በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

በይሖዋ ዓይን የላቀ ግምት የሚሰጠው ልግስና

በይሖዋ ዓይን የላቀ ግምት የሚሰጠው ልግስና

በይሖዋ ዓይን የላቀ ግምት የሚሰጠው ልግስና

የሚከተለውን ደብዳቤ የላከልን ሞዛምቢክ የሚገኘው የይሖዋ ምሥክሮች ቅርንጫፍ ቢሮ ነው:-

“የሰባት ዓመት ልጅ ነኝ። ገና የአንደኛ ደረጃ ተማሪ ነኝ። ይህ የላክሁላችሁ 12, 000 ሜቲካይስ [አንድ የአሜሪካ ዶላር] ያሳደግሁትን ጫጩት ሸጬ ያገኘሁት ገንዘብ ነው። የመጀመሪያው የዶሮ ጫጩቴ አድጎ አውራ ዶሮ እንዲሆን ስላደረገልኝ ይሖዋን አመሰግነዋለሁ። የላኩት ስጦታ የይሖዋን መንግሥት ሥራ ለመደገፍ እንዲውል እፈልጋለሁ።

“ማሳሰቢያ:- ይህን ደብዳቤ በመጻፍ አባቴ ረድቶኛል።”

አንዳንድ ሰዎች ልግስናን የሚያያይዙት የተትረፈረፈ ቁሳዊ ሀብት ካላቸው ሰዎች ጋር ነው። ይሁን እንጂ በመዝገብ ውስጥ “ሁለት ሳንቲም” ብቻ ስለጣለችው መበለት የሚናገረውን የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባ ስናነብ ልግስና የሚለካው በሚሰጠው ነገር መጠን ሳይሆን በግለሰቡ ትክክለኛ የልብ ዝንባሌ እንደሆነ እንገነዘባለን።​—⁠ሉቃስ 21:​1-4

ይሖዋ በፍቅር በተገፋፋ ልብ የሚቀርበውን ስጦታ የቱንም ያህል ትንሽ ቢሆን በጣም ያደንቃል። ጊዜያቸውን፣ ጉልበታቸውን ወይም ቁሳዊ ንብረታቸውን ለመንግሥቱ ሥራ በማዋል የእርሱን ልግስና የሚኮርጁትን ሁሉ አትረፍርፎ ይባርካቸዋል።​—⁠ማቴዎስ 6:​33፤ ዕብራውያን 6:​10