በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

መጽሐፍ ቅዱስ ሰብዓዊ ጥበብ የሚንጸባረቅበት መጽሐፍ ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ ሰብዓዊ ጥበብ የሚንጸባረቅበት መጽሐፍ ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

 መጽሐፍ ቅዱስ፣ ቅዱሳን መጻሕፍት በመባልም የሚታወቅ ሲሆን ጥበብ የሚንጸባረቅባቸው በርካታ አባባሎችን ይዟል። ይሁን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ራሱ ምሥክርነት ሲሰጥ “ቅዱስ መጽሐፉ ሁሉ በአምላክ መንፈስ መሪነት የተጻፈ ነው” እንደሚል ልብ በል። (2 ጢሞቴዎስ 3:16) የዚህን አባባል እውነተኝነት የሚያረጋግጡ በርካታ ማስረጃዎች አሉ። የሚከተሉትን ተመልከት፦

  •   በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተመዝግበው የሚገኙት ታሪኮች ትክክለኛ ናቸው የሚለውን ሐሳብ ውድቅ ማድረግ የቻለ አንድም ሰው የለም።

  •   የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎች ፍጹም ግልጽነት በሚንጸባረቅበት መንገድ የጻፉ ሐቀኛ ሰዎች ነበሩ። ግልጽነታቸው ደግሞ የጻፏቸው ነገሮች እውነት መሆናቸውን ያሳያል።

  •   መጽሐፍ ቅዱስ አንድ ማዕከላዊ ጭብጥ አለው ይኸውም አምላክ የሰው ልጆችን ለመግዛት ያለው መብት መረጋገጡ እንዲሁም በሰማይ ባለው መንግሥቱ አማካኝነት ዓላማውን ከግብ የሚያደርስ መሆኑ ነው።

  •   መጽሐፍ ቅዱስ በሺህ ከሚቆጠሩ ዓመታት በፊት የተጻፈ ቢሆንም በጥንቱ ዓለም ሰፊ ተቀባይነት አግኝተው ከነበሩ በርካታ የተሳሳቱ ሳይንሳዊ አመለካከቶች የጸዳ ነው።

  •   የታሪክ መዛግብት እንደሚያረጋግጡት የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች ፍጻሜያቸውን አግኝተዋል።