መጠበቂያ ግንብ—የጥናት እትም ሐምሌ 2015

ይህ እትም ከነሐሴ 31 እስከ መስከረም 27, 2015 የሚጠኑ የጥናት ርዕሶችን ይዟል።

ራሳቸውን በፈቃደኝነት አቅርበዋል—ሩሲያ

ሰባኪዎች ይበልጥ ወደሚያስፈልጉበት ወደ ሩሲያ ስለተዛወሩ ያገቡም ሆነ ያላገቡ ክርስቲያኖች እንድታነብ እንጋብዝሃለን። በይሖዋ ላይ ይበልጥ መታመንን ተምረዋል!

መንፈሳዊውን ገነት ይበልጥ አስውቡት

መንፈሳዊው ገነትና መንፈሳዊው ቤተ መቅደስ ትርጉማቸው አንድ ነው? ጳውሎስ ‘በሦስተኛው ሰማይ’ ላይ የተመለከተው “ገነት” ምንድን ነው?

‘በመከራ ቀናት’ ይሖዋን ማገልገል

ጠንካራ እምነት ይዛችሁ መቀጠልና በይሖዋ አገልግሎት ንቁ ተሳትፎ ማድረግ የምትችሉት እንዴት ነው? ይሖዋን በደስታ ስላገለገሉት በጥንት ጊዜ የኖሩ አገልጋዮቹ አንብቡ።

‘መዳናችሁ እየቀረበ ነው’!

ታላቁ መከራ ከጀመረ በኋላ ምን መልእክት ይታወጃል? በዚህ ጊዜ ውስጥ ቅቡዓኑ ምን ይሆናሉ?

ሥራህን የሚያይልህ ሰው አለመኖሩ ለውጥ ያመጣል?

ባስልኤልና ኤልያብ የተዉት ምሳሌ አንድ አስፈላጊ ሐቅ ያስገነዝበናል፦ የምንሠራውን ሥራ ማንም ሰው ባያይልን እንኳ ይሖዋ ያየዋል።

ለአምላክ መንግሥት ምንጊዜም ታማኝ ሁኑ

ክርስቲያኖች ለይሖዋና ለመንግሥቱ ታማኝ ለመሆን ራሳቸውን ማሠልጠን የሚችሉት እንዴት ነው?

ይህ የአምልኮ ቦታችን ነው

የንጹሕ አምልኮ ማዕከሎች የሆኑትን አዳራሾቻችንን እንዴት ልንይዛቸው ይገባል? አዳራሹን ለመገንባትና ለመንከባከብ የሚያስፈልገው ገንዘብ የሚገኘው ከየት ነው?

ይህን ያውቁ ኖሯል?

መጽሐፍ ቅዱስ የተስፋይቱ ምድር የተወሰኑ ክፍሎች በደን የተሸፈኑ እንደነበሩ ይናገራል። በዛሬው ጊዜ አብዛኛው ክፍል የተመነጠረ ከመሆኑ አንጻር ይህ እውነት ሊሆን ይችላል?