በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 88

መንገድህን አሳውቀኝ

መንገድህን አሳውቀኝ

(መዝሙር 25:4)

  1. 1. ይሖዋ በፊትህ ተሰብስበናል፤

    ግብዣህንም ተቀብለናል።

    ቃልህ ብርሃን ነው፤ መንገድ ያሳየናል።

    ያንተን ትም’ርት ይገልጽልናል።

    (አዝማች)

    አምላኬ ሆይ፣ ልወቅ መንገድህን፤

    አስተምረኝ የጽድቅ ሕጎችህን።

    በ’ውነተኛው ጎዳና ላይ ምራኝ፤

    ት’ዛዛትህ ደስታ ያስገኙልኝ።

  2. 2. አምላካችን ሆይ፣ ጥበብህ ጥልቅ ነው፤

    ሥርዓትህ የሚያረጋጋ ነው።

    በድንቅ ነገሮች ተሞልቷል ያንተ ቃል፤

    ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።

    (አዝማች)

    አምላኬ ሆይ፣ ልወቅ መንገድህን፤

    አስተምረኝ የጽድቅ ሕጎችህን።

    በ’ውነተኛው ጎዳና ላይ ምራኝ፤

    ት’ዛዛትህ ደስታ ያስገኙልኝ።

(በተጨማሪም ዘፀ. 33:13⁠ን፣ መዝ. 1:2⁠ን እና 119:27, 35, 73, 105⁠ን ተመልከት።)