በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

አምላክ፣ የራሱ ማንነት የሌለው ኃይል ነው?

አምላክ፣ የራሱ ማንነት የሌለው ኃይል ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

 አምላክ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ከዋክብትን የፈጠረው እንዴት እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ሲገልጽ እንዲህ ይላል፦ “ዐይናችሁን አንሡ፤ ወደ ሰማይ ተመልከቱ፤ እነዚህን ሁሉ የፈጠረ ማን ነው? የከዋክብትን ሰራዊት አንድ በአንድ የሚያወጣቸው፣ በየስማቸው የሚጠራቸው እርሱ [አምላክ] ነው። ከኀይሉ ታላቅነትና ከችሎታው ብርታት የተነሣ፣ አንዳቸውም አይጠፉም።” (ኢሳይያስ 40:25, 26) አምላክ ተወዳዳሪ የሌለው ኃይሉን በአጽናፈ ዓለም ውስጥ ይጠቀምበታል።

 ይሁን እንጂ አምላክን የራሱ ማንነት የሌለው ኃይል እንደሆነ አድርገን ማሰብ የለብንም። መጽሐፍ ቅዱስ፣ አምላክ ስሜት እንዳለው ይናገራል፤ ለምሳሌ ያህል፣ የፍቅር እና የጥላቻ ስሜት አለው። (መዝሙር 11:5፤ ዮሐንስ 3:16) እንዲሁም ሰዎች የሚያደርጉት ነገር ስሜቱን ሊጎዳው እንደሚችል መጽሐፍ ቅዱስ ይገልጻል።—መዝሙር 78:40, 41