በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መጠበቂያ ግንብ ቁጥር 1 2018 | መጽሐፍ ቅዱስ በዚህ ዘመንም ጠቃሚ ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ በዚህ ዘመን ጠቃሚ ነው?

የምንኖረው መረጃ እንደ ልብ በሚገኝበት የሥልጣኔ ዘመን ነው፤ ከዚህ አንጻር የመጽሐፍ ቅዱስ ምክር ጊዜ ያለፈበት ይመስልሃል? መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦

‘ቅዱሳን መጻሕፍት ሁሉ በአምላክ መንፈስ መሪነት የተጻፉና ጠቃሚ ናቸው።’—2 ጢሞቴዎስ 3:16

ይህ የመጠበቂያ ግንብ እትም የመጽሐፍ ቅዱስ ምክሮች በዕለት ተዕለት ሕይወታችን የሚጠቅሙን እንዴት እንደሆነ ያብራራል።

 

የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ በዘመናችን ጠቃሚ ነው?

ዘመናዊ በሆነውና በቴክኖሎጂ በመጠቀው በዚህ ዓለም ውስጥ እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ባለ ከተጻፈ ወደ 2,000 ዓመት ያስቆጠረ መጽሐፍ የምንጠቀምበት ምን ምክንያት ይኖራል?

ዘመን የማይሽራቸው የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያዎች

አዳዲስ እውቀት መገኘቱ መጽሐፍ ቅዱስን ዘመን ያለፈበት እንዲሆን አላደረገውም፤ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች የተመሠረቱት ጠቃሚና ዘመን በማይሽራቸው መመሪያዎች ላይ ነው።

ዘመን ያለፈበት ወይስ ከዘመኑ የቀደመ?

መጽሐፍ ቅዱስ የሳይንስ ማስተማሪያ መጽሐፍ ባይሆንም ከሳይንስ አንጻር ሊያስገርሙህ የሚችሉ መረጃዎችን ይዟል።

ከችግሮች ለመራቅ የሚረዳ ምክር

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘው ምክር ሰዎች፣ ከባድ ችግሮችን ማስወገድ እንዲችሉ እንዴት እንደረዳቸው ተመልከት።

ችግሮችን ለመፍታት የሚረዳ ምክር

መጽሐፍ ቅዱስ በቀላሉ የማይወገዱ ችግሮችን እንኳ ለመቋቋም የሚረዱ መመሪያዎች ይዟል። ለምሳሌ ያህል ከልክ በላይ ከመጨነቅ፣ ዛሬ ነገ ከማለት ልማድ እንዲሁም ከብቸኝነት ጋር የተያያዙ መመሪያዎች በውስጡ ይገኛሉ።

ችግሮችን ለመቋቋም የሚረዳ ምክር

በአሁኑ ጊዜ ሊወገዱ አሊያም መፍትሔ ሊገኝላቸው የማይችሉ ችግሮች አሉ። ለምሳሌ ያህል፣ የምትወደውን ሰው በሞት አጥተህ ቢሆን ወይም ደግሞ ሥር የሰደደ ሕመም ቢኖርብህ መጽሐፍ ቅዱስ ሊረዳህ ይችላል?

መጽሐፍ ቅዱስና የወደፊት ሕይወትህ

የአምላክ ቃል፣ በምሳሌያዊ አነጋገር በቅርባችን ያሉትን ሁኔታዎች ይኸውም በዕለት ተዕለት ሕይወታችን የሚያጋጥሙንን ችግሮች ለማስተዋልና ለመፍታት ይረዳናል። ከመጽሐፍ ቅዱስ የምናገኘው ጥቅም ግን ይህ ብቻ አይደለም። የወደፊቱ ጊዜ ፍንትው ብሎ እንዲታየን ያደርጋል።

ምን ይመስልሃል?

አንዳንዶች ምን ብለው እንደሚያምኑና መጽሐፍ ቅዱስ ስለዚህ ጉዳይ ምን እንደሚል አንብብ።