

․․․․․

በትንሣኤ ማንን ማግኘት ትፈልጋለህ?

․․․․․

ከዚህ ታሪክ ውስጥ ልብህን ይበልጥ የነካው ምንድን ነው? ለምንስ?

․․․․․