በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

2 | ‘ከቅዱሳን መጻሕፍት የምናገኘው መጽናኛ’

2 | ‘ከቅዱሳን መጻሕፍት የምናገኘው መጽናኛ’

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል? “በምናሳየው ጽናትና ከቅዱሳን መጻሕፍት በምናገኘው መጽናኛ ተስፋ ይኖረን ዘንድ ቀደም ብሎ የተጻፈው ነገር ሁሉ ለእኛ ትምህርት እንዲሆን ተጽፏል።”—ሮም 15:4

ምን ማለት ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ የሚያጽናኑ ሐሳቦችን ይዟል፤ እነዚህ ሐሳቦች አፍራሽ አስተሳሰቦችን ለማሸነፍ የሚያስፈልገንን ብርታት ይሰጡናል። በተጨማሪም መጽሐፍ ቅዱስ፣ የስሜት ሥቃይ ያለፈ ታሪክ የሚሆንበት ጊዜ እንደሚመጣ ተስፋ ይሰጠናል።

የሚረዳን እንዴት ነው?

ሁላችንም አልፎ አልፎ ሐዘን ይሰማናል። ሆኖም ድባቴ ወይም ጭንቀት ያለባቸው ሰዎች በየዕለቱ ከማያቋርጥ የስሜት ሥቃይ ጋር መታገል ሊያስፈልጋቸው ይችላል። ታዲያ መጽሐፍ ቅዱስ ሊረዳቸው የሚችለው እንዴት ነው?

  • በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉት አዎንታዊ ሐሳቦች በውስጣችን ያለውን አሉታዊ አስተሳሰብ ለማሸነፍ ይረዱናል። (ፊልጵስዩስ 4:8) መጽሐፍ ቅዱስ አእምሯችን በሚያጽናኑና በሚያረጋጉ ሐሳቦች እንዲሞላ ይረዳናል፤ ይህ ደግሞ ስሜታችንን ለመቆጣጠር ያስችለናል።—መዝሙር 94:18, 19

  • የከንቱነት ስሜት የሚሰማን ከሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ይህን ስሜት ለማሸነፍ ይረዳናል።—ሉቃስ 12:6, 7

  • ብቻችንን እንዳልሆንን እንዲሁም ፈጣሪያችን ስሜታችንን ሙሉ በሙሉ እንደሚረዳልን ዋስትና የሚሰጡን ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች አሉ።—መዝሙር 34:18፤ 1 ዮሐንስ 3:19, 20

  • መጽሐፍ ቅዱስ፣ አምላክ መጥፎ ትዝታዎችን በሙሉ እንደሚያስወግድ ተስፋ ይሰጠናል። (ኢሳይያስ 65:17፤ ራእይ 21:4) የሚረብሹ ሐሳቦችና ስሜቶች ሲመጡብን ይህ ተስፋ ለመጽናት የሚያስችል ብርታት ሊሰጠን ይችላል።

a “ድባቴ” በመባል የሚታወቀው የአእምሮ ችግር “ድብርት” ወይም “የመንፈስ ጭንቀት” ተብሎም ይጠራል።