በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ማጨስ የማልፈልግበት ምክንያት

ማጨስ የማልፈልግበት ምክንያት

ማጨስ የማልፈልግበት ምክንያት

በዩናይትድ ስቴትስ ሚዙሪ ስቴት ሜዲካል አሶሲዬሽን (MSMA) የተባለ አንድ ድርጅት በዚህ ርዕስ አገር አቀፍ የተማሪዎች የሥነ ጽሑፍ ውድድር አዘጋጅቶ ነበር። ከ42 ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ 675 ተማሪዎች በውድድሩ ተካፍለዋል። ሽልማቱን ያገኘችው ብሪያን የተባለች አንዲት የ12 ዓመት ልጅ ስትሆን አሸናፊ የሆነችበት ግጥም ሚዙሪ ሜዲስን በተባለው የድርጅቱ መጽሔት ላይ ታትሞ ወጥቷል። ከዚህም በላይ ብሪያን ግጥሙን በድርጅቱ ዓመታዊ ጉባኤ ላይ ለተገኙ ተሰብሳቢዎች የማንበብ አጋጣሚ አግኝታለች። ግጥሟን ከማንበቧ በፊት እንዲህ ብላ ነበር:-

“እኔ የይሖዋ ምሥክር ስሆን በግጥሜ ውስጥ ያሰፈርኳቸውን ሐሳቦች በሙሉ የወሰድኩት ከንቁ! መጽሔት ላይ ነው። እንዲያውም በጣም ከወደድኳቸው ስንኞች መካከል የአንደኛውን ሐሳብ የወሰድኩት ከዚህ [ከሐምሌ 8, 1989 ንቁ!] እትም የመጀመሪያ ገጽ ላይ ነው። የሽፋኑ ሥዕል በአፉ ሲጋራ የያዘ የራስ ቅል የሚያሳይ ሲሆን ‘ሞትን በገንዘብ መግዛት’ ይላል። ንቁ! መጽሔት ለበርካታ ዓመታት ስለ ሲጋራ አደገኝነት የሚናገሩ ብዙ ርዕሶችን ይዞ ወጥቷል።”

የይሖዋ ምሥክሮች ሲጋራ ከማጨስ ይርቃሉ። ሰውነትን የሚያረክስ ማንኛውንም ዓይነት ነገር ሆነ ብሎ መጠቀም ለፈጣሪ እንዲሁም የእርሱ ስጦታ ለሆነው ለሕይወት አክብሮት አለማሳየት እንደሆነ ይሰማቸዋል። (የሐዋርያት ሥራ 17:24, 25) በመሆኑም “ሥጋንና መንፈስን ከሚያረክስ ነገር ሁሉ ራሳችንን እናንጻ” የሚለውን ቅዱስ ጽሑፋዊ ማሳሰቢያ ይከተላሉ።—2 ቆሮንቶስ 7:1

እንደ ሌሎች ወጣት የይሖዋ ምሥክሮች ሁሉ ብሪያንም በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶች ለመመራት ጥረት ታደርጋለች። እነዚህ ወጣቶች ሁሉ የፈጣሪን ልብ ደስ እንደሚያሰኙ አያጠራጥርም።—ምሳሌ 27:11

[በገጽ 29 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

ብሪያን (አሁን 14 ዓመቷ ነው) የጻፈችውን ግጥም ይዛ