በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

አምላክን “በአንድ ልብና በአንድ ሐሳብ” ማገልገል

አምላክን “በአንድ ልብና በአንድ ሐሳብ” ማገልገል

 አምላክን “በአንድ ልብና በአንድ ሐሳብ” ማገልገል

አይሁዳውያንና ወደ አይሁድ እምነት የተለወጡ ሰዎች በኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ዙሪያ ተሰብስበዋል። ወቅቱ የጴንጤቆስጤ በዓል የሚከበርበት ጊዜ ሲሆን እነዚህ ሰዎች በስተ ምዕራብ እስከ ሮም፣ በስተ ምሥራቅ ደግሞ እስከ ጳርቴና ካሉ በጣም ሩቅ ከሆኑ አካባቢዎች በዓሉን ለማክበር ወደ ኢየሩሳሌም የመጡ ናቸው። እዚያ የተሰበሰቡት ሰዎች የተለያየ ቋንቋ የሚናገሩ ሲሆኑ ከእነሱ ጋር እየተነጋገሩ ያሉት የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ግን የገሊላ ሰዎች ናቸው። በመሆኑም በዓሉን ለማክበር ከመጡት አንዳንዶቹ በጉዳዩ በመገረም “እያንዳንዳችን በተወለድንበት፣ በራሳችን ቋንቋ ሲናገሩ የምንሰማቸው እንዴት ቢሆን ነው?” በማለት ጠየቁ።—ሥራ 2:8

 ሐዋርያው ጴጥሮስ ከመካከላቸው ተነስቶ እያዩት ያለው ተአምር በምን ምክንያት እንደተከናወነ ገለጸ። እዚያ የተሰበሰበው ሕዝብ ወዲያው ምላሽ ሰጠ። በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተጠመቁ! (ሥራ 2:41) ምንም እንኳ ጉባኤው በፍጥነት እያደገ ቢሄድም አንድነቱን እንደጠበቀ ቀጥሏል። በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ታሪኩን የዘገበው ሉቃስ “ያመኑትም ሁሉ በአንድ ልብና በአንድ ሐሳብ ተስማምተው ነበር” ብሏል።—ሥራ 4:32

በ33 ከክርስቶስ ልደት በኋላ በጴንጤቆስጤ ዕለት የተጠመቁት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ስለ አዲሱ እምነታቸው ይበልጥ ለመማር በኢየሩሳሌም ረዘም ላለ ጊዜ ለመቆየት ፈለጉ። ወደዚያ ሲመጡ ግን ረዘም ላለ ጊዜ እንቆያለን የሚል ሐሳብ አልነበራቸውም። በመሆኑም ለተወሰነ ጊዜ ገንዘብ ማዋጣት አስፈልጎ ነበር። አንዳንድ አማኞች ያሏቸውን ንብረቶች በፈቃደኝነት በመሸጥ ገንዘቡ ለችግረኞች እንዲከፋፈል ለሐዋርያት አስረከቡ። (ሥራ 2:42-47) እንዴት ያለ ፍቅርና ልግስና የተንጸባረቀበት መንፈስ ነው!

እውነተኛ ክርስቲያኖች መቼም ቢሆን እንዲህ ዓይነቱን የፍቅርና የልግስና መንፈስ ሲያሳዩ ኖረዋል። በዛሬው ጊዜ የክርስቲያን ጉባኤ “በአንድ ልብና በአንድ ሐሳብ” ይሖዋን በጋራ ማገልገሉን ቀጥሏል። ሁሉም ክርስቲያኖች በግለሰብ ደረጃ ምሥራቹን ለመስበክና ከአምላክ መንግሥት ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን ለመደገፍ ጊዜያቸውን፣ ጉልበታቸውንና ገንዘባቸውን በልግስና ይሰጣሉ።— “አንዳንዶች መዋጮ የሚያደርጉባቸው መንገዶች” የሚለውን ሣጥን ተመልከት።

[በገጽ 6,7 ላይ የሚገኙ ሥዕሎች]

 አንዳንዶች መዋጮ የሚያደርጉባቸው መንገዶች

ለዓለም አቀፉ ሥራ የሚደረጉ መዋጮዎች

ብዙዎች “ለዓለም አቀፉ ሥራ” ተብሎ የተለጠፈባቸው ሣጥኖች ውስጥ የሚጨምሩት የተወሰነ ገንዘብ ያስቀምጣሉ ወይም ይመድባሉ።

ጉባኤዎች የተዋጣውን ገንዘብ በአገራቸው ሥራውን ለሚቆጣጠረው የይሖዋ ምሥክሮች ቢሮ በየወሩ ይልካሉ። ከዚህ በተጨማሪ በፈቃደኝነት የሚደረጉ የገንዘብ መዋጮዎችን በቀጥታ Watch tower Bible and Tract Society of New York, Inc., Attention Treasurer’s Office, 25 Columbia Heights, Brooklyn, New York 11201-2483 በሚለው አድራሻ ወይም በአገራችሁ ለሚገኘው የይሖዋ ምሥክሮች ቅርንጫፍ ቢሮ መላክ ይቻላል። ቼኮች ለ“የይሖዋ ምሥክሮች” የሚከፈሉ መሆናቸው መገለጽ አለበት። ከውድ ማዕድናት የተሠሩ ጌጣጌጦችን ወይም ሌሎች ውድ ዕቃዎችንም መስጠት ይቻላል። የተላከው ዕቃ ሙሉ በሙሉ ስጦታ መሆኑን የሚገልጽ አጭር ደብዳቤ ተያይዞ መላክ ይኖርበታል።

ተመላሽ ሊሆን የሚችል ገንዘብ የሚሰጥበት ዝግጅት

አንድ ሰው ገንዘቡን ዎች ታወር ባይብል ኤንድ ትራክት ሶሳይቲ ኦቭ ፔንስልቬንያ ዓለም አቀፉን ሥራ ለማካሄድ እንዲጠቀምበት በአደራ መልክ ሊሰጥና ሲያስፈልገው ማኅበሩን በመጠየቅ መልሶ ማግኘት ይችላል። ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት ከላይ በተገለጸው አድራሻ በመጻፍ ወይም በስልክ ቁጥር (718) 560-7500 በመደወል መጠየቅ ይቻላል።

በእቅድ የሚደረግ ስጦታ

ገንዘብ በስጦታ ከመለገስ በተጨማሪ በመላው ዓለም የሚካሄደውን የመንግሥቱን ሥራ መደገፍ የሚቻልባቸው ሌሎች መንገዶችም አሉ። እነዚህም የሚከተሉትን ያጠቃልላሉ፦

ኢንሹራንስ፦ የፔንስልቬንያው የመጠበቂያ ግንብ መጽሐፍ ቅዱስና ትራክት ማኅበር የሕይወት ኢንሹራንስ ፖሊሲ ወይም የጡረታ ክፍያ ተጠቃሚ እንዲሆን ስም ሊዛወርለት ይችላል።

የባንክ ሒሳብ፦ የአገሩ ባንክ ደንብ በሚፈቅደው መሠረት የባንክ ሒሳቦች፣ ገንዘብ መቀመጡን የሚገልጽ የምሥክር ወረቀት ወይም የግል ጡረታ ሒሳቦች በአደራ ወይም በሞት ጊዜ የሚከፈል መሆኑ ተገልጾ ለፔንስልቬንያው የመጠበቂያ ግንብ መጽሐፍ ቅዱስና ትራክት ማኅበር ሊሰጥ ይችላል።

አክሲዮኖችና ቦንዶች፦ አክሲዮኖችንና ቦንዶችን በስጦታ መልክ ለፔንስልቬንያው የመጠበቂያ ግንብ መጽሐፍ ቅዱስና ትራክት ማኅበር መስጠት ይቻላል።

የማይንቀሳቀስ ንብረት፦ ሊሸጥ ሊለወጥ የሚችል ቋሚ ንብረት በስጦታ መስጠት ወይም መኖሪያ ቤት በሚሆንበት ጊዜ ደግሞ ባለ ንብረቱ በሕይወት እስካለ ድረስ ተጠቅሞበት ከዚያ በኋላ ማውረስ ይቻላል። አንድ ሰው ማንኛውንም የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤትነት ከማዛወሩ በፊት በአገሩ ከሚገኘው ቅርንጫፍ ቢሮ ጋር መነጋገር ይኖርበታል።

የስጦታ አበል፦ የስጦታ አበል አንድ ሰው ገንዘቡን ወይም የባለቤትነት መብትን የሚያረጋግጡ ሰነዶችን የይሖዋ ምሥክሮችን ወክሎ ለሚሠራው ማኅበር ለማዛወር የሚያደርገውን ዝግጅት ያመለክታል። በምላሹም ለጋሹ ወይም እሱ የወከለው ግለሰብ በሕይወት እስካለበት ጊዜ ድረስ የተወሰነ መጠን ያለው ገንዘብ በየዓመቱ በአበል መልክ ይከፈለዋል። ለጋሹ የስጦታ አበሉን ለማስተላለፍ በተስማማበት ዓመት የገቢ ግብር ቅናሽ ያገኛል።

ኑዛዜዎችና አደራዎች፦ ንብረት ወይም ገንዘብ በሕግ ፊት ተቀባይነት ባለው ኑዛዜ አማካኝነት ለፔንስልቬንያው የመጠበቂያ ግንብ መጽሐፍ ቅዱስና ትራክት ማኅበር በውርስ ሊሰጥ ወይም የፔንስልቬንያው የመጠበቂያ ግንብ መጽሐፍ ቅዱስና ትራክት ማኅበር በአደራ የተሰጠው ንብረት ተጠቃሚ ተደርጎ ስሙ ሊዛወር ይችላል። አንድ ሃይማኖታዊ ድርጅት እንዲጠቀምበት በአደራ የተሰጠ ንብረት በቀረጥ ረገድ የሚያስገኛቸው አንዳንድ ጥቅሞች አሉ።

“በእቅድ የሚደረግ ስጦታ” የሚለው አገላለጽ፣ እነዚህን የመሳሰሉ መዋጮዎች የሚያደርገው ግለሰብ እቅድ ማውጣት እንደሚያስፈልገው ይጠቁማል። የይሖዋ ምሥክሮችን ዓለም አቀፍ ሥራ በእቅድ በሚደረግ ስጦታ ለመደገፍ ለሚፈልጉ ግለሰቦች ጉዳዩን ይበልጥ ግልጽ ለማድረግ ዓለም አቀፉን የመንግሥቱን ስብከት ሥራ ለመደገፍ በእቅድ የሚደረግ ስጦታ የሚል ብሮሹር በእንግሊዝኛና በስፓንኛ ቋንቋ ተዘጋጅቷል። ይህ ብሮሹር የተዘጋጀው ሰዎች ስጦታ ለመስጠት ወይም በሚሞቱበት ጊዜ በኑዛዜ ውርስ ለመተው የሚችሉባቸውን የተለያዩ መንገዶች አስመልክቶ መረጃ ለመስጠት ነው። ብዙዎች ይህን ብሮሹር ካነበቡ በኋላ ከሕግ ወይም ከቀረጥ አማካሪዎቻቸው ጋር በመማከር በዓለም ዙሪያ የምናከናውነውን ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴና ሰብዓዊ እርዳታ ለመደገፍ ከመቻላቸውም በላይ ከቀረጥ ጋር በተያያዘ የተሻለ ጥቅም ለማግኘት ችለዋል። ይህን ብሮሹር ለማግኘት በእቅድ የሚደረግ ስጦታን ጉዳይ የሚከታተለውን ቢሮ በቀጥታ መጠየቅ ይቻላል።

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ከታች ያለውን አድራሻ ወይም ስልክ ቁጥር ተጠቅመህ በእቅድ የሚደረገውን ስጦታ ጉዳይ የሚከታተለውን ቢሮ መጠየቅ ትችላለህ። አሊያም በአገርህ ለሥራው አመራር የሚሰጠውን ቅርንጫፍ ቢሮ ማነጋገር ትችላለህ።

Charitable Planning Office

Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania

100 Watchtower Drive

Patterson, New York 12563-9204

ስልክ፦ (845) 306-0707