የይሖዋ ንጹሕ አምልኮ መልሶ ተቋቋመ!

የሕዝቅኤል መጽሐፍ ንጹሕ አምልኮ መልሶ እንደሚቋቋም የሚገልጹ በርካታ ትንቢቶችን ይዟል። የእነዚህ ትንቢቶች ፍጻሜ ከእኛ ጋር ምን ግንኙነት አለው?

የበላይ አካሉ መልእክት

ይህ መጽሐፍ ለይሖዋ የሚገባውን ንጹሕ አምልኮ ማቅረብ እንድትችሉ እንዲረዳችሁ እንመኛለን።

የመጽሐፉ ልዩ ገጽታዎች ማብራሪያ

በመጽሐፉ ውስጥ የሚገኙት ሣጥኖችና የጊዜ ሰሌዳዎች ግንዛቤህን ለማስፋት የሚረዳ ተጨማሪ መረጃ ይዘዋል።

ምዕራፍ 1

“ይሖዋ አምላክህን ብቻ አምልክ”

ሰይጣን በኤደን ዓመፅ እንዲቀሰቀስ በማድረግ የይሖዋን የመግዛት መብት ከመገዳደር አልፎ በንጹሕ አምልኮ ላይ ጥቃት ሰንዝሯል።

ምዕራፍ 2

‘አምላክ ስጦታቸውን ተቀብሏል’

ታማኝ ሰዎች የተዉት ምሳሌ አንድ ሰው የሚያቀርበው አምልኮ ተቀባይነት እንዲያገኝ አራት መሠረታዊ መሥፈርቶች መሟላት እንዳለባቸው ያሳያል።

ምዕራፍ 3

“አምላክ የገለጠልኝን ራእዮች ማየት ጀመርኩ”

ሕዝቅኤል ያየው የመጀመሪያ ራእይ በጣም አስደንግጦታል። ይህ ራእይ በዛሬው ጊዜ ለሚኖሩ የአምላክ አገልጋዮች ጥልቅ ትርጉም አለው።

ምዕራፍ 4

‘አራት ፊት ያላቸው አራቱ ሕያዋን ፍጥረታት’ ምን ያመለክታሉ?

ይሖዋ ለመረዳት የሚከብዱ እውነታዎችን ለማስተማር ሲል ለሕዝቅኤል ራእይ አሳይቶታል።

ምዕራፍ 5

“የሚሠሯቸውን ክፉና አስጸያፊ ነገሮች ተመልከት”

ሕዝቅኤል መላው ብሔር የደረሰበትን ያዘቀጠ መንፈሳዊ ሁኔታ የሚያሳዩ ትእይንቶችን ተመለከተ።

ምዕራፍ 6

“አሁን ፍጻሜሽ ደርሷል”

ሕዝቅኤል ያሳያቸው ትንቢታዊ ድራማዎች በኢየሩሳሌም ላይ የሚመጣውን የይሖዋ ቁጣ የሚያሳዩ ናቸው።

ምዕራፍ 7

ብሔራት “እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ”

የይሖዋን ስም ያቃለሉትም ሆኑ ሕዝቡን ያሳደዱት ወይም የበከሉት ብሔራት የእጃቸውን ማግኘታቸው አይቀርም። እስራኤል ከእነዚህ ብሔራት ጋር ከነበራት ግንኙነት ምን ትምህርት ማግኘት እንችላለን?

ምዕራፍ 8

“አንድ እረኛ . . . አስነሳለሁ”

ይሖዋ ሕዝቅኤልን በመንፈሱ በመምራት ስለ መሲሑ ማለትም ንጹሕ አምልኮን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መልሶ ስለሚያቋቁመው እረኛና ገዢ ትንቢት እንዲናገር አድርጓል።

ምዕራፍ 9

“አንድ ልብ እሰጣቸዋለሁ”

በባቢሎን ለሚኖሩት ታማኝ አይሁዳውያን ግዞተኞች የተነገሩት ትንቢቶች ለእኛም የያዙት መልእክት አለ?

ምዕራፍ 10

“ሕያው ትሆናላችሁ”

ሕዝቅኤል በአንድ ሸለቆ ውስጥ የተከመሩ የደረቁ አጥንቶች ሕያው ሲሆኑ በራእይ አየ። የራእዩ ትርጉም ምንድን ነው?

ምዕራፍ 11

“ጠባቂ አድርጌ ሾሜሃለሁ”

ይህ ጠባቂ ያለው ኃላፊነት ምንድን ነው? ምን ዓይነት ማስጠንቀቂያ ማወጅ ነበረበት?

ምዕራፍ 12

“አንድ ብሔር አደርጋቸዋለሁ”

ይሖዋ ሕዝቦቹን አንድ እንደሚያደርግ ተስፋ ሰጠ።

ምዕራፍ 13

“ስለ ቤተ መቅደሱ ግለጽላቸው”

ሕዝቅኤል በራእይ ያየው ቤተ መቅደስ ትርጉም ምንድን ነው?

ምዕራፍ 14

“የቤተ መቅደሱ ሕግ ይህ ነው”

በግዞት የነበሩት አይሁዳውያን ሕዝቅኤል ስለ ቤተ መቅደሱ ካየው ራእይ ምን ትምህርት አግኝተው መሆን አለበት? ይህ ራእይ እኛንስ ምን ያስተምረናል?

ምዕራፍ 15

“ምንዝርሽንም አስተውሻለሁ”

በሕዝቅኤልና በራእይ መጽሐፍ ውስጥ ስለተጠቀሱት ዝሙት አዳሪዎች ወይም አመንዝሮች ከተሰጠው መግለጫ ምን ትምህርት እናገኛለን?

ምዕራፍ 16

‘በግንባራቸው ላይ ምልክት አድርግ’

በሕዝቅኤል ዘመን የነበሩ ታማኝ ሰዎች ከጥፋት እንዲተርፉ ምልክት የተደረገባቸው እንዴት እንደሆነ ማወቃችን ለእኛም ይጠቅመናል።

ምዕራፍ 17

“ጎግ ሆይ፣ እኔ በአንተ ላይ ተነስቻለሁ”

የማጎጉ ጎግ ማን ነው? የሚወረው ‘ምድርስ’ ምንድን ነው?

ምዕራፍ 18

“ታላቅ ቁጣዬ ይነድዳል”

ጎግ የሚሰነዝረው ጥቃት የይሖዋን ቁጣ በመቀስቀስ ሕዝቦቹን እንዲታደግ ያደርገዋል።

ምዕራፍ 19

“ጅረቱ በሚፈስበት ቦታ ያለው ነገር ሁሉ በሕይወት ይኖራል”

ሕዝቅኤል ከቤተ መቅደሱ ወጥቶ ስለሚፈስ ወንዝ ያየው ራእይ በጥንት ዘመንና በአሁኑ ጊዜ ፍጻሜውን አግኝቷል ወደፊትም ፍጻሜውን ያገኛል የምንለው ለምንድን ነው?

ምዕራፍ 20

‘ምድሪቱን ርስት አድርጋችሁ ተከፋፈሉ’

አምላክ በራእይ አማካኝነት ሕዝቅኤልንና ግዞተኛ ወገኖቹን ተስፋይቱን ምድር ለእስራኤል ነገዶች እንዲያከፋፍሉ ነገራቸው።

ምዕራፍ 21

“ከተማዋ ‘ይሖዋ በዚያ አለ’ ተብላ ትጠራለች”

ሕዝቅኤል ስለ ከተማዋ ካየው ራእይና ከከተማዋ ስም ምን ትምህርት እናገኛለን?

ምዕራፍ 22

“ለአምላክ ስገድ”

ይህ መጽሐፍ የተዘጋጀው ይሖዋ አምላክን ብቻ ለማምለክ ያለንን ቁርጠኝነት እንድናጠናክር ለመርዳት ታስቦ ነው።

ማስተካከያ የተደረገባቸው ትምህርቶች

በሕዝቅኤል መጽሐፍ ውስጥ ከሚገኙ አንዳንድ ትንቢቶች ጋር በተያያዘ በነበረን ግንዛቤ ላይ ማስተካከያ ያደረግነው ለምንድን ነው?

ሣጥን 1ሀ

አምልኮ ምንድን ነው?

አምልኮ ሲባል ምን ማለት ነው? በሕዝቅኤል መጽሐፍ ውስጥ የአምልኮ ጉዳይ ጎላ ተደርጎ የተገለጸው እንዴት ነው? ንጹሕ አምልኮ ምንን ይጨምራል?

ሣጥን 1ለ

የሕዝቅኤል መጽሐፍ አጠቃላይ ይዘት

መጽሐፉን በጊዜ ቅደም ተከተልም ሆነ በርዕሰ ጉዳይ ከፋፍሎ ማየት ይቻላል።

ሣጥን 2ሀ

የሕዝቅኤልን ትንቢቶች መረዳት

የሕዝቅኤል መጽሐፍ ራእዮችን፣ ምሳሌዎችንና በድራማ መልክ የቀረቡ ትንቢታዊ መልእክቶችን አካቷል። ሁሉም ስለ ወደፊቱ ጊዜ የሚናገሩ መለኮታዊ መልእክቶች ናቸው።

ሣጥን 2ለ

ሕዝቅኤል—ያሳለፈው ሕይወትና የኖረበት ዘመን

ሕዝቅኤል በኖረበት ዘመን ትንቢት የሚናገሩ ሌሎች ነቢያትም ነበሩ። በሕዝቅኤል የሕይወት ዘመን፣ በይሖዋ ሕዝቦች ታሪክ ውስጥ ጉልህ ቦታ የሚሰጣቸው ክንውኖች ተፈጽመዋል።

ሣጥን 3ሀ

ወደ ባቢሎን የሚወስደው ረጅም መንገድ

ግዞተኞቹ ከይሁዳ ወደ ባቢሎን ሲወሰዱ የሄዱት የትኛውን መንገድ ተከትለው ሊሆን ይችላል?

ሣጥን 4ሀ

‘ሕያዋን ፍጥረታቱን እየተመለከትኩ ነበር’

ሕዝቅኤል በራእይ ባያቸው አራት ፍጥረታትና በጥንቷ አሦርና ባቢሎን ይገኙ በነበሩት ግዙፍ ሐውልቶች መካከል ያለው ልዩነት ምን ነበር?

ሣጥን 5ሀ

“የሰው ልጅ ሆይ፣ ይህን ታያለህ?”

ሕዝቅኤል በቤተ መቅደሱ ውስጥ አራት አስጸያፊ ነገሮች ሲፈጸሙ ተመለከተ።

ሣጥን 6ሀ

“የራስህን ፀጉርና ጢምህን ተላጭ”

አምላክ ሕዝቅኤልን በቅርቡ በኢየሩሳሌም ላይ የሚደርሰውን ነገር የሚያሳዩ ትንቢታዊ ድራማዎችን እንዲያሳይ አዘዘው።

ሣጥን 7ሀ

በኢየሩሳሌም ዙሪያ የነበሩት ብሔራት

ይሁዳና በዙሪያዋ የነበሩት አገሮች ከፍተኛ የሥልጣን ሽኩቻ የሚደረግባቸው መድረኮች ነበሩ።

ሣጥን 7ለ

በሕዝቅኤል መጽሐፍ ውስጥ የሚገኙ ቁልፍ አገላለጾች

በዚህ የትንቢት መጽሐፍ ውስጥ አንዳንድ አገላለጾች በተደጋጋሚ ተጠቅሰው ይገኛሉ።

ሣጥን 8ሀ

ስለ መሲሑ የሚናገር ትንቢት—የሚያምር የአርዘ ሊባኖስ ዛፍ

በሕዝቅኤል ምዕራፍ 17 ላይ የሚገኘው እንቆቅልሽ ትርጉም ምንድን ነው?

ሣጥን 8ለ

ስለ መሲሑ የተነገሩ ሦስት ትንቢቶች

ሕዝቅኤል ወደፊት በሚነሳው የአምላክ ሕዝቦች ገዢ ላይ እምነት ልንጥልበት እንደሚገባ ተንብዮአል።

ሣጥን 9ሀ

ይሖዋ የሰጠው ተስፋ ይፈጸማል—በጥንት ዘመን

አምላክ ሕዝቅኤልን በመንፈሱ በመምራት አይሁዳውያን ነፃ ወጥተው ወደ አገራቸው ከመመለሳቸው ጋር በተያያዘ አምስት ተስፋዎችን እንዲናገር አድርጎታል።

ሣጥን 9ለ

በ1919 ነው የምንለው ለምንድን ነው?

የአምላክ ሕዝቦች ከታላቂቱ ባቢሎን ምርኮ ነፃ የወጡት በ1919 ነው የምንለው ለምንድን ነው?

ሣጥን 9ሐ

ይሖዋ የሰጠው ተስፋ ይፈጸማል—በዘመናችን

አምላክ የሰጣቸው አንዳንድ ተስፋዎች ሁለት ፍጻሜ የኖራቸው እንዴት ነው?

ሣጥን 9መ

ስለ ግዞትና ስለ መልሶ መቋቋም የሚገልጹ ትንቢቶች

አይሁዳውያን በጥንቷ ባቢሎን በግዞት ስለመወሰዳቸውና መልሰው ስለ መቋቋማቸው የሚናገሩት ትንቢቶች ከረጅም ጊዜ በኋላ የክርስቲያን ጉባኤ በታላቂቱ ባቢሎን በምርኮ በተያዘበትና ከጊዜ በኋላ መልሶ በተቋቋመበት ወቅት በላቀ ሁኔታ ፍጻሜያቸውን አግኝተዋል።

ሣጥን 9ሠ

“ነገሮች ሁሉ የሚታደሱበት ዘመን”

ሐዋርያው ጴጥሮስ በሐዋርያት ሥራ 3:21 ላይ ክርስቶስ ንጉሥ ሆኖ መግዛት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ እስከ ሺው ዓመት መጨረሻ ድረስ ስለሚኖረው ጊዜ በመንፈስ ተመርቶ ትንቢት ተናግሯል።

ሣጥን 10ሀ

ንጹሕ አምልኮ ቀስ በቀስ መልሶ ተቋቋመ

የስብከቱ ሥራ በዘመናችን እንዲጀመር መንገድ የጠረጉት ነገሮች የትኞቹ ናቸው?

ሣጥን 10ለ

‘በደረቁት አጥንቶች’ እና ‘በሁለቱ ምሥክሮች’ መካከል ያለው ዝምድና ምንድን ነው?

እነዚህ ትንቢቶች በዘመናችን ፍጻሜያቸውን ያገኙት እንዴት ነው?

ሣጥን 10ሐ

ተመልሰን በእግራችን እንድንቆም የሚያስችል እርዳታ

አንዳንድ ጊዜ ችግሮች ሊደራረቡብን ወይም ልንዝል እንችላለን፤ ሆኖም ወደ ሕይወት ስለተመለሱት የደረቁ አጥንቶች የሚገልጸው ራእይ ብርታት ይሰጠናል።

ሣጥን 11ሀ

ምሳሌ የሚሆኑ አንዳንድ ጠባቂዎች

ተቃውሞ ደርሶባቸዋል፤ በታማኝነት ጸንተዋል እንዲሁም ማስጠንቀቂያና ምሥራች አውጀዋል።

ሣጥን 12ሀ

የሁለቱ በትሮች አንድ መሆን

እነዚህ በትሮች በጥንት ዘመን እንዲሁም በዘመናችን እነማንን ያመለክታሉ?

ሣጥን 13ሀ

የተለያዩ ቤተ መቅደሶች፣ የተለያዩ ትምህርቶች

ሕዝቅኤል በራእይ ያየው ቤተ መቅደስ ሐዋርያው ጳውሎስ ከጠቀሰው መንፈሳዊ ቤተ መቅደስ የሚለየው በምን መንገድ ነው?

ሣጥን 14ሀ

ሕዝቅኤል ስለ ቤተ መቅደሱ ካየው ራእይ የምናገኛቸው ትምህርቶች

ሕዝቅኤል ስለ ቤተ መቅደሱ ካየው ራእይ ውስጥ ለይሖዋ ከምታቀርበው አምልኮ ጋር በተያያዘ ተግባራዊ ልታደርግ የምትችለው ትምህርት አግኝተሃል?

ሣጥን 15ሀ

ዝሙት አዳሪዎቹ እህትማማቾች

ይሖዋ ስለ ኦሆላና ኦሆሊባ የገለጸው ነገር የእሱ ሕዝቦች እንደሆኑ እየተናገሩ ቅዱስ ስሙን ለሚያሰድቡና ለንጹሕ አምልኮ ያወጣውን መሥፈርት ለማያከብሩ ሁሉ ያለውን አመለካከት ያሳያል።

ሣጥን 16ሀ

ኢየሩሳሌም ለሕዝበ ክርስትና ጥላ ነች?

አመለካከታችንን ማስተካከል ያስፈለገን ለምንድን ነው?

ሣጥን 16ለ

ማዘንና መቃተት፣ ምልክት ማድረግ፣ ማጥፋት—መቼና እንዴት?

በሕዝቅኤል ምዕራፍ 9 ላይ ተመዝግቦ የሚገኘው ራእይ የዚህን ሥርዓት መጨረሻ በልበ ሙሉነት እንድንጠባበቅ ያስችለናል።

ሣጥን 18ሀ

ይሖዋ ስለ መጪው ታላቅ ጦርነት የሰጠው ማስጠንቀቂያ

መጽሐፍ ቅዱስ አምላክ ተቃዋሚዎቹን በሙሉ የሚያጠፋበት ታላቅ ጦርነት እንደሚመጣ ይተነብያል።

ሣጥን 19ሀ

የይሖዋን በረከት የሚያስገኙ ወንዞች

የተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎች የይሖዋን በረከት ለመግለጽ ተመሳሳይ ምሳሌ ተጠቅመዋል።

ሣጥን 19ለ

ቀስ እያለ የሚፈሰው ውኃ ትልቅ ወንዝ ሆነ!

ከአምላክ ቤተ መቅደስ ወጥቶ የሚፈሰው ወንዝ ምን ያመለክታል?

ሣጥን 20ሀ

የምድሪቱ አከፋፈል

ሕዝቅኤል ስለ ምድሪቱ አከፋፈል ያየው ራእይ በባቢሎን ለነበሩት ግዞተኞች ብቻ ሳይሆን በዛሬው ጊዜ ላሉት የአምላክ ሕዝቦችም አበረታች መልእክት ይዟል።

ሣጥን 21ሀ

“መዋጮ አድርጋችሁ ለመስጠት የምትለዩት መሬት”

አምላክ የለየው የምድሪቱ ክፍል የትኞቹን 5 ቦታዎች ያቀፈ ነው? እነዚህ ቦታዎች ምን ዓላማ ነበራቸው?

ሣጥን 22ሀ

የመጨረሻው ፈተና

የመጨረሻውን ፈተና የሚያልፉ ሰዎች ምን ይጠብቃቸዋል?