በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

“ልታደርገው የምትችለው ከሁሉ የተሻለ ነገር ነው”

“ልታደርገው የምትችለው ከሁሉ የተሻለ ነገር ነው”

“ልታደርገው የምትችለው ከሁሉ የተሻለ ነገር ነው”

አሌክሲስ በሜክሲኮ፣ ሞሬሊያ ከተማ የሚኖር የአምስት ዓመት ልጅ ሲሆን ወላጆቹ መጽሐፍ ቅዱስን የሚያጠኑ ከመሆኑም በላይ የይሖዋ ምሥክሮች በሚያደርጓቸው ስብሰባዎች ላይ ይገኛሉ። ከቤተሰቡ ጋር ሆኖ በአንድ የወረዳ ስብሰባ ላይ በተገኘበት ወቅት ከቤት ወደ ቤት እየሄዱ ስለ መስበክ የሚያሳይ አንድ ሠርቶ ማሳያ ተመለከተ። ከዚያም በድንገት ወደ አባቱ ዞረና “አባዬ አንተም ለምን እየዞርክ አትሰብክም?” በማለት ጠየቀው። አባቱም “እንደዚያ ማድረግ እንድችል መጽሐፍ ቅዱስን እያጠናሁ ነው” ብሎ መለሰለት። አሌክሲስም ደስ ብሎት “አባዬ፣ ይህ ልታደርገው የምትችለው ከሁሉ የተሻለ ነገር ነው” አለው።

ይህ ትንሽ ልጅ ስለ ይሖዋ ያገኘውን እውቀት በሥራ ላይ ማዋል እንዳለበት ተገንዝቦ ነበር። ሁለት የአክስቱ ልጆች አብረውት ስለሚኖሩ አስቀድሞ ወደ ይሖዋ ጸለየና ወላጆቹ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ ከተባለው መጽሐፍ ያስጠኑትን ታሪክ ይነግራቸው ጀመር። አሌክሲስ ገና ማንበብ ባይችልም ስዕሎቹን በማየት ብቻ የመጽሐፉን ሐሳብ በሚገባ ያውቀዋል። ስለ አምላክ ዓላማ የተማረውን ለሰዎች በየቤታቸው እየሄደ የመናገር ፍላጎት እንዳለውም ተናግሯል።

አዎን፣ ወጣቶችም ሆኑ አረጋውያን ‘ቅዱሱ’ ይሖዋ ከሚፈልግባቸው ብቃት ጋር ተስማምተው መኖር የሚችሉ ከመሆኑም በላይ በአሕዛብ መካከል ስለ እርሱ የመናገር ከምንም ነገር የሚበልጥ ትልቅ መብት አላቸው። (ኢሳይያስ 43:3፤ ማቴዎስ 21:16) በእርግጥም ይህ አንድ ሰው ሊያደርገው ከሚችለው ከማንኛውም ነገር የላቀ ሥራ እንደሆነ አያጠራጥርም።