በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 14

አዲሱን የምድር ንጉሥ አወድሱ

አዲሱን የምድር ንጉሥ አወድሱ

(መዝሙር 2:12)

  1. 1. ከብሔራት የተውጣጡ

    እጅግ ብዙ ሕዝቦችን፣

    በመሰብሰብ ላይ ናቸው

    ክርስቶስና ቅቡዓን።

    የአምላክ መንግሥት ተወልዷል፤

    በቅርቡ ምድርን ይገዛል።

    ይህ ተስፋ ነው ታላቅ ስጦታ፤

    ያስገኛል መጽናኛ ደስታ።

    (አዝማች)

    ይወደስ ይሖዋ፤ ይወደስ ኢየሱስ፤

    አመስግኑት አዲሱን ንጉሥ።

    በደስታ ’ንገዛለት፤

    ውዳሴ ’ናቅርብለት ባንድነት።

  2. 2. ክርስቶስ በመግዛት ላይ ነው፤

    እንግለጽ ደስታችንን።

    በቅርቡ ለፍርድ ይመጣል፤

    ያድነናል ይህ መስፍን።

    ይታየናል ተስፋው ካሁን፣

    ሽብር ሲጠፋ ከምድር፣

    ሙታን ሲወጡ ከመቃብር፣

    ሐሴት ያደርጋል የሰው ዘር!

    (አዝማች)

    ይወደስ ይሖዋ፤ ይወደስ ኢየሱስ፤

    አመስግኑት አዲሱን ንጉሥ።

    በደስታ ’ንገዛለት፤

    ውዳሴ ’ናቅርብለት ባንድነት።

(በተጨማሪም መዝ. 2:6⁠፤ 45:1⁠ን፣ ኢሳ. 9:6⁠ን እና ዮሐ. 6:40⁠ን ተመልከት።)