በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

የአምላክን የማይታዩ ባሕርያት ታስተውላለህ?

የአምላክን የማይታዩ ባሕርያት ታስተውላለህ?

በቀለማት ያሸበረቁ አበቦችን፣ በከዋክብት የተሞላውን ሰማይ ወይም እየተንዶለዶለ የሚወርድ ፏፏቴ ስትመለከት የፈጣሪን ሥራ ታደንቃለህ? የይሖዋን የማይታዩ ባሕርያት በዙሪያችን ካሉት ፍጥረታት በግልጽ መመልከት እንችላለን። (ሮም 1:20) በምናያቸው ነገሮች ላይ ቆም ብለን የምናሰላስል ከሆነ የአምላክን ኃይል፣ ፍቅር፣ ጥበብና ፍትሕ አልፎ ተርፎም ልግስናውን ማስተዋል እንችላለን።—መዝ 104:24

ከይሖዋ የፍጥረት ሥራዎች መካከል በየዕለቱ የትኞቹን የመመልከት አጋጣሚ አለህ? የምትኖረው ከተማ ውስጥ ቢሆንም እንኳ ወፎችን ወይም ዛፎችን ማየትህ አይቀርም። የይሖዋን የፍጥረት ሥራዎች በትኩረት መመልከታችን፣ ከልክ በላይ እንዳንጨነቅና ይበልጥ አስፈላጊ በሆኑት ነገሮች ላይ እንድናተኩር ይረዳናል፤ በተጨማሪም ይሖዋ እኛን ለዘላለም መንከባከብ እንደሚችል ያለንን እምነት ያጠናክረዋል። (ማቴ 6:25-32) ልጆች ካሏችሁ፣ ወደር የሌላቸውን የይሖዋ ባሕርያት እንዲያስተውሉ እርዷቸው። ለአምላክ የፍጥረት ሥራዎች ያለን አድናቆት እየጨመረ መሄዱ ወደ ፈጣሪያችን ይበልጥ እንድንቀርብ ያደርገናል።—መዝ 8:3, 4

አስደናቂ የፍጥረት ሥራዎች የአምላክን ክብር ይገልጣሉ—ብርሃን እና ቀለም የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • ቀለማትን ለማየት የሚያስችለን ምንድን ነው?

  • ኢሬደሰንስ ምንድን ነው?

  • በሰማይ ላይ የተለያዩ ቀለማት የምናየው ለምንድን ነው?

  • በምትኖርበት አካባቢ በሚገኙ የፍጥረት ሥራዎች ላይ የትኞቹን አስደናቂ ቀለማት ተመልክተሃል?

  • የፍጥረት ሥራዎችን ጊዜ ወስደን መመልከታችን ምን ጥቅም አለው?

ብርሃንና ቀለም ስለ ይሖዋ ባሕርያት ምን ያስተምሩናል?