ኢሳይያስ 43:1-28

  • ይሖዋ ሕዝቡን መልሶ ሰበሰበ (1-7)

  • አማልክት የገጠማቸው ግድድር (8-13)

    • “እናንተ ምሥክሮቼ ናችሁ” (10, 12)

  • ከባቢሎን ነፃ መውጣት (14-21)

  • “ጉዳያችንን አቅርበን እንሟገት” (22-28)

43  አሁን ግን፣ ያዕቆብ ሆይ ፈጣሪህ፣እስራኤልም ሆይ የሠራህ ይሖዋ+ እንዲህ ይላል፦ “እኔ ተቤዥቼሃለሁና+ አትፍራ። በስምህ ጠርቼሃለሁ። አንተ የእኔ ነህ።   በውኃዎች መካከል ስታልፍ እኔ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤+በወንዞችም መካከል ስትሻገር አያሰምጡህም።+ በእሳት መካከል ስትሄድ አትቃጠልም፤ነበልባሉም አይፈጅህም።   እኔ ይሖዋ አምላክህ፣የእስራኤል ቅዱስ፣ አዳኝህ ነኝና። ግብፅን ለአንተ ቤዛ አድርጌ ሰጥቻለሁ፤ኢትዮጵያንና ሴባን በአንተ ምትክ ሰጥቻለሁ።   አንተ በዓይኔ ፊት ውድ ሆነሃልና፤+የተከበርክም ነህ፤ እኔም ወድጄሃለሁ።+ ስለዚህ በአንተ ምትክ ሰዎችን፣በሕይወትህም* ምትክ ብሔራትን እሰጣለሁ።   እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ።+ ዘርህን ከምሥራቅ አመጣለሁ፤ከምዕራብም እሰበስብሃለሁ።+   ሰሜንን ‘ልቀቃቸው!’ እለዋለሁ፤+ ደቡብንም እንዲህ እለዋለሁ፦ ‘አታግታቸው። ወንዶች ልጆቼን ከሩቅ፣ ሴቶች ልጆቼንም ከምድር ዳርቻ አምጣ፤+   በስሜ የተጠራውን፣+ለክብሬም የፈጠርኩትን፣የሠራሁትንና ያበጀሁትን ሁሉ አምጣ።’+   ዓይን ቢኖራቸውም ዕውር የሆኑትን፣ጆሮ ቢኖራቸውም ደንቆሮ የሆኑትን ሰዎች አውጣ።+   ብሔራት ሁሉ አንድ ቦታ ይሰብሰቡ፤ሕዝቦችም በአንድነት ይሰብሰቡ።+ ከመካከላቸው ይህን ሊናገር የሚችል ማን አለ? ወይስ የመጀመሪያዎቹን ነገሮች ሊነግሩን ይችላሉ?*+ ትክክል መሆናቸውን እንዲያረጋግጡ ምሥክሮቻቸውን ያቅርቡ፤ወይም ሰምተው ‘ይህ እውነት ነው!’ ይበሉ።”+ 10  “እናንተ ምሥክሮቼ ናችሁ”+ ይላል ይሖዋ፤“አዎ፣ የመረጥኩት አገልጋዬ ናችሁ፤+ይህም ታውቁና ታምኑብኝ ዘንድ*ደግሞም እኔ ምንጊዜም ያው እንደሆንኩ ታስተውሉ ዘንድ ነው።+ ከእኔ በፊት አምላክ አልተሠራም፤ከእኔም በኋላ የለም።+ 11  እኔ፣ አዎ እኔ ይሖዋ ነኝ፤+ ከእኔ በቀር አዳኝ የለም።”+ 12  “በመካከላችሁ ባዕድ አምላክ ባልነበረበት ጊዜየተናገርኩት፣ ያዳንኩትና ያሳወቅኩት እኔ ነኝ።+ ስለዚህ እናንተ ምሥክሮቼ ናችሁ” ይላል ይሖዋ፤ “እኔም አምላክ ነኝ።+ 13  ደግሞም እኔ ምንጊዜም ያው ነኝ፤+ከእጄም አንዳች ነገር ሊነጥቅ የሚችል የለም።+ እርምጃ በምወስድበት ጊዜ ሊያግድ የሚችል ማን ነው?”+ 14  እናንተን የሚቤዠው+ የእስራኤል ቅዱስ ይሖዋ+ እንዲህ ይላል፦ “ለእናንተ ስል ወደ ባቢሎን እሰዳለሁ፤ የበሮቹንም መቀርቀርያዎች ሁሉ እጥላለሁ፤+በመርከቦቻቸው ላይ ያሉት ከለዳውያንም በጭንቀት ይጮኻሉ።+ 15  እኔ ይሖዋ የእናንተ ቅዱስ፣+ የእስራኤል ፈጣሪ፣+ ንጉሣችሁ ነኝ።”+ 16  ይሖዋ ይኸውምበባሕር መካከል መንገድ የሚያበጀው፣በሚናወጡ ውኃዎችም መካከል ጎዳና የሚዘረጋው፣+ 17  የጦር ሠረገላውንና ፈረሱን፣+ሠራዊቱንና ኃያላን ተዋጊዎቹን በአንድነት የሚያወጣው አምላክ እንዲህ ይላል፦ “ይተኛሉ፤ አይነሱምም።+ እንደሚነድ የጧፍ ክር ተዳፍነው ይጠፋሉ።” 18  “የቀድሞዎቹን ነገሮች አታስታውሱ፤ያለፈውንም ነገር አታውጠንጥኑ። 19  እነሆ፣ አዲስ ነገር አደርጋለሁ፤+አሁንም እንኳ መከናወን ጀምሯል። ይህን አታስተውሉም? በምድረ በዳ መንገድ አዘጋጃለሁ፤+በበረሃም ወንዞችን አፈልቃለሁ።+ 20  የዱር አውሬ፣ ቀበሮዎችናሰጎኖች ያከብሩኛል፤በምድረ በዳ ውኃ፣በበረሃም ወንዞችን እሰጣለሁና፤+ይህን የማደርገው የመረጥኩት ሕዝቤ+ እንዲጠጣ፣ 21  ለራሴ የሠራሁትም ሕዝብ እንዲጎነጭ ነው፤ሕዝቤ ውዳሴዬን እንዲያውጅ ይህን አደርጋለሁ።+ 22  እስራኤል ሆይ፣ አንተ ግን የእኔ ነገር ስለታከተህ፣+ያዕቆብ ሆይ፣ አልጠራኸኝም።+ 23  ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባ ለማቅረብ በግ አላመጣህልኝም፤ወይም መሥዋዕቶች በማቅረብ አላከበርከኝም። ስጦታ እንድታመጣልኝ አላስገደድኩህም፤ነጭ ዕጣን አቅርብልኝ ብዬም አላሰለቸሁህም።+ 24  በገንዘብህ ጠጅ ሣር* አልገዛህልኝም፤በመሥዋዕቶችህም ስብ አላጠገብከኝም።+ ከዚህ ይልቅ ኃጢአትህን አሸክመኸኛል፤በምትፈጽማቸውም በደሎች አሰልችተኸኛል።+ 25  ስለ ራሴ ስል+ በደልህን* እኔ ራሴ እደመስሰዋለሁ፤+ኃጢአትህንም አላስታውስም።+ 26  እስቲ አስታውሰኝ፤ ጉዳያችንን አቅርበን እንሟገት፤ትክክለኛ መሆንህን ለማረጋገጥ በበኩልህ ጉዳይህን ተናገር። 27  የመጀመሪያው አባትህ ኃጢአት ሠርቷል፤የገዛ ቃል አቀባዮችህም* በእኔ ላይ ዓምፀዋል።+ 28  ስለዚህ በቅዱሱ ስፍራ የሚገኙትን መኳንንት አረክሳለሁ፤ያዕቆብንም ለጥፋት አሳልፌ እሰጠዋለሁ፤እስራኤልንም ለስድብ እዳርገዋለሁ።+

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “በነፍስህም።”
ወደፊት የሚመጡትን የመጀመሪያዎቹን ነገሮች የሚያመለክት ሊሆን ይችላል።
ወይም “ትታመኑብኝ ዘንድ።”
እዚህ ላይ የተጠቀሰው የዕብራይስጥ ቃል ጥሩ መዓዛ ያለውን ተክል ያመለክታል። ሆኖም የተክሉ ምንነት በእርግጠኝነት አይታወቅም።
ወይም “የዓመፅ ድርጊትህን።”
የሕጉን አስተማሪዎች የሚያመለክት ሊሆን ይችላል።