በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም አሌክሳንደር ሉቢን እና ባለቤቱ ታትያና

የካቲት 5, 2024
ሩሲያ

“መንገድህን ለይሖዋ አደራ ስጥ”

“መንገድህን ለይሖዋ አደራ ስጥ”

በኩርጋን ክልል የሚገኘው የሻድሪንስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት፣ በወንድም አሌክሳንደር ሉቢን ክስ ላይ በቅርቡ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል። አቃቤ ሕጉ እንዲተላለፍበት የሚፈልገውን ብይን ገና አላሳወቀም።

አጭር መግለጫ

ምንም ዓይነት አስጨናቂ ሁኔታ ቢገጥመን የይሖዋ ድጋፍ እስካለን ድረስ እኛም እንደ አሌክሳንደር በታማኝነት መጽናት እንደምንችል ሙሉ እምነት አለን።​—ኢሳይያስ 38:14

የክሱ ሂደት

  1. ሐምሌ 13, 2021

    የወንጀል ክስ ተመሠረተበት

  2. ሐምሌ 14, 2021

    የስምንት የይሖዋ ምሥክሮች ቤቶች ተፈተሹ። አሌክሳንደር በቁጥጥር ሥር ውሎ ምርመራ ተደረገበት፤ ከዚያም ጣቢያ እንዲቆይ ተደረገ

  3. ሐምሌ 16, 2021

    ወደ ማረፊያ ቤት ተላከ

  4. ሐምሌ 19, 2021

    ባለበት ከባድ የጤና እክል ምክንያት አቤቱታ አቀረበ

  5. ነሐሴ 28, 2021

    በአውሮፓ የሰብዓዊ መብቶች ፍርድ ቤት እና በአንዳንድ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ጥያቄ አሌክሳንደር ተፈታ። ሆኖም የጉዞ ገደብ ተጣለበት

  6. ሐምሌ 14, 2023

    ክሱ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ

  7. መስከረም 7, 2023

    አሌክሳንደር ሐኪም ቤት በመተኛቱ ምክንያት የችሎት ቀጠሮው ለሌላ ጊዜ ተላለፈ