በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ንድፍ አውጪ አለው?

እርጥበት የመሳብ ችሎታ ያለው የናሚብ ጥንዚዛ ክንፍ ሽፋን

እርጥበት የመሳብ ችሎታ ያለው የናሚብ ጥንዚዛ ክንፍ ሽፋን

● በመላው ዓለም 900 ሚሊዮን የሚያህሉ ሰዎች ንጹሕ የመጠጥ ውኃ አያገኙም። በብዙ አካባቢዎች ደግሞ ረጅም ርቀት ተጉዞ ውኃ የመቅዳቱ ኃላፊነት የሚወድቀው በሴቶችና በልጆች ላይ ነው። በማሳቹሴትስ የቴክኖሎጂ ተቋም መሐንዲስ የሆኑት ሽሬራንግ ቻትሪ “ድሆች መሠረታዊ ፍላጎታቸውን ለማሟላት በየቀኑ ረጅም ሰዓት በእግር ለመጓዝ መገደዳቸው በጣም የሚያሳዝን ነው” ብለዋል። ቻትሪና ባልደረቦቻቸው ለዚህ ችግር መፍትሔ ለማግኘት ሲሉ በጉም ውስጥ የሚገኘውን እርጥበት ሰብስቦ ማውጣት ስለሚቻልበት ሳይንስ ጥናት በማድረግ ላይ ናቸው፤ ለዚህም የመነሻ ሐሳብ ያገኙት ከናሚብ ጥንዚዛ ነው።

እስቲ የሚከተለውን አስብ፦ ማለዳ ላይ በአፍሪካ የሚገኘው የናሚብ በረሃ በጉም ይሸፈናል። የናሚብ ጥንዚዛ ለአጭር ጊዜ በሚቆየው በዚህ አጋጣሚ ለመጠቀም ስትል በትክክለኛው ቦታ ትቆማለች። * በክንፎቿ ሽፋን ላይ ያሉት ጉብ ጉብ ያሉ ነገሮች የተሠሩት እርጥበትን መሳብ ከሚችሉ ንጥረ ነገሮች ነው። እርጥበቱ ውስጥ ያሉት የውኃ ቅንጣቶች ጠርቀምቀም ሲሉ ተለቅ ያለ ጠብታ ይፈጥራሉ። ከዚያም የስበት ኃይል ጠብታው በጥንዚዛዋ ክንፍ ሽፋን ላይ ባሉት ጉብ ያሉ ነገሮች መካከል ወደሚገኝ ቦይ መሳይ ነገር እንዲንከባለል ያደርገዋል። በጥንዚዛዋ ክንፍ ሽፋን ላይ የሚገኙት ቦዮች ደግሞ ውኃ የማያስገቡ በመሆናቸው ጠብታዎቹ ኮለል ብለው በመውረድ ወደ ጥንዚዛዋ አፍ ይገባሉ።

ቻትሪና ባልደረቦቻቸው ተመሳሳይ ዘዴ በመጠቀም ለሰዎች የመጠጥ ውኃ ለማግኘት እየጣሩ ነው። እርግጥ ነው፣ የሰው ልጆች የሚያስፈልጋቸው ውኃ የናሚብ ጥንዚዛ ከሚያስፈልጋት መጠን የበለጠ ነው። በተጨማሪም እንዲህ ያለውን ዘዴ ሥራ ላይ ለማዋል የሚያስፈልገውን ገንዘብ ማግኘት ተፈታታኝ ነው። ሰዎች ከጉም ላይ ውኃ ለማግኘት የሚያደርጉት ጥረት “ገና በጅምር ላይ የሚገኝ” ነገር እንደሆነ ቻትሪ ተናግረዋል።

ታዲያ ምን ይመስልሃል? እርጥበት የመሳብ ችሎታ ያለው የናሚብ ጥንዚዛ ክንፍ ሽፋን በዝግመተ ለውጥ የተገኘ ነው? ወይስ ንድፍ አውጪ አለው?

[የግርጌ ማስታወሻ]

^ አን.4 ሌሎች የጥንዚዛ ዝርያዎችም ውኃ ለማግኘት ተመሳሳይ ዘዴ ይጠቀማሉ።

[በገጽ 22 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

የውኃ ጠብታዎቹ ኮለል ብለው ወደ ጥንዚዛዋ አፍ ይገባሉ

[በገጽ 22 ላይ የሚገኝ የሥዕል ምንጭ]

Photo: Chris Mattison Photography/photographersdirect.com