በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ቤተሰብ የሚወያይበት

ቤተሰብ የሚወያይበት

ቤተሰብ የሚወያይበት

ይህ የሆነው የት ነበር?

1. ይህ ድርጊት የተፈጸመው የት ከተማ አጠገብ ነው?

ፍንጭ፦ የሐዋርያት ሥራ 6:7-9ን እና 7:54-60ን አንብብ። መልስህን በካርታው ላይ አክብብ።

ደማስቆ

ኢየሩሳሌም

ቤተልሔም

2. እስጢፋኖስን የሚወግሩት ለምንድን ነው?

․․․․․

3. እስጢፋኖስ የሚወግሩትን ሰዎች አምላክ ምን እንዲያደርጋቸው ጠየቀ?

․․․․․

ለውይይት፦

እስጢፋኖስ ለወገሩት ሰዎች ስለነበረው አመለካከት ምን ይሰማሃል? በእስጢፋኖስ ቦታ ብትሆን ኖሮ ምን ታደርግ ነበር? ለምን?

ስለ ንጉሥ ሕዝቅያስ ምን የምታውቀው ነገር አለ?

4. የሕዝቅያስ አባት ማን ነበር?

ፍንጭ፦ 2 ነገሥት 18:1ን አንብብ።

․․․․․

5. የሕዝቅያስ አባት በጣም ክፉ ሰው የነበረ ቢሆንም ሕዝቅያስ ምን ዓይነት ስም አትርፎ ነበር?

ፍንጭ፦ 2 ነገሥት 18:5ን አንብብ።

․․․․․

ለውይይት፦

ሕዝቅያስ ጠንካራ ሆኖ እንዲቀጥል የረዳው ምንድን ነው?

ፍንጭ፦ 2 ነገሥት 18:6ን አንብብ።

ከቤተሰብህ አባል አንዱ አምላክን ማገልገል ቢያቆም የሕዝቅያስን ምሳሌ ልትከተል የምትችለው እንዴት ነው?

ለልጆች የቀረበ የሥዕል ጥያቄ

ከዚህ መጽሔት ውስጥ እነዚህን ሥዕሎች ማግኘት ትችላለህ? እያንዳንዱ ሥዕል ምን እንደሚያሳይ በራስህ አባባል ግለጽ።

ከዚህ እትም

የሚከተሉትን ጥያቄዎች መልስ፤ እንዲሁም የጎደለውን ቁጥር አሟላ።

ገጽ 5 የሰውነታችን አሠራር ምን ያረጋግጣል? መዝሙር 139:․․․

ገጽ 8 የአምላክ ሰላም ምን ያደርጋል? ፊልጵስዩስ  4:․․․

ገጽ 14 አንድ ዕፍኝ እረፍት ከምን ይሻላል? መክብብ 4:․․․

ገጽ 23 አምላክ የሚወደው ምን ዓይነት ሰው ነው? 2 ቆሮንቶስ 9:․․․

● መልሱ በገጽ 11 ላይ ይገኛል

በገጽ 31 ላይ ለቀረቡት ጥያቄዎች የተሰጡ መልሶች

1. ኢየሩሳሌም።

2. እስጢፋኖስ አምላክን ተሳድቧል ተብሎ ስለ ተከሰሰ።

3. የወገሩትን ሰዎች ይቅር እንዲላቸው።

4. ንጉሥ አካዝ።

5. ለእውነተኛው አምልኮ በነበረው ቅንዓት ረገድ እንደ እሱ ያለ ሌላ ንጉሥ አልነበረም።