በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

የይሖዋ ምሥክሮች የራሳቸው ሃይማኖት ያላቸውን ሰዎች የሚያናግሩት ለምንድን ነው?

የይሖዋ ምሥክሮች የራሳቸው ሃይማኖት ያላቸውን ሰዎች የሚያናግሩት ለምንድን ነው?

 የራሳቸው ሃይማኖት ያላቸው ብዙ ሰዎች ስለ መጽሐፍ ቅዱስ መወያየት እንደሚያስደስታቸው ከተሞክሮ አይተናል። እርግጥ ነው፣ አንድ ሰው ከእኛ የተለየ እምነት ሊኖረው እንደሚችል እናውቃለን፤ ይህን መብቱንም እናከብራለን፤ በተጨማሪም ሌሎች መልእክታችንን እንዲቀበሉ አንጫንም።

 ስለ ሃይማኖት ከሰዎች ጋር በምንወያይበት ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስ “በገርነት መንፈስና በጥልቅ አክብሮት” መነጋገር እንዳለብን የሚሰጠውን ምክር ተግባራዊ ለማድረግ እንጥራለን። (1 ጴጥሮስ 3:15) አንዳንዶች መልእክታችንን እንደማይቀበሉ እንጠብቃለን። (ማቴዎስ 10:14) ይሁንና ካላናገርናቸው በስተቀር ሰዎች ምን ምላሽ ሊሰጡ እንደሚችሉ አስቀድመን ማወቅ አንችልም። በሌላ በኩል ደግሞ የሰዎች ሁኔታ ሊለወጥ እንደሚችል እንገነዘባለን።

 ለምሳሌ አንድ ሰው በሥራ በጣም ከመወጠሩ የተነሳ እኛን ለማነጋገር ፈቃደኛ ላይሆን ይችላል፤ ይኸው ሰው ግን በሌላ ጊዜ ደስ ብሎት ከእኛ ጋር ሊነጋገር ይችላል። በሌላ በኩል ደግሞ ሰዎች ከዚህ በፊት ደርሶባቸው የማያውቅ ችግር ወይም ፈተና መጋፈጥ ሊኖርባቸው ይችል ይሆናል፤ በዚህም የተነሳ ለመጽሐፍ ቅዱስ መልእክት ጆሯቸውን ሊሰጡ ይችላሉ። ሰዎችን በተደጋጋሚ ለማናገር ጥረት የምናደርገው ለዚህ ነው።