በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ታስታውሳለህ?

ታስታውሳለህ?

ታስታውሳለህ?

በቅርቡ የወጡትን የመጠበቂያ ግንብ እትሞች በማንበብ ተጠቅመሃል? እስቲ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር:-

• የክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት “ጉባኤ” የሚለውን ቃል በየትኞቹ አራት መንገዶች ተጠቅመውበታል?

ጉባኤ የሚለው ቃል በዋነኛነት የተሠራበት መላውን የቅቡዓን ክርስቲያኖች ቡድን ለማመልከት ነው (በአንዳንድ ጥቅሶች ላይ ክርስቶስንም ይጨምራል)። በሌላ ወቅት ደግሞ ‘የአምላክ ጉባኤ’ የሚለው አባባል በአንድ ወቅት የኖሩ ክርስቲያኖችን ለማመልከት ተሠርቶበታል። በሦስተኛ ደረጃ፣ ይህ ቃል በአንድ አካባቢ የሚገኙ ክርስቲያኖችን በአጠቃላይ ለማመልከት የተሠራበት ሲሆን በመጨረሻም በአንድ ጉባኤ የሚሰበሰቡ ክርስቲያኖችን ለማመልከት አገልግሏል።—4/15፣ ገጽ 21-23

• ወደ ሰማይ የመሄድ ተስፋ ያላቸው ክርስቲያኖች መጠራት የሚያበቃው መቼ ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ ለዚህ ጥያቄ ግልጽ የሆነ መልስ አይሰጥም። ጥሪው የጀመረው በ33 ከክርስቶስ ልደት በኋላ ሲሆን አሁንም ድረስ ቀጥሏል። ከ1935 ጀምሮ፣ ደቀ መዛሙርት የማድረጉ ሥራ እጅግ ብዙ ሰዎችን በመሰብሰቡ ላይ ያተኮረ ነበር። ይሁንና ከ1935 ወዲህ የተጠመቁ አንዳንድ ክርስቲያኖች ወደ ሰማይ የመሄድ ተስፋ እንዳላቸው መንፈስ ቅዱስ መሥክሮላቸዋል፤ በመሆኑም መጠራቱ የሚያበቃበትን ትክክለኛ ጊዜ መናገር አንችልም። እውነተኛ ቅቡዓን ክርስቲያኖች ከሌሎች በጎች የበለጠ የአምላክ መንፈስ የላቸውም፤ እንዲሁም ሌሎች እንዲያገለግሏቸው አይጠብቁም። ተስፋቸው በሰማይም ይሁን በምድር ሁሉም ክርስቲያኖች ታማኝ መሆንና የአምላክን ፈቃድ ማድረጋቸውን መቀጠል ይኖርባቸዋል።—5/1፣ ገጽ 30-31

• ዮፍታሔ ስእለት ሲሳል ቃል በቃል ልጁን የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ ለአምላክ ለማቅረብ ቃል መግባቱ ነበር?

በፍጹም አልነበረም። ዮፍታሔ መጀመሪያ የሚቀበለውን ሰው ለአምላክ አገልግሎት ሙሉ በሙሉ የተወሰነ እንዲሆን ለመስጠት ቃል መግባቱ ነው። የሙሴ ሕግ አንድን ሰው ለይሖዋ አገልግሎት ለመስጠት መሳል ይቻል እንደነበር ይጠቁማል። (1 ሳሙኤል 2:22) የዮፍታሔ ሴት ልጅ አባቷ የተሳለውን ስእለት ለመፈጸም ፈቃደኛ በመሆን በቤተ መቅደሱ ውስጥ ማገልገሏን ቀጥላለች። ሕይወቷን በሙሉ ባል ስለማታገባ የከፈለችው መሥዋዕትነት በቀላሉ የሚታይ አልነበረም።—5/15፣ ገጽ 9-10

• ኮዴክስ በጥንት የክርስትና ዘመን ምን ሚና ተጫውቷል?

ክርስቲያኖች ቢያንስ ከክርስቶስ ልደት በኋላ እስከ መጀመሪያው መቶ ዘመን ማብቂያ አካባቢ ድረስ በአብዛኛው በጥቅልሎች ይጠቀሙ የነበረ ይመስላል። በቀጣዩ መቶ ዘመን በአንድ በኩል ኮዴክስን በሌላ በኩል ደግሞ ጥቅልልን በሚደግፉ ሰዎች መካከል ውዝግብ ነበር። ክርስቲያኖች በኮዴክስ መጠቀማቸው ኮዴክስ ሰፊ ተቀባይነት እንዲኖረው በማድረግ ረገድ ጉልህ ሚና መጫወቱን ምሁራን ያምናሉ።—6/1፣ ገጽ 14-15

• የጌዝር የቀን መቁጠሪያ ምንድን ነው?

ጌዝር በምትባል ከተማ በ1908 የተገኘ ትንሽ የበሃ ድንጋይ ነው። ብዙዎች በዚህ ድንጋይ ላይ የተቀረጸው ጽሑፍ አንድ ተማሪ የጻፈው የቤት ሥራ ነው ብለው ያምናሉ። በድንጋዩ ላይ የተቀረጸው ጽሑፍ፣ በዘመናችን የቀን አቆጣጠር ከመስከረም አጋማሽ እስከ ጥቅምት አጋማሽ ባለው ጊዜ ከሚጀምረው የመከር ወቅት አንስቶ፣ በዓመት ውስጥ የሚሰበሰቡትን የሰብል ዓይነቶችና በእርሻ ወቅቶች የሚደረጉትን እንቅስቃሴዎች በአጭሩ ይዘረዝራል።—6/15፣ ገጽ 8

• በመንፈስ ቅዱስ ላይ ኃጢአት መሥራት ሲባል ምን ማለት ነው?

አንድ ሰው በይሖዋ ቅዱስ መንፈስ ላይ ኃጢአት ሊሠራ ይችላል። እንዲህ ያለው ኃጢአት ይቅርታ አይደረግለትም። (ማቴዎስ 12:31) ይቅር የማይባል ኃጢአት መሥራት አለመሥራታችንን የሚወስነውም ሆነ መንፈሱን ሊወስድብን የሚችለው አምላክ ብቻ ነው። (መዝሙር 51:11) በፈጸምነው ኃጢአት ከልብ ካዘንን፣ ይህ እውነተኛ ንስሐ መግባታችንን የሚያሳይ ሊሆን ይችላል። እንዲህ ከሆነ ደግሞ በመንፈስ ቅዱስ ላይ ኃጢአት አልሠራንም ማለት ነው።—7/15፣ ገጽ 16-17

• ንጉሥ ሳኦል ቀደም ብሎ ከዳዊት ጋር ይተዋወቅ ከነበረ፣ ዳዊትን ‘የማን ልጅ ነህ?’ ብሎ የጠየቀው ለምንድን ነው? (1 ሳሙኤል 16:22፤ 17:58)

ሳኦል ማወቅ የፈለገው የዳዊትን አባት ስም ብቻ አልነበረም። ዳዊት፣ ጎልያድን ያሸነፈ ታላቅ እምነትና ድፍረት ያለው ሰው መሆኑን ሲመለከት ሳኦል እንዲህ ዓይነቱን ወጣት ማን እንዳሳደገው ለማወቅ ፈልጎ ነበር። ሳኦል ይህን ጥያቄ ያቀረበው እሴይ ወይም ሌሎች የቤተሰቡ አባላት ወደ ጦር ሠራዊቱ እንዲቀላቀሉ ለማድረግ አስቦም ሊሆን ይቻላል።—8/1፣ ገጽ 31