በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

እንደ ሙሴ የዋህ መሆን እፈልጋለሁ

እንደ ሙሴ የዋህ መሆን እፈልጋለሁ

አውርድ፦

 1. 1. ሙሴ ወላጆቹን በደንብ አዳምጧል።

  ሰምቶ ስለታዘዘ ያምላክ ወዳጅ ሆኗል።

  ወላጆቼ ሲያስተምሩኝ እሰማለሁ ሁሌ፤

  መሆን ስለምፈልግ የዋህ እንደ ሙሴ።

 2. 2. ከይሖዋ ተማረ፣ በግ እየጠበቀ፤

  ሌሎችን የሚያዳምጥ፣ ታጋሽ ሰው ሆነ።

  ይሖዋ ’ሚነግረኝን እሰማለሁ ሁሌ፤

  መሆን ስለምፈልግ የዋህ እንደ ሙሴ።

 3. 3. ይሖዋ ቢሾመውም ሕዝቡን ’ንዲመራ፣

  ሙሴ ግን ትሑት ነበር፣ ምክር የሚሰማ።

  ሲመክሩኝ ጓደኞቼ እሰማለሁ ሁሌ፤

  መሆን ስለምፈልግ የዋህ እንደ ሙሴ።

  (መደምደሚያ)

  ይሖዋ ’ሚነግረኝን እሰማለሁ ሁሌ፤

  መሆን ስለምፈልግ የዋህ እንደ ሙሴ።