በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

አዲስ ዓለም ያስፈልገናል!

አዲስ ዓለም ያስፈልገናል!

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ የሆኑት አንቶኒዮ ጉቴሬዝ “ዓለማችን ከፍተኛ ቀውስ ውስጥ ናት” ብለዋል። ይህ አባባል እውነት እንደሆነ ይሰማሃል?

በዜና የምናየውና የምንሰማው ነገር በአብዛኛው አስጨናቂ ነው፤ የሚከተሉትን ነገሮች እንደ ምሳሌ ማንሳት ይቻላል፦

  • በሽታና ወረርሽኝ

  • የተፈጥሮ አደጋዎች

  • ድህነትና ረሃብ

  • የአካባቢ ብክለትና የምድር ሙቀት መጨመር

  • ወንጀል፣ ዓመፅና ሙስና

  • ጦርነት

አዲስ ዓለም እንደሚያስፈልገን ግልጽ ነው። መጪው አዲስ ዓለም ውስጥ እንደሚከተሉት ያሉ ነገሮች ቢኖሩ ደስ ይለናል፦

  • የተሟላ ጤንነት

  • ከስጋት ነፃ የሆነ ሕይወት

  • የተትረፈረፈ ምግብ

  • ከብክለት የጸዳ አካባቢ

  • ፍትሕ ለሁሉም ሰው

  • ዓለም አቀፍ ሰላም

ሆኖም አዲስ ዓለም ይመጣል ስንል ምን ማለታችን ነው?

አሁን የምንኖርበት ዓለም ምን ይሆናል?

በመጪው አዲስ ዓለም ውስጥ ለመኖር ምን ማድረግ ይኖርብናል?

ለእነዚህና ተዛማጅ ለሆኑ ሌሎች ጥያቄዎች መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠውን የሚያጽናና መልስ በዚህ መጽሔት ላይ ማንበብ ትችላለህ።