በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ሣጥን 7ለ

በሕዝቅኤል መጽሐፍ ውስጥ የሚገኙ ቁልፍ አገላለጾች

በሕዝቅኤል መጽሐፍ ውስጥ የሚገኙ ቁልፍ አገላለጾች

“የሰው ልጅ”

ከ90 ጊዜ በላይ ተጠቅሶ ይገኛል

ሕዝቅኤል ከ90 ጊዜ በላይ “የሰው ልጅ” ተብሎ ተጠርቷል። (ሕዝ. 2:1) በዚህ መንገድ ይሖዋ ሕዝቅኤልን ታላላቅ መብቶች ያገኘ ቢሆንም ተራ ምድራዊ ሰው እንደሆነ እንዲያስታውስ አድርጎታል። ኢየሱስም በወንጌል ዘገባዎች ውስጥ 80 ጊዜ ያህል “የሰው ልጅ” ተብሎ መጠራቱ ትኩረት የሚስብ ነው፤ ይህም የሰው ሥጋ የለበሰ መልአክ ሳይሆን ሙሉ በሙሉ ሰው እንደነበረ ያመለክታል።—ማቴ. 8:20

“እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ”

ከ50 ጊዜ በላይ ተጠቅሶ ይገኛል

አምላክ የተናገራቸው “እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ” እንዲሁም “እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ” እንደሚሉት ያሉ አገላለጾች በሕዝቅኤል መጽሐፍ ውስጥ ከ50 ጊዜ በላይ ተመዝግበው ይገኛሉ፤ ይህም ንጹሕ አምልኮ ሊቀርብ የሚገባው ለይሖዋ ብቻ መሆኑን ያጎላል።—ሕዝ. 6:7

“ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ”

217 ጊዜ ተጠቅሶ ይገኛል

“ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ” የሚለው አገላለጽ በሕዝቅኤል መጽሐፍ ውስጥ 217 ጊዜ ይገኛል። ይህም መለኮታዊው ስም፣ የሚገባውን ጉልህ ቦታ እንዲያገኝ ያደረገ ሲሆን ሁሉም ፍጥረት የይሖዋ የበታች መሆኑን ያስገነዝባል።—ሕዝ. 2:4