በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የአንባቢያን ጥያቄዎች

የአንባቢያን ጥያቄዎች

የአንባቢያን ጥያቄዎች

በሶፎንያስ 2:3 ላይ የሚገኘው “ይሆናል” የሚለው ቃል የአምላክ አገልጋዮች የዘላለም ሕይወት እንደሚያገኙ እርግጠኞች መሆን እንደማይችሉ የሚያሳይ ነው?

ጥቅሱ እንዲህ ይላል:- “እናንት የምድር ትሑታን ሁሉ፣ ትእዛዙን የምትፈጽሙ፣ እግዚአብሔርን እሹ፤ ጽድቅንና ትሕትናን ፈልጉ፤ በእግዚአብሔር የቍጣ ቀን፣ ትሰወሩ ይሆናል።” ይህ ጥቅስ “ይሆናል” የሚለው ለምንድን ነው?

ይሖዋ አርማጌዶን ሲመጣ በሕይወት ለሚገኙ ታማኝ አገልጋዮቹ ምን እንደሚያደርግላቸው ለመገንዘብ፣ አምላክ ከዚህ የፍርድ ቀን በፊት በታማኝነት ለሞቱት ሰዎች የሚያደርግላቸውን ነገር በተመለከተ መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሚል መመልከታችን ጠቃሚ ነው። አንዳንዶቹ መንፈሳዊ ፍጥረታት ሆነው በሰማይ ለመኖር የማይጠፋ ሕይወት ይዘው ይነሳሉ፤ ሌሎቹ ደግሞ በገነት ላይ ለዘላለም ለመኖር በምድር ላይ ይነሳሉ። (ዮሐንስ 5:28, 29፤ 1 ቆሮንቶስ 15:53, 54) ይሖዋ ከአርማጌዶን በፊት የሞቱ ታማኝ አገልጋዮቹን ከማስታወስም አልፎ ወሮታ የሚከፍላቸው ከሆነ የቁጣው ቀን ሲመጣ በሕይወት ለሚገኙት አገልጋዮቹም ተመሳሳይ ነገር እንደሚያደርግ እሙን ነው።

በመንፈስ አነሳሽነት የተነገሩት የሐዋርያው ጴጥሮስ ቃላትም አበረታች ሐሳብ ይዘዋል። ጴጥሮስ እንዲህ ሲል ጽፏል:- ‘አምላክ የጽድቅ ሰባኪ የነበረውን ኖኅን ከሌሎች ሰባት ሰዎች ጋር አድኖ ለቀድሞው ዓለም ሳይራራ በኀጢአተኞች ላይ የጥፋት ውሃ ካመጣና ጻድቅ የሆነውን ሎጥን ካዳነ፣ ጌታ በእውነት እያመለኩት የሚኖሩትን ከፈተና እንዴት እንደሚያድናቸውና ዐመፀኞችን እየቀጣ ለፍርድ ቀን እንዴት ጠብቆ እንደሚያቈያቸው ያውቃል።’ (2 ጴጥሮስ 2:5-9) ቀደም ባሉት ጊዜያት ይሖዋ ክፉዎችን ያጠፋ ቢሆንም እርሱን በታማኝነት ያገለገሉት ኖኅና ሎጥ ግን በሕይወት እንዲተርፉ አድርጓል። ክፉዎች በአርማጌዶን በሚጠፉበት ጊዜም ይሖዋ ለእርሱ ያደሩ ሕዝቦችን ያድናቸዋል። “ብዙ ሕዝብ” ተብለው የተጠሩት ጻድቃን በሕይወት ይተርፋሉ።—ራእይ 7:9, 14

ስለዚህ በሶፎንያስ 2:3 ላይ “ይሆናል” የሚለው ቃል የገባው አምላክ የእርሱን ሞገስ ያገኙ ሰዎችን ለማዳን መቻሉ አጠራጣሪ መሆኑን ለማሳየት አይመስልም። ከዚህ ይልቅ አንድ ግለሰብ በይሖዋ የቁጣ ቀን መሰወሩ አጠራጣሪ የሚሆነው ጽድቅንና ትሕትናን መፈለግ በጀመረበት ወቅት ላይ ነው። ግለሰቡ የይሖዋን ጥበቃ እንዲያገኝ ትሕትናንና ጽድቅን በመፈለግ መጽናት ይኖርበታል።—ሶፎንያስ 2:3

[በገጽ 31 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

‘ይሖዋ፣ በእውነት እያመለኩት የሚኖሩትን ከፈተና እንዴት እንደሚያድናቸው ያውቃል’