በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ምን ይመስልሃል?

ምን ይመስልሃል?

መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክ ወዳጅ እንድትሆን ሊረዳህ ይችላል?

አንዳንዶች ምን ብለው ያምናሉ?

አንዳንድ ሰዎች ኃጢአተኛ እንደሆኑ ስለሚሰማቸው የአምላክ ወዳጅ መሆን እንደማይችሉ ያስባሉ። ሌሎች ደግሞ አምላክ ስለ እኛ ግድ እንደማይሰጠው ይናገራሉ። አንተስ ምን ይመስልሃል?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

አምላክ “ከቅኖች ጋር . . . የጠበቀ ወዳጅነት አለው።” (ምሳሌ 3:32) አምላክን ከታዘዝን ወዳጆቹ መሆን እንችላለን።

መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረው ሌላስ ነገር አለ?

  • አምላክ ወዳጆቹ እንድንሆን ይፈልጋል።—ያዕቆብ 4:8

  • አምላክ ወዳጆቹን ለመርዳትና ኃጢአታቸውን ይቅር ለማለት ዝግጁ ነው።—መዝሙር 86:5

  • የአምላክ ወዳጆች እሱ የሚወደውን ይወዳሉ፤ እንዲሁም የሚጠላውን ይጠላሉ።—ሮም 12:9