በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ዳንኤልና በአውራጃ ስብሰባ ላይ ያደረገው ባጅ

ዳንኤልና በአውራጃ ስብሰባ ላይ ያደረገው ባጅ

ዳንኤልና በአውራጃ ስብሰባ ላይ ያደረገው ባጅ

ኢየሱስ፣ ራሳቸውን የሚያመጻድቁ የሃይማኖት መሪዎች ልጆች በአደባባይ አምላክን ሲያወድሱ ሰምተው በተናደዱ ጊዜ ገሥጿቸው ነበር። ከዚያም ‘ከልጆችና ጡት ከሚጠቡ ሕፃናት አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ የሚለውን ከቶ አላነበባችሁምን?’ በማለት ጠይቋቸዋል።—ማቴዎስ 21:15, 16

ጀርመን በሚገኝ የሩሲያ ቋንቋ ጉባኤ ውስጥ የሚሰበሰበው የስድስት ዓመቱ ዳንኤል በዘመናችንም ልጆች ይሖዋን እያወደሱ እንዳሉ አሳይቷል። ይህ ልጅ ከእናቱና ከእህቱ ጋር በዲስበርግ በተደረገው የአውራጃ ስብሰባ ላይ የተገኘ ሲሆን ቤተሰቡ እንዲህ ባለው ትልቅ ስብሰባ ላይ ሲገኝ ይህ የመጀመሪያ ጊዜው ነበር። ሁሉም ነገር ማለትም ሆቴሉ፣ ብዛት ያላቸው ተሰብሳቢዎች፣ ለሦስት ቀናት ቁጭ ብሎ ማዳመጥ፣ የጥምቀት ሥርዓቱ እንዲሁም ድራማው ለዳንኤል አዲስ ነበር። በዚህ ወቅት የዳንኤል ባሕርይ እንዴት ነበር? ለሌሎች ምሳሌ የሚሆን ባሕርይ አሳይቷል።

ዳንኤል ስብሰባው አልቆ ወደ ቤቱ ከተመለሰ በኋላ ሰኞ ዕለት ጠዋት ወደ ትምህርት ቤት ለመሄድ ተነሳ። ነገር ግን የስብሰባውን ባጅ ከኮቱ ላይ አላወለቀውም ነበር። እናቱም “ስብሰባው እኮ አልቋል፤ ዛሬ ባጁን ልታወልቀው ትችላለህ” አለችው። ዳንኤል ግን “ሰው ሁሉ የት እንደነበርኩና ምን እንደተማርኩ እንዲያውቅ እፈልጋለሁ” በማለት መለሰ። ከዚያም ቀኑን ሙሉ በኩራት ትምህርት ቤት ውስጥ ባጁን አድርጎት ዋለ። አስተማሪውም ስለ ባጁ በጠየቀችው ወቅት ስለ ስብሰባው ፕሮግራም በዝርዝር ነገራት።

ዳንኤል እንዲህ በማድረግ ባለፉት ዘመናት ይሖዋን በሕዝብ ፊት ያወደሱትን በሺህ የሚቆጠሩ ወንዶችና ሴቶች ልጆች ምሳሌ ተከትሏል።