በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ንቁ! ቁጥር 2 2018 | ቤተሰብ ስኬታማ እንዲሆን የሚረዱ 12 ወሳኝ ነገሮች

ቤተሰብ ስኬታማ እንዲሆን የሚረዱ 12 ወሳኝ ነገሮች

ብዙውን ጊዜ አንድ ቤተሰብ ስኬታማ ሳይሆን የቀረው ለምን እንደሆነ ሲነገር እንሰማለን። በአንጻሩ ግን አንዳንድ ቤተሰቦች ስኬታማ ሊሆኑ የቻሉት ለምንድን ነው?

  • በዩናይትድ ስቴትስ፣ በ1990 እና በ2015 መካከል ባለው ጊዜ ውስጥ ከ50 ዓመት በላይ የሆኑ ሰዎች ፍቺ በእጥፍ የጨመረ ሲሆን ከ65 ዓመት በላይ የሆኑ ሰዎች ፍቺ ቁጥር ደግሞ በሦስት እጥፍ ጨምሯል።

  • ወላጆች ግራ ገብቷቸዋል፤ አንዳንድ ባለሙያዎች ‘ልጆች ምንም አደረጉ ምን እነሱን ማበረታታት አስፈላጊ ነው’ በማለት ይመክራሉ፤ ሌሎች ደግሞ አንድ አፍቃሪ ወላጅ በልጆቹ ላይ ጥብቅ መሆን እንዳለበት ይናገራሉ።

  • ወጣቶች ስኬታማ ለመሆን የሚያስፈልጓቸውን ችሎታዎች ሳይማሩ ያድጋሉ።

ሐቁ ግን የሚከተለው ነው፦

  • ትዳር አስደሳችና ዘላቂ ጥምረት መሆን ይችላል።

  • ወላጆች ልጆቻቸውን በፍቅር መቅጣት የሚችሉበትን መንገድ ሊማሩ ይችላሉ።

  • ወጣቶች አዋቂ ሲሆኑ የሚያስፈልጓቸውን ችሎታዎች ከልጅነታቸው መማር ይችላሉ።

ይህን ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው? ይህ ንቁ! መጽሔት ቤተሰብ ስኬታማ እንዲሆን የሚረዱ 12 ወሳኝ ነገሮችን ያብራራል።

 

1፦ ቃል ኪዳንን ማክበር

ባልና ሚስቶች ቃል ኪዳናቸውን አክብረው እንዲኖሩ የሚረዱ ሦስት ጠቃሚ ምክሮች።

2፦ ተባብሮ መሥራት

ከባለቤትህ ጋር የትዳር ጓደኛሞች ናችሁ ወይስ ደባል?

3፦ መከባበር

የትዳር ጓደኛህ እንዳከበርካት የሚሰማት ምን ብትላት ወይም ምን ብታደርግላት እንደሆነ የሚጠቁሙ ጠቃሚ ምክሮች።

4፦ ይቅር ባይ መሆን

በትዳር ጓደኛችሁ አለፍጽምና ላይ ትኩረት ላለማድረግ ምን ሊረዳችሁ ይችላል?

5፦ የሐሳብ ልውውጥ ማድረግ

ከልጆቻችሁ ጋር ይበልጥ መቀራረብ እንድትችሉ የሚረዱ ሦስት ጠቃሚ ምክሮች።

6፦ ተግሣጽ መስጠት

ለልጆች ተግሣጽ መስጠት በራሳቸው እንዳይተማመኑ ያደርጋቸዋል?

7፦ በሥነ ምግባር መሥፈርቶች መመራት

ልጆቻችሁን ማስተማር ያለባችሁ የትኞቹን የሥነ ምግባር መሥፈርቶች ነው?

8፦ ምሳሌ መሆን

የምትናገሩት ነገር የልጆቻችሁን ልብ እንዲነካ ከፈለጋችሁ እናንተ ራሳችሁ እንደምትሉት ሆናችሁ መገኘት አለባችሁ።

9፦ ማንነትን ማወቅ

ወጣቶች ለሚያምኑበት ነገር ጥብቅና መቆም የሚችሉት እንዴት ነው?

10፦ እምነት የሚጣልበት መሆን

የወላጆችህን አመኔታ ማትረፍህ እየበሰልክ መምጣትህን የሚያሳይ አንድ ምልክት ነው።

11፦ ታታሪ መሆን

ገና በወጣትነታችሁ ተግቶ መሥራትን ከተማራችሁ በሕይወታችሁ ውስጥ በምታከናውኑት ሥራ ሁሉ ስኬታማ መሆን ትችላላችሁ።

12፦ ግብ ማውጣት

ያወጣሃቸው ግቦች ላይ መድረስህ በራስ የመተማመን ስሜትህ ከፍ እንዲል፣ ከሌሎች ጋር ያለህ ወዳጅነት እንዲጠናከርና ይበልጥ ደስተኛ እንድትሆን ይረዳሃል።

ለቤተሰቦች የሚሆን ተጨማሪ እርዳታ

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘው ምክር ትዳርህ ስኬታማ እንዲሆንና አስደሳች የቤተሰብ ሕይወት እንዲኖርህ ይረዳሃል።