በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ይቅር ባይ መሆን በጠብ ምክንያት የተነሳውን እሳት ለማጥፋት ያስችላል

 ለባለትዳሮች

4፦ ይቅር ባይ መሆን

4፦ ይቅር ባይ መሆን

ምን ማለት ነው?

አንድ ሰው ይቅር ባይ ነው የሚባለው የተፈጸመበትን በደል የሚተውና በዚህ ምክንያት ያደረበትን ቅሬታ የሚያስወግድ ከሆነ ነው። ይቅር ባይ መሆን ሲባል የተፈጸመውን በደል አቅልሎ መመልከት ወይም ጨርሶ እንዳልተፈጸመ መቁጠር ማለት አይደለም።

የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ፦ “አንዱ በሌላው ላይ ቅር የተሰኘበት ነገር ቢኖረው እንኳ እርስ በርስ መቻቻላችሁንና በነፃ ይቅር መባባላችሁን ቀጥሉ።”—ቆላስይስ 3:13

“አንድን ሰው የምትወዱት ከሆነ በዚያ ሰው አለፍጽምና ላይ ከማተኮር ይልቅ ግለሰቡ ምን ዓይነት ሰው ለመሆን እየጣረ እንደሆነ ትመለከታላችሁ።”—አሮን

አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

ቂም መያዝ በትዳራችሁ ላይ ከሚያስከትለው ጉዳት ባሻገር አካላዊም ሆነ ስሜታዊ ጉዳት ሊያስከትልባችሁ ይችላል።

“በአንድ ወቅት ባሌ ስሜቴን በጣም ስለጎዳው ይቅርታ ጠየቀኝ። በወቅቱ ይቅር ማለት ከብዶኝ ነበር። ከጊዜ በኋላ ባለቤቴን ይቅር ያልኩት ቢሆንም ወዲያውኑ ይቅር አለማለቴ ይቆጨኛል። ምክንያቱም ሁኔታው በመካከላችን አላስፈላጊ ውጥረት እንዲፈጠር አድርጓል።”—ጁልያ

ምን ማድረግ ትችላለህ?

ራስህን ፈትሽ

የትዳር ጓደኛችሁ በተናገረው ወይም ባደረገው ነገር ስሜታችሁ ሲጎዳ ራሳችሁን እንዲህ እያላችሁ ጠይቁ፦

  • ‘እንዲህ የተሰማኝ ሆደ ባሻ ሆኜ ይሆን?’

  • ‘የተፈጸመብኝ በደል በጣም ከባድ ስለሆነ የግድ ይቅርታ ልጠየቅ ይገባል የሚል አቋም አለኝ? ወይስ በደሉን ችላ ብዬ ላልፈው እችላለሁ?’

የሚከተሉትን ጥያቄዎች ከትዳር ጓደኛችሁ ጋር ተወያዩባቸው

  • አንዳችን ሌላውን ይቅር ለማለት በአብዛኛው ምን ያህል ጊዜ ይወስድብናል?

  • ቂም ይዘን እንዳንቆይ ምን ማድረግ እንችላለን?

ጠቃሚ ምክሮች

  • ቅር የሚያሰኝ ነገር ሲያጋጥማችሁ የትዳር ጓደኛችሁ እናንተን ለመጉዳት ሆን ብሎ ያደረገው ነገር እንደሆነ አድርጋችሁ አታስቡ።

  • “ሁላችንም ብዙ ጊዜ [እንደምንሰናከል]” በማስታወስ የትዳር ጓደኛችሁ ያደረገውን ነገር በይቅርታ ለማለፍ ጥረት አድርጉ።—ያዕቆብ 3:2

“ሁለታችንም ጥፋተኞች ስንሆን ይቅር መባባል ቀላል ነው፤ ጥፋቱ የሌላው ሰው ነው ብለን በምናስብበት ጊዜ ግን ይቅርታ ማድረግ በጣም አስቸጋሪ ይሆንብናል። ይቅርታ ስትጠየቁ ይቅርታ ማድረግ እውነተኛ ትሕትና ይጠይቃል።”—ኪምበርሊ

የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ፦ “ፈጥነህ ታረቅ።”—ማቴዎስ 5:25

ቂም መያዝ በትዳራችሁ ላይ ከሚያስከትለው ጉዳት ባሻገር አካላዊም ሆነ ስሜታዊ ጉዳት ሊያስከትልባችሁ ይችላል