የይሖዋ ምሥክሮች ከቤት ወደ ቤት የሚሄዱት ለምንድን ነው?
ኢየሱስ ‘ከሁሉም ብሔራት ሰዎችን ደቀ መዛሙርት እንዲያደርጉ’ ለተከታዮቹ ነግሯቸው ነበር። (ማቴዎስ 28:19, 20) ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ለስብከት ሲልካቸው ሰዎችን በየቤታቸው እየሄዱ እንዲያናግሩ መመሪያ ሰጥቷቸው ነበር። (ማቴዎስ 10:7, 11-13) ኢየሱስ ከሞተ በኋላም በመጀመሪያው መቶ ዘመን ይኖሩ የነበሩት ክርስቲያኖች “በአደባባይና ከቤት ወደ ቤት” በመሄድ መልእክታቸውን ማሰራጨታቸውን ቀጥለው ነበር። (የሐዋርያት ሥራ 5:42፤ 20:20) እኛም የጥንቶቹን ክርስቲያኖች አርዓያ እንከተላለን፤ ደግሞም ከቤት ወደ ቤት ማገልገል ሰዎችን ለማግኘት የተሻለ መንገድ እንደሆነ ይሰማናል።