በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ታስታውሳለህ?

ታስታውሳለህ?

ታስታውሳለህ?

በቅርቡ የወጡትን የመጠበቂያ ግንብ እትሞች አንብበሃል? እስቲ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር:-

• የኮምፕሉቴንስ መጽሐፍ ቅዱስ ምንድን ነው? ትልቅ ቦታ የተሰጠውስ ለምንድን ነው?

በጊዜው የነበሩትን በዕብራይስጥ፣ በግሪክና በላቲን የተዘጋጁ ቅዱሳን ጽሑፎችና በአረማይክ የተዘጋጁ የተወሰኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችን ጎን ለጎን በተለያዩ አምዶች ላይ አጣምሮ የያዘ የመጽሐፍ ቅዱስ እትም ነው። ይህ መጽሐፍ ቅዱስ ቅዱሳን ጽሑፎች በመጀመሪያ በተጻፉባቸው ቋንቋዎች ከበፊቱ የተሻለ ትርጉም በማዘጋጀት ረገድ ትልቅ እመርታ የታየበት ነበር።—4/15, ገጽ 28-31

• ሰዎች አምላክን ማስደሰት የሚችሉት እንዴት ነው?

ይሖዋ ሕያው አካል ያለው አምላክ እንደመሆኑ ማሰብና የተለያዩ ድርጊቶችን ማከናወን የሚችል ከመሆኑም በላይ ስሜቶችም አሉት። ይሖዋ “ደስተኛ አምላክ” ሲሆን ዓላማውን ከግብ በማድረስ ይደሰታል። (1 ጢሞቴዎስ 1:11 NW፤ መዝሙር 104:31) የአምላክን አስተሳሰብ ይበልጥ ባወቅን መጠን እርሱን ለማስደሰት ምን ማድረግ እንደምንችል እየተገነዘብን እንሄዳለን።—5/15, ገጽ 4-7

• ዳዊት ሚስቱ ሜልኮል ተራፊም ወይም ጣዖት እንዲኖራት የፈቀደው ለምን ነበር?

ንጉሥ ሳኦል ዳዊትን ለመግደል ሲያስብ ሜልኮል በአልጋ ላይ አንድ ምስል (የሰው ቅርጽ ያለው ሳይሆን አይቀርም) በማስተኛት ዳዊትን እንዲያመልጥ ረዳችው። ሜልኮል የተራፊም ምስል የነበራት ልብዋ ሙሉ በሙሉ ከይሖዋ ጋር ስላልሆነ ሊሆን ይችላል። ዳዊት ግን ስለ ተራፊሙ የሚያውቀው ነገር ላይኖር ይችላል፤ ወይም ሜልኮል የንጉሥ ሳኦል ልጅ ስለነበረች አልከለከላትም ይሆናል። (1 ዜና መዋዕል 16:25, 26)—6/1, ገጽ 29

• አምላክ ደምን በሚመለከት የሰጣቸው ሕጎች በየትኛው መሠረታዊ እውነታ ላይ እንድናተኩር ያደርጉናል?

አምላክ ከጥፋት ውኃ በኋላ በተናገረው ሐሳብ፣ በሙሴ ሕግ እንዲሁም በሐዋርያት ሥራ 15:28, 29 ላይ ደምን በሚመለከት የሰጠው መመሪያ በፈሰሰው የኢየሱስ ደም አማካኝነት ስለተከፈለው መሥዋዕት እንድናስብ ያደርገናል። ለኃጢአታችን ይቅርታ ማግኘትና ከአምላክ ጋር ሰላማዊ ግንኙነት መመሥረት የምንችለው በዚህ ደም አማካኝነት ብቻ ነው። (ቆላስይስ 1:20)—6/15, ገጽ 14-19

• ኢየሱስ ከፈጸማቸው ተአምራት ውስጥ ምን ያህሉ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተጠቅሰዋል?

በወንጌል ዘገባዎች ውስጥ 35 የሚሆኑ የኢየሱስ ተአምራት ተጠቅሰዋል። በጽሑፍ ያልሰፈሩትን ጨምሮ በጠቅላላው ምን ያህል ተአምራት እንደፈጸመ ግን አልተገለጸም። (ማቴዎስ 14:14)—7/15, ገጽ 5