በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ኪሳራውን ታሰላለህን?

ኪሳራውን ታሰላለህን?

ኪሳራውን ታሰላለህን?

ኢየሱስ ክርስቶስ ለደቀ መዛሙርቱ የዘላለም ሕይወትን ተስፋ ዘርግቶላቸዋል፤ ሆኖም ክርስቲያን መሆን የሚጠይቀውን ዋጋ እንዲያሰሉም አጥብቆ አሳስቧቸዋል። ነጥቡን በምሳሌ ለማስረዳት እንዲህ ሲል ጠይቋል:- “ከእናንተ ግንብ ሊሠራ የሚወድ ለመደምደሚያ የሚበቃ ያለው እንደ ሆነ አስቀድሞ ተቀምጦ [ኪ]ሳራውን የማይቈጥር ማን ነው?” (ሉቃስ 14:28) ኢየሱስ ኪሳራ ሲል ምን ማለቱ ነበር?

ሁሉም ክርስቲያኖች ፈተናዎች ያጋጥሟቸዋል፤ አንዳንዴም ፈተናው ከበድ ያለ ሊሆን ይችላል። (መዝሙር 34:19፤ ማቴዎስ 10:36) በመሆኑም ተቃውሞ ወይም ሌሎች ችግሮች ሲያጋጥሙን እንዳንደናገጥ በአእምሮም ሆነ በመንፈስ የተዘጋጀን መሆን ይገባናል። የክርስቶስ ደቀ መዝሙር መሆናችን እንደዚህ ዓይነት ፈተናዎችን እንደሚያስከትል ሆኖም የምናገኘው ከኃጢአትና ከሞት ነጻ የመሆን ሽልማት ይህ ሥርዓት ሊሰጠን ከሚችለው ከማንኛውም ነገር የላቀ መሆኑን በመገንዘብ ኪሳራውን አስቀድመን አስልተን መሆን አለበት። አዎን፣ አምላክን ማገልገላችንን እስከቀጠልን ድረስ እርሱ እንዲደርስብን የሚፈቅደው ማንኛውም ፈተና፣ ሞትም እንኳን ቢሆን ዘላቂ የሆነ ጉዳት ሊያስከትል አይችልም።​—⁠2 ቆሮንቶስ 4:16-18፤ ፊልጵስዩስ 3:8, 9

እምነታችን የዚህን ያህል ሊጠነክር የሚችለው እንዴት ነው? በተለይ ተቃራኒውን እንድናደርግ ግፊት ቢደርስብንም ትክክለኛ ውሳኔ ስናደርግ፣ ለክርስትና መሠረታዊ ሥርዓቶች ጠንካራ አቋም ስንወስድ ወይም አንድን ድርጊት ከአምላክ ፈቃድ ጋር በሚስማማ መንገድ ስናከናውን እምነታችን ይጠነክራል። በታማኝነት በወሰድነው አቋም ምክንያት የይሖዋን በረከት በግላችን ስንቀምስ እምነታችን እየጠነከረና ጥልቅ እየሆነ ይሄዳል። በዚህ መንገድ የኢየሱስን፣ የመጀመሪያ ደቀ መዛሙርቱንና ባለፉት ዘመናት ሁሉ አምላክን ማገልገል የሚጠይቀውን ዋጋ በትክክል ያሰሉት የታመኑ ወንዶችና ሴቶች የተዉልንን ምሳሌ እንከተላለን።​—⁠ማርቆስ 1:16-20፤ ዕብራውያን 11:4, 7, 17, 24, 25, 32-38