በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

“የአምላክ ቃል ምንኛ ኃያል ነው!”

“የአምላክ ቃል ምንኛ ኃያል ነው!”

“የአምላክ ቃል ምንኛ ኃያል ነው!”

‘የእግዚአብሔር ቃል ሕያውና የሚሠራ ነው።’ (ዕብራውያን 4:​12) የ2003 የይሖዋ ምሥክሮች የቀን መቁጠሪያ የአምላክ ቃል ከፍተኛ ኃይል እንዳለው የሚያረጋግጡ ከዓለም ዙሪያ የተገኙ ስድስት እውነተኛ የሕይወት ታሪኮችን ይዟል። የቀን መቁጠሪያው “በፊትና አሁን” በሚል ርዕስ ሥር የይሖዋ ምሥክሮች የሚያከናውኑት የማስተማር ሥራ ሰዎች ሥነ ምግባራቸውን እንዲያሻሽሉ፣ ጎጂ አኗኗርን እንዲተዉ፣ የቤተሰብ ሕይወታቸውን እንዲያጠናክሩና ከአምላክ ጋር የግል ዝምድና እንዲመሠርቱ እንዴት እንደረዳቸው ገልጿል።

የ2003ን የቀን መቁጠሪያ በሚመለከት ብዙ የአድናቆት መግለጫ ደብዳቤዎች ደርሰውናል። ከተሰጡት አስተያየቶች ውስጥ ጥቂቶቹን እነሆ:-

“እውነተኛ ክርስቲያኖች ይህን የቀን መቁጠሪያ ሲመለከቱ ልክ እንደ እነርሱ ለእምነታቸው ብርቱ ተጋድሎ ማድረግ ያስፈለጋቸው ሌሎችም እንዳሉ ይገነዘባሉ። አንዳንዶች ፎቶግራፎቹን በማየት በራሳቸው ሕይወት ያደረጓቸውን ለውጦች ማስታወስ ይችላሉ።”​—⁠ስቴቨን፣ ዩናይትድ ስቴትስ

“ይህንን አጭር ማስታወሻ የጻፍኩላችሁ የ2003 የቀን መቁጠሪያ ምን ያህል ልቤን እንደነካው ልገልጽላችሁ ስለፈለግሁ ነው። የቀን መቁጠሪያ የአሁኑን ያህል ነክቶኝ አያውቅም። መጽሐፍ ቅዱስ በግለሰቦች ሕይወት ላይ ከፍተኛ የሆነ በጎ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር ለሰዎች ለማሳየት እነዚህን ሕያውና አስደናቂ የሕይወት ታሪኮች የያዘውን የቀን መቁጠሪያ በአገልግሎት ቦርሳዬ ውስጥ እይዘዋለሁ።”​—⁠ማርክ፣ ቤልጅየም

“ልቤ በቀን መቁጠሪያው በጣም ነው የተነካው። ይሖዋ እነዚህን ግለሰቦች እንዴት እንደለወጣቸው ስመለከት ሲቃ ተናነቀኝ። በዚህም ምክንያት የራሴን ሕይወት ለመለወጥ በማደርገው ጥረት ለመግፋት ቆርጫለሁ። አሁን ከምንጊዜውም ይበልጥ የዓለም አቀፋዊው የወንድማማች ማኅበር አካል እንደሆንኩ ይሰማኛል።”​—⁠ሜሪ፣ ዩናይትድ ስቴትስ

“ኢየሱስ በሕዝቡ መንፈሳዊ ጉስቁልና ስሜቱ በጥልቅ ተነክቶ ነበር። የኢየሱስን ምሳሌ በመከተል በ2003 የቀን መቁጠሪያ ላይ እንደዚህ ያሉ የሕይወት ታሪኮች ስላቀረባችሁልን አመሰግናችኋለሁ። በሕይወቴ የቀን መቁጠሪያ ተመልክቼ እንደዚህ አልቅሼ አላውቅም።”​—⁠ካሳንድራ፣ ዩናይትድ ስቴትስ

“ማጨስ የጀመርኩት በ11 ዓመቴ ሲሆን ቆየት ብሎ ደግሞ አደገኛ ዕፆችን መውሰድ ጀመርኩ። ብዙ ጊዜ ሕይወቴን ለማጥፋት አስብ ነበር። ይሖዋን ሳውቅ እነዚህን ልማዶች ለመተው የሚያስችል እርዳታ አገኘሁ። ይህ የቀን መቁጠሪያ ለእኔ በጣም ጠቃሚ ነው። በዓለም ዙሪያ ያሉ ወንድሞቼና እህቶቼ የሚያሳዩት ምሳሌነት አጠንክሮኛል። አሁን በዚህ ትግል ብቻዬን እንዳልሆንኩና ከሁሉ ይበልጥ አስፈላጊው ነገር ይሖዋን መውደድና እርሱን በሙሉ ልብ ማገልገል መሆኑን ተረድቻለሁ።”​—⁠ማርጋሬት፣ ፖላንድ

“የአምላክ ቃል ምንኛ ኃያል ነው! የ2003 የቀን መቁጠሪያ ሲደርሰኝ እንባ ተናነቀኝ። ተሞክሮዎቹና ፎቶግራፎቹ እምነት የሚያጠነክሩ ናቸው።”​—⁠ዳርሊን፣ ዩናይትድ ስቴትስ

“ከእነዚህ ሰዎች ውስጥ የአንዳንዶቹ የቀድሞ አኗኗር ከድሮ ሕይወቴ ጋር በጣም ይመሳሰላል። ሊወገዱ የማይችሉ የሚመስሉ መጥፎ ልማዶችን ለመተው ይሖዋ ኃይል ሰጥቶኛል። እነዚህን የሕይወት ታሪኮች ስላቀረባችሁልን በጣም አመሰግናችኋለሁ።”​—⁠ዊልያም፣ ዩናይትድ ስቴትስ