በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የኢየሱስ ሕይወት ታሪክ

የኢየሱስ ሕይወት ታሪክ

አውርድ፦

 1. 1. ጨረቃና ከዋክብት

  በሰማይ ከመኖራቸው በፊት፤

  ልጁን ፈጠረ ’ምላክ።

  ኢየሱስ ምድር መጥቶ፣

  የታመሙትን በሙሉ ፈውሷል፤

  ኃይሉን አሳይቷል።

  ለሰው ልጆች ሲል ሕይወቱን ሰጥቷል።

  (አዝማች)

  እውነተኛ፣ በሁሉም ነገር ታማኝ፣

  ባቋሙ ’ሚጸና።

  “የነገሥታት ንጉሥ” ሆኗል፤ ሁሉን ይገዛል፤

  ለዘላለም ሰላም ያሰፍናል።

 2. 2. የወርቅ አክሊሉን ደፍቷል፤

  በቅርቡ መላዋን ምድር ይገዛል።

  ገነት ያደርጋታል።

  ያምላክ ተስፋ ሁሉ ይፈጸማል።

  (አዝማች)

  እውነተኛ፣ በሁሉም ነገር ታማኝ፣

  ባቋሙ ’ሚጸና።

  ከታዘዝነው ይመራናል፣ ኃይል ይሰጠናል፤

  ለዘላለም እንድንሆን ታማኝ።