በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ደፋሯ አስቴር

ደፋሯ አስቴር

አውርድ፦

 1. 1. አስቴር ታዛዥ ነበረች

  በትንሽነቷ፤

  አሳደጋት ባምላክ ምክር፣

  መርዶክዮስ ዘመዷ።

  ንግሥት ስትሆን አድጋ፣

  ቢቀየርም ሕይወቷ፤

  ታዛዥና ደፋር ሴት ነች፤

  አስቴር ጎበዟ!

  (አዝማች)

  እኔም ልክ እንደ አስቴር

  ደፋር ሰው እሆናለሁ፤

  ስለ ይሖዋ በድፍረት

  እመሠክራለሁ።

  እኔም ልክ እንደ አስቴር

  ታዛዥ ሰው እሆናለሁ።

  እንደ’ሷ መሆን ነው፣

  እኔ ’ምፈልገው!

 2. 2. ባሏ አምላክን ’ማያውቅ

  ቁጡ ንጉሥ ነበር፤

  አስቴር ግን በአክብሮት

  ታናግረው ነበር።

  ሕዝቧን እንድታድን

  ስትጠየቅ እሺ አለች፤

  ታዛዥና ደፋር ሴት ነች።

  አስቴር ጎበዟ!

  (አዝማች)

  እኔም ልክ እንደ አስቴር

  ደፋር ሰው እሆናለሁ፤

  ስለ ይሖዋ በድፍረት

  እመሠክራለሁ።

  እኔም ልክ እንደ አስቴር

  ታዛዥ ሰው እሆናለሁ።

  እንደ’ሷ መሆን ነው፣

  እኔ ’ምፈልገው!