በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የጥላቻን ሰንሰለት መበጠስ የሚቻለው እንዴት ነው?

1 | አታዳላ

1 | አታዳላ

የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት፦

“አምላክ እንደማያዳላ በእርግጥ አስተዋልኩ፤ ከዚህ ይልቅ ከየትኛውም ብሔር ቢሆን እሱን የሚፈራና ትክክል የሆነውን ነገር የሚያደርግ ሰው በእሱ ዘንድ ተቀባይነት አለው።”የሐዋርያት ሥራ 10:34, 35

ምን ማለት ነው?

ይሖዋ * አምላክ በዜግነታችን፣ በዘራችን፣ በቆዳ ቀለማችን ወይም በባሕላችን አይገምተንም። ከዚህ ይልቅ የሚያተኩረው በውስጣዊ ማንነታችን ላይ ነው። በእርግጥም “ሰው የሚያየው ውጫዊ ገጽታን ነው፤ ይሖዋ ግን የሚያየው ልብን ነው።”—1 ሳሙኤል 16:7

ምን ማድረግ ትችላለህ?

የሰዎችን ልብ ማንበብ ባንችልም አምላክን በመምሰል ሌሎችን ከአድልዎ ነፃ በሆነ መንገድ ለማየት ጥረት ማድረግ እንችላለን። ሰዎችን በቡድን ደረጃ ሳይሆን በግለሰብ ደረጃ ለማየት ሞክር። ለሌሎች፣ ምናልባትም ሌላ ዘር ወይም ዜግነት ላላቸው ሰዎች አሉታዊ ስሜት እንዳለህ ካስተዋልክ ወደ አምላክ ጸልይ፤ እንዲህ ያለውን ስሜት ከልብህ ነቅለህ ለማውጣት እንዲረዳህ ጠይቀው። (መዝሙር 139:23, 24) አድልዎ ላለማድረግ እንዲረዳህ ይሖዋን ከልብህ ከጠየቅከው፣ ጸሎትህን ሰምቶ እንደሚረዳህ መተማመን ትችላለህ።—1 ጴጥሮስ 3:12

^ አን.6 ይሖዋ የአምላክ የግል ስም ነው።—መዝሙር 83:18

“ከነጮች ጋር . . . በሰላም ጎን ለጎን ተቀምጬ አላውቅም። አሁን ግን የእውነተኛው የዓለም አቀፍ የወንድማማች ማኅበር አባል ሆኛለሁ።”—ታይተስ