መጠበቂያ ግንብ የካቲት 2015 | ከሥራህ ደስታ ማግኘት የምትችለው እንዴት ነው?

ብዙ ሰዎች ጠንክሮ መሥራት ደስታ እና እርካታ እንደሚያስገኝ ይሰማቸዋል። እነዚህ ሰዎች ጠንክሮ ስለ መሥራት እንዲህ ያለ አዎንታዊ አመለካከት እንዲኖራቸው የረዳቸው ምንድን ነው?

የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ

ጠንክሮ መሥራት ጊዜ ያለፈበት ነገር ነው?

አንዳንድ ሰዎች ጠንክረው መሥራት እንደማያስፈልጋቸው ይሰማቸዋል። ሆኖም በርትቶ መሥራት የሚያስደስታቸው ሌሎች ብዙ ሰዎችም አሉ። እነዚህ ሰዎች ከሥራቸው ደስታ ማግኘት እንዲችሉ የረዳቸው ምንድን ነው?

የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ

ከሥራ ደስታ ማግኘት የሚቻለው እንዴት ነው?

ከሥራ ደስታ እና እርካታ ማግኘት ስለሚቻልበት መንገድ መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠውን ምክር ተመልከት።

መጽሐፍ ቅዱሳዊ ውይይት

መጽሐፍ ቅዱስን መመርመር ለምን አስፈለገ?

መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈው ከረጅም ጊዜ በፊት ቢሆንም ለዘመናችን ጠቃሚ ነው። የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያዎች በሕይወትህ ሊጠቅሙህ የሚችሉት እንዴት ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ የሰዎችን ሕይወት ይለውጣል

መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠው ግልጽና አሳማኝ መልስ አስደነቀኝ

ኧርነስት ሎዲ ከሕይወት ጋር በተያያዘ ለነበሩት አንዳንድ ጥያቄዎች መልስ አግኝቷል። ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ያገኘው ግልጽ መልስ ስለ ወደፊቱ ጊዜ እውነተኛ ተስፋ እንዲኖረው ረድቶታል።

በእምነታቸው ምሰሏቸው

“ሕልምን የሚፈታው አምላክ አይደለም?”

ዮሴፍ የግብፅን የመጠጥ አሳላፊዎች አለቃ፣ የዳቦ ጋጋሪዎቹን አለቃና የፈርዖንን ሕልሞች እንዲፈታ ያስቻለው ምንድን ነው? እስረኛ የነበረው ዮሴፍ በአንድ ጀምበር ከፍተኛ ባለሥልጣን መሆን የቻለው እንዴት ነበር?

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

ዓለም በአንድ መንግሥት ቢተዳደር ኖሮ በምድር ላይ ምን ያህል ሰላምና ደኅንነት ይሰፍን እንደነበር ለማሰብ ሞክር። አምላክ እንዲህ ዓይነት መንግሥት እንደሚያመጣ እርግጠኞች የምንሆነው ለምንድን ነው? የዚህ መንግሥት ገዢ የሚሆነውስ ማን ነው?

በተጨማሪም . . .

መጽሐፍ ቅዱስ ሰብዓዊ ጥበብ የሚንጸባረቅበት መጽሐፍ ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ራሱ የሚሰጠውን ምሥክርነት ልብ በል።