የደብዳቤ አጻጻፍ
ጥናት 17
የደብዳቤ አጻጻፍ
1, 2. ደብዳቤዎች ምን ዓይነት ጥሩ ዓላማ ሊያከናውኑ ይችላሉ?
1 በጥንቱ የክርስቲያን ጉባኤ ደብዳቤዎች በብዙ መንገድ ጥቅም አስገኝተዋል። ጉባኤዎች እርስ በርሳቸው የሚገናኙበት አንዱ መንገድ በደብዳቤ አማካኝነት ነበር። (ፊልጵ. 1:1) ደብዳቤዎች ልዩ ኃላፊነት የተጣለባቸውን ወንድሞች ለማበረታታት አገልግለዋል። (2 ጢሞ. 1:1, 2, 6) ደብዳቤዎች ወደ ክርስትና ከመጡ ብዙ ጊዜ ያልሆናቸውንና የተለያየ መከራ የደረሰባቸውን ያንጹ ነበር። (1 ተሰ. 1:1–7፤ 3:1–7) በተጨማሪም የጥንቶቹ ክርስቲያኖች በጌታ አገልግሎት የቅርብ ወዳጆቻቸው ከሆኑት ወንድሞች በደብዳቤ አማካኝነት ግንኙነት ያደርጉ ነበር። — 3 ዮሐ. 1, 14
2 በዘመናችን የሚኖሩት ቲኦክራሲያዊ አገልጋዮችም ቢሆኑ ደብዳቤ የሚጽፉባቸው ብዙ ምክንያቶች ያጋጥሙአቸዋል። ደብዳቤዎቻቸውም ብዙ ጠቃሚ ሥራ ሊያከናውኑ ይችላሉ። ለሥራ ጉዳይ ደብዳቤ መጻፍ አስፈላጊ የሚሆንባቸው ጊዜያት ሊኖሩ ይችላሉ። የመንግሥቱን ሥራ አስመልክቶ ለሕዝብ ባለ ሥልጣናት ደብዳቤ መጻፍ ሊያስፈልግ ይችላል። የውጭ ሰው እንዲገባ በማይፈቀድባቸው ሕንጻዎች ለሚኖሩ ሰዎችና የይሖዋ ምሥክሮች በማይገኙባቸው ገለልተኛ አካባቢዎች ለሚኖሩ ሰዎች “ምሥራቹን” ለማድረስ የሚቻለው በደብዳቤ አማካኝነት ብቻ
ነው። በጉባኤህ የነበሩ አስፋፊዎች ወደሌላ አካባቢ ተዛውረው ይሆናል። ወይም ራቅ ባለ አካባቢ የሚኖሩ ዘመዶች ሊኖሩህ ይችላሉ። ለእነዚህ ሰዎች ፍቅራዊ አሳቢነት ያለህ መሆኑን ደብዳቤ በመጻፍ ለማሳየት ትፈልግ ይሆናል። በተጨማሪም አመስጋኝነትህን ወይም ሐዘንህን ለመግለጽ ደብዳቤ የምትልክባቸው ጊዜያት ይኖራሉ።3. ደብዳቤዎቻችን የተሰጠንን አገልግሎት የሚያስከብሩ እንዲሆኑ ከተፈለገ ምን ዓይነት ባሕርይ ሊኖራቸው ይገባል?
3 የምንጽፋቸው ደብዳቤዎች አምላክ ለሰጠን አገልግሎት ክብር የሚሰጡ መሆን ይኖርባቸዋል። ለሚያነቡአቸው ሰዎች የወዳጅነት መንፈስ፣ ዘዴኛነትና አሳቢነት ያለን መሆኑን የሚያሳዩ መሆን ይኖርባቸዋል። አፍራሽና ችግር የሚያወሩ ከመሆን ይልቅ አዎንታዊና የሚያንጹ መሆን ይገባቸዋል። አፍራሽና ችግር የሚያወሩ ደብዳቤዎች እምነት የሚያፈርሱ ከመሆናቸውም ሌላ አንባቢውን ያሳዝናሉ። የአምላክ ቃል “ፍቅር ያንጻል” ይላል። (1 ቆሮ. 8:1) በተጨማሪም ደብዳቤው ያለውን አጠቃላይ መልክና በሚመለከቱት ሰዎች ላይ የሚያሳድረውን መንፈስ ግምት ውስጥ ማስገባት ያስፈልጋል። ደብዳቤው ንጹሕ ሆኖ እንዲታይ በጎንና በጎኑ እንዲሁም በራስጌውና በግርጌው በቂና የማይበላለጥ ህዳግ መተው ይጠቅማል። ስርዝና ድልዝ ያለበት ከሆነ የሚመለከተው ሰው ለደብዳቤው ጥሩ ግምት አይኖረውም። በተጨማሪም ቃሎቹ የሆሄያት ግድፈት የሌላቸው መሆናቸውንና አረፍተ ነገሮቹ በጥሩ ሁኔታ የተቀናበሩ መሆናቸውን ማረጋገጥ ተገቢ ነው። ይሁን እንጂ በዚህ ረገድ ጥሩ ችሎታ ባይኖርህ ተስፋ ቆርጠህ ለወዳጆችህ ደብዳቤ መጻፍ ማቆም አይገባህም። በደብዳቤህ የሚንጸባረቀው ፍቅራዊ ስሜት፣ ግለትና አሳቢነት በቃላት አጻጻፍና በአረፍተ ነገሮች ቅንብር ረገድ የምታደርገውን ስህተት ሊያካክስልህ ይችላል። ቢሆንም የሆሄያት ግድፈት በመዝገበ ቃላት በመጠቀም ሊሻሻል ይችላል። አረፍተ ነገር የማቀናበር ችሎታችንም ሌሎች እንዴት ቃላትንና ሐረጎችን አሳክተው ጥሩ አረፍተ ነገር እንደሚያቀናብሩ በማጤን ሊሻሻል ይችላል። እነዚህን ነጥቦች በአእምሮአችን ይዘን ከአገልግሎታችን ጋር በተያያዘ ጉዳይ ስለምንጽፋቸው የተለያዩ ዓይነት ደብዳቤዎች ከዚህ ቀጥሎ እንመልከት።
4. የሥራ ደብዳቤ ምን ዓይነት ቅርጽ ሊኖረው እንደሚገባ ግለጽ።
4 ስለ ሥራ ጉዳይ የሚጻፉ ደብዳቤዎች። ለሥራ ጉዳይ ደብዳቤ በምትጽፍበት ጊዜ ከደብዳቤው አናት ላይ ስምህን፣ አድራሻህንና ቀኑን ብትጽፍ ጥሩ ይሆናል። ይህ የደብዳቤው ርዕስ ሲባል የሚጻፈውም ከወረቀቱ በስተቀኝ ነው። (ለመጠበቂያ ግንብ ማኅበር በሚጻፉ ደብዳቤዎች ላይ ጉዳዩ አንድን ጉባኤ የሚመለከት ከሆነ በደብዳቤው ርዕስ ላይ የላኪው ጉባኤ ስም መጻፍ ይኖርበታል።) “የውስጡ የተቀባይ አድራሻ” በወረቀቱ በስተግራ ከደብዳቤው ርዕስ ጥቂት ዝቅ ብሎ ይጻፋል። እዚህ ላይ ደብዳቤውን የምትጽፍለትን ድርጅት ወይም ግለሰብ ስም ትጽፋለህ። ከዚህ በኋላ የሚቀጥለው የደብዳቤው መክፈቻ የሆነው አርዕስት ነው። ከይሖዋ ምሥክሮች ጋር ግንኙነት ለሌላቸው ድርጅቶች ወይም
ግለሰቦች በምትጽፍበት ጊዜ “ክቡር ሆይ” ወይም “የተከበሩ አቶ——” ወይም ይህንን በሚመስሉ ሌሎች ቃላት መጠቀም ተገቢ ይሆናል። ለማኅበሩ ወይም የይሖዋ ምሥክሮች ለሆኑ ሰዎች በምትጽፍበት ጊዜ ደግሞ “ውድ ወንድሞች” ወይም “የተወደድህ ወንድም——” ብሎ መጀመር የተለመደ ነው። በመጨረሻም “አክባሪዎ” ወይም “ከሰላምታ ጋር” እንደሚሉት ያሉ የመደምደሚያ ቃላት ይጻፋሉ። በይሖዋ ድርጅት ውስጥ ላሉ ሰዎች በምትጽፍበት ጊዜ እንደ “ወንድማችሁ” ወይም “የአገልግሎት ባልደረባችሁ” ያሉትን የመደምደሚያ ቃላት መጠቀም ተገቢ ነው። ይህ የመደምደሚያ ቃል መጻፍ የሚጀምረው ከገጹ አጋማሽ ጀምሮ ሲሆን ነጠላ ሰረዝ ይከተለዋል። ከዚህ ግርጌ ፊርማህን ታስቀምጣለህ። ደብዳቤው አንድን ጉባኤ ወይም ክልል ስለሚመለከት ጉዳይ ለማኅበሩ የተጻፈ ከሆነ የደብዳቤው ጸሐፊ ከፊርማው ግርጌ “መሪ የበላይ ተመልካች” ወይም “የክልል የበላይ ተመልካች” ብሎ በመጻፍ የአገልጋይነት ቦታውን ይገልጻል።5, 6. በደብዳቤው ላይ በመጀመሪያ ደረጃ ሊደረግ የሚገባው ነገር ምንድን ነው? አብዛኛውን ጊዜ ጥሩ ምላሽ ለማግኘት የሚረዳው ምንድን ነው?
5 ገና ደብዳቤህን ስትጀምር የደብዳቤህን ዓላማ ግለጽ። ይህን ካደረግህ የደብዳቤው ተቀባይ የጻፍክበትን ምክንያት ለማወቅ ይችላል። ደብዳቤው ከዚህ በፊት ከተጻጻፋችሁበት ጉዳይ ጋር ግንኙነት ያለው ከሆነ ይህን ቀደም ያለ ደብዳቤና ስለምን ጉዳይ የተጻፈ መሆኑን መጥቀስ ጥሩ ይሆናል። ደብዳቤው የተጻፈው ብዙ መምሪያዎች ላሉት ትልቅ ድርጅት ከሆነ ድርጅቱ ቀደም ሲል ለላከልህ ደብዳቤ መለያ እንዲሆን የጻፈው ምልክት ወይም ቁጥር ካለ ቢጠቀስ ጠቃሚ ይሆናል። በደብዳቤው አካል ረገድ ለእያንዳንዱ ጉዳይ ወይም ሐሳብ የተለያየ አንቀጽ መጠቀም ጥሩ ውጤት እንደሚያስገኝ መገንዘብ ትችላለህ። ይህን ማድረግህ በደብዳቤህ ውስጥ የጠቀስካቸው የተለያዩ ጉዳዮች ተለይተው እንዲታዩ ስለሚያደርግ አብዛኛውን ጊዜ የተሻለ አገልግሎት እንድታገኝ ያስችልሃል። ደብዳቤህ በከፊል የሥራ ጉዳይ፣ በከፊል ደግሞ ስለ አጠቃላይ ነገሮች የሚገልጽ ከሆነ የሥራውን ጉዳይ ማስቀደሙ ይመረጣል።
6 ደብዳቤ በሚጻፍበት ጊዜ ሁሉ ሐሳብን በአጭሩ መግለጽ በጣም ጠቃሚ ነው። ቢሆንም ልታስተላልፍ የፈለግከው መልእክት ወይም መረጃ ግልጽና የተሟላ መሆን ይኖርበታል። ይሁን እንጂ አስፈላጊ ያልሆኑ ቃላትና ተደጋጋሚ ሐሳቦች ታርመው ቢወጡ ደብዳቤህ ይበልጥ ውጤታማ ሊሆን ይችላል። ከምትጽፈው ጉዳይ ጋር ቀጥተኛ ተዛምዶ የሌላቸውን ነገሮች ብታስወጣ የደብዳቤህ ዓላማ በይበልጥ ግልጽ ሊሆን ይችላል። በተጨማሪም በደብዳቤህ ላይ ሰዎቹ ላደረጉት መልካም ጥረት አድናቆት መግለጽ አብዛኛውን ጊዜ ተገቢ ነው። አንዳንድ ችግሮችን በዝርዝር የሚገልጽ የሥራ ደብዳቤ እንኳን “ለሚደረግልኝ ትብብር ሁሉ አመስጋኝ ነኝ” የሚል ወይም ይህን የሚመስል ሐሳብ ከተጨመረበት
ጥሩ ምላሽ ማግኘት ይቻላል።7–9. ምሥክርነት ለመስጠት ታቅዶ በሚጻፍ ደብዳቤ ውስጥ ምን ነገር ሊገለጽ ይችላል?
7 ምሥክርነት ለመስጠት። በተጨማሪም ደብዳቤ መጻፍ የመንግሥቱን መልእክት በማሰራጨት ረገድ ትልቅ አገልግሎት አበርክቶአል። በአንዳንድ አካባቢዎች በቀላሉ ሊሠራ የማይቻልባቸው ትላልቅ የአፓርተማ ሕንጻዎችና የመኖሪያ ሆቴሎች አሉ። እንደነዚህ ባሉት ቦታዎች ለሚኖሩ ሰዎች ደብዳቤ መጻፍ እንችላለን። አንዳንዶችን ደግሞ ከቤት ወደ ቤት በሚደረገው አገልግሎት እቤታቸው ማግኘት አስቸጋሪ ይሆናል። የሚደርሳቸውን ደብዳቤ ግን ተቀብለው ማንበባቸው አይቀርም። በሕመም ወይም በአካለ ስንኩልነት ምክንያት ከቤቱ መውጣት የማይችል አስፋፊ የመንግሥቱን ምሥራች ለሌሎች ሊያካፍል የሚችለው እንደነዚህ ላሉት ሰዎች ደብዳቤ በመጻፍ ብቻ ሊሆን ይችላል።
8 ስለ አምላክ መንግሥት ምሥክርነት ለመስጠት ደብዳቤ በምትጽፍበት ጊዜ መጀመሪያ ራስህን ብታስተዋውቅ ጥሩ ይሆናል። በተጨማሪም በግል ሄደህ ከማነጋገር ይልቅ ደብዳቤ ለመጻፍ የተገደድክበትን ምክንያት መግለጽ ትፈልግ ይሆናል። ይህን ማድረግህ ደብዳቤህ የሚደርሰው ሰው ልባዊ አሳቢነት ያለህ ሰው መሆንህን ሊያስገነዝበው ይችላል። ከዚህ በኋላ በግል አግኝተህ ብታነጋግረው ኖሮ ልታወያየው የፈለግከውን ነገር መጻፍ ጀምር። በአገልግሎት ትምህርት ቤት ስትማር የቆየሃቸውን መሠረታዊ ሥርዓቶች ሥራ ላይ ካዋልክ ይህን ማድረግ አስቸጋሪ አይሆንብህም። በቅርቡ በመንግሥት አገልግሎታችን ላይ በወጣ የአቀራረብ ዘዴ ልትጠቀም ወይም በመጠበቂያ ግንብ ወይም በንቁ! መጽሔት ላይ የተገለጸውን ሐሳብ በራስህ አነጋገር ልትጽፍለት ትችላለህ። አለበለዚያም በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ ከተባለው መጽሐፍ ሐሳብ መውሰድ ትችላለህ። በተጨማሪም አንድ ትራክት ወይም መጽሔት ወይም መጽሐፍ አብረህ ልትልክና ጽሑፉን እንዲያነበው ልታበረታታው ትችላለህ። የጻፍክለት ጉዳይ በጣም አስፈላጊ የሆነበትን ምክንያት ግለጽለት። ከቤት ወደ ቤት ስታገለግል እንደምታደርገው ጥቅሶቹን ከራሱ መጽሐፍ ቅዱስ አውጥቶ እንዲያነብ ልታበረታታው ትችላለህ። በመጨረሻም የተቀሰቀሰውን ፍላጎት ለማጠናከር እንድትችል እንዴት ሊያገኝህ እንደሚችልና ተገናኝታችሁ ብትነጋገሩ በጣም ደስ እንደሚልህ ግለጽለት። ሊያመሰግንህ ከፈለገ ወይም የመጠበቂያ ግንብ ወይም የንቁ! መጽሔት ኮንትራት ለመግባት ከፈለገ የት ለመጻፍ እንደሚችል እንዲያውቅ አድራሻህንና ስምህን ግልጽ አድርገህ ጻፍለት።
9 ምን ጊዜም ቢሆን በፖስታው ላይ የራስህን አድራሻ መጻፍ አትዘንጋ። በተለይ በፖስታህ ውስጥ ጽሑፍ ጨምረህ ከነበረ ለክብደቱ ተመጣጣኝ የሆነ የፖስታ ቴምብር የተለጠፈ መሆኑን አረጋግጥ። ተመጣጣኝ የሆነ ቴምብር ያልተለጠፈበት ከሆነ ደብዳቤውን የሚቀበለው ሰው ተጨማሪ ገንዘብ እንዲከፍል ሊጠየቅ ይችላል። ይህም ጥሩ
ምሥክርነት ለመስጠት የሚያስችልህን አጋጣሚ ያበላሽብሃል።10, 11. ለወዳጆችና ለቤተሰብ አባሎች የሚጻፉ ደብዳቤዎች ጠቃሚ የሚሆኑት ለምንድን ነው? ምን ነገሮችንስ ሊያካትቱ ይችላሉ?
10 ለቤተሰብ አባሎችና ለቅርብ ወዳጆች። በዕለታዊ ኑሮአችን በጣም አስፈላጊ ናቸው ለምንላቸው ጉዳዮችና ሥራዎች ከፍተኛ ትኩረትና ጊዜ እንሰጣለን። ይሁን እንጂ ጊዜ ወስደን ከምንወዳቸው ዘመዶቻችንና የቅርብ ወዳጆቻችን ጋር በደብዳቤ እንጠያየቃለንን? ወላጆች ልጆቻቸው ደብዳቤ ሲጽፉላቸው በጣም ደስ ይላቸዋል። ልጆች ደግሞ ወላጆቻቸው ከሚጽፉላቸው ደብዳቤ ብዙ ጥቅም ያገኛሉ። የቤተሰብ አባሎች ተራርቀው በሚኖሩበት ጊዜ እንኳ በደብዳቤ አማካኝነት የሚደረገው “ጭውውትና የሐሳብ መለዋወጥ” በጣም ያቀራርባቸዋል። ወዳጆችህና ዘመዶችህ አሳቢነትህን የሚገልጽ ወይም የሚያስደስት ዜና የሚገልጽ ደብዳቤ ከአንተ ሲደርሳቸው በጣም ይታነጻሉ። ይህን ትጠራጠራለህን? ከተጠራጠርህ ስለ ራስህ ተሞክሮ ለአንድ አፍታ አስብ። አስደሳች ደብዳቤ የመቀበልን ያህል የሚያስደስቱ ነገሮች በጣም ጥቂት ናቸው። ተቀባዩን በደስታ ያስፈነድቃል። ስለ አንተ የሚያስብ ሰው መኖሩ ያስደስትሃል። ከዋነኞቹ የክርስቲያን ባሕርያት አንዱ እርስ በርስ መዋደዳቸው እንደሆነና ይህም ፍቅር ሊገለጽ ከሚችልባቸው መንገዶች አንዱ በቦታ ተራርቀው በሚኖሩበትም ጊዜ እንኳ በደብዳቤ መጠያየቃቸው እንደሆነ አስታውስ።
11 ይሁን እንጂ ስለምን ነገር ትጽፋለህ? አስደሳች ተሞክሮ አጋጥሞሃልን? አንተን ያስደሰተህ ነገር ሌሎችንም ሳያስደስት አይቀርም። ራስህ በአገልግሎት ያጋጠመህ ወይም ከሌሎች የሰማኸው ተሞክሮ ሊሆን ይችላል። (ይሁን እንጂ አጠራጣሪ የሆኑ ነገሮችን ለሌሎች ማስተላለፍ ጥበብ አይደለም።) ከምትጽፍለት ሰው ጋር ስላሳለፍከው አስደሳች ተሞክሮ ልታስታውሰው የምትፈልግበት ጊዜ ሊኖር ይችላል። ይህም ወዳጆች እርስ በርሳቸው እንዲቀራረቡ ያስችላል። በተጨማሪም ስለተማርከው አዳዲስ ነገሮች ልትጽፍ ትችላለህ። በቅርብ ጊዜያት ያደረግሃቸው ነገሮች ወይም የጎበኘሃቸው ቦታዎችስ? እንደነዚህ ያሉት ጉዳዮች ምንም ጊዜ ቢሆን ወዳጆቻችንን ያስደስታሉ። የምትጽፍለት ሰው ያመዋልን? የማጽናኛና የማበረታቻ መልእክት ላክለት። እንደምታስብለትና በጥቂት ጊዜ ውስጥ እንደሚሻለው ተስፋ እንደምታደርግ ግለጽለት። በተጨማሪም ታማሚው ሰው በጉባኤያችሁ ውስጥ ስለተፈጸመ አስደሳች ነገር፣ ሊያጽናናውና ቀኑን ብሩህ ሊያደርግለት ስለሚችል ነገር ጻፍለት። ስለምትጽፋቸው ነገሮች ስናነሳ በቅርቡ የተፈጸሙ ነገሮችን ወይም ስታስብ የነበረውን ነገር ማስታወስ የሚቸግርህ ከሆነ ለምን ሐሳቡ እንደመጣልህ በማስታወሻ ወረቀት ላይ አትጽፈውም? እንዲህ ካደረግህ ደብዳቤውን ለመጻፍ በምትቀመጥበት ጊዜ ሐሳቡን በቀላሉ ለማግኘት ትችላለህ።
12, 13. ደብዳቤዎቻችን ሌሎችን በእውነት መንገድ እንዲቀጥሉ ሊያበረታቱ የሚችሉት እንዴት ነው?
12 በተጨማሪም በደብዳቤህ ስለምትጽፋቸው ነገሮች ከተነሳ ደብዳቤው መሳ. 11:40) በተጨማሪም በነበሩበት ጉባኤ ውስጥ ምን ነገሮች እንደተከናወኑ በደብዳቤህ ውስጥ ብትገልጽላቸው ደስ ይሰኛሉ።
የሚደርሰውን ሰው የእውነትን መንገድ እንዲጀምር፣ ጀምሮ ከሆነም እንዲገፋበት ከማበረታታት የበለጠ ዋጋ ያለው ነገር ይኖራል ብለህ ታስባለህን? ምናልባት መጽሐፍ ቅዱስ ታስጠናው የነበረ ሰው ወደ ሌላ ከተማ ተዛውሮ ይሆናል። በግል እንደምታስብለት የሚገልጽና የሚያበረታታው ደብዳቤ ብትጽፍለት ይህ ደብዳቤህ ለእውነት ያለው ፍላጎት ሕያው ሆኖ እንዲኖር አይረዳውምን? ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ ከቤቱ ርቆ የሚኖር ልጅ ለወላጆቹ ደብዳቤ ሲጽፍና ወላጆቹ ባለፉት ዘመናት በሙሉ ለይሖዋ የታመኑ ሆነው በመኖራቸውና ልጆቻቸውን የይሖዋን መንገዶች እንዲያደንቁ አድርገው በማሳደጋቸው በጣም እንደሚያደንቃቸው ሲጽፍ ምን እንደሚሰማቸው አስቡ። በተጨማሪም ርዳታ በጣም ወደሚያስፈልግባቸው ቦታዎች የተዛወሩት ወይም የቤቴል ወይም የሚሲዮናዊነት አገልግሎት የጀመሩስ? ለይሖዋ ለሚያቀርቡት የታማኝነት አገልግሎት የሚያመሰግናቸው ደብዳቤ ቢደርሳቸው በጣም ይበረታታሉ። (13 በደብዳቤህ ውስጥ በራስህ ላይ ብቻ ትኩረት ባለማድረግ የደብዳቤህን ጥራት መጨመር ትችላለህ። ስለምትጽፍለት ሰው ደህንነት፣ ስለ እቅዶቹ፣ ከዚህ በፊት የጻፈልህ ጉዳይ ምን እንደደረሰ፣ ስለ ጋራ ወዳጆቻችሁ፣ መጽሐፍ ቅዱስን የሚያስጠናቸው ሰዎች ስላሳዩት ዕድገት በመጠየቅ እንደምታስብለት አሳይ። ይህን የመሰለው ጤናማ የሆነ የአሳቢነት መንፈስ ደብዳቤው የተጻፈለትን ሰው ከማነጹም በላይ ሌላ ደብዳቤ እንድትለዋወጡ ያነሣሣል።
14, 15. የደብዳቤህ መደምደሚያ ትርጉም ያለው እንዲሆን ምን ማድረግ ይቻላል?
14 የደብዳቤህን ሐተታ ከጨረስክ በኋላ እንዴት ትደመድመዋለህ? ትርጉም ያለው መደምደሚያ አስፈላጊ ነው። “ቦታ ስላልበቃኝ እዚህ ላይ ለማቆም ተገድጃለሁ” ብሎ መደምደም በደብዳቤው ጸሐፊ ላይ ጥሩ ግምት አያሳድርም። ከዚህ የበለጠ ትርጉም ስለሚሰጥ መደምደሚያ አስቡ። ሐዋርያው ጳውሎስ ደብዳቤዎቹን በተለያዩ ጥሩ መንገዶች ደምድሟል። ለምሳሌ ያህል “ወንድሞች ሆይ፣ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከመንፈሳችሁ ጋር ይሁን” በማለት ደምድሟል። (ገላ. 6:18፤ 2 ቆሮ. 13:14) ሐዋርያው ዮሐንስ ከደብዳቤዎቹ አንዱን እንደሚከተለው በማለት ደምድሟል። “ሰላም ለአንተ ይሁን። ወዳጆች ሰላምታ ያቀርቡልሃል። ወዳጆችን በየስማቸው እየጠራህ ሰላምታ አቅርብልኝ።” (3 ዮሐ. 14 በአማርኛው መጽሐፍ ቅዱስ ቁጥር 15) ከደብዳቤህ ርዕሰ ጉዳይና ደብዳቤውን ከምትጽፍለት ግለሰብ ጋር ካላችሁ ዝምድና ጋር በሚስማማ መደምደሚያ ተጠቀም።
15 በየዕለቱ በአካባቢህ የሚፈጸሙትን ነገሮች በትኩረት ብትከታተል ደብዳቤ መጻፍ አስቸጋሪ አይሆንብህም። የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች ፍጻሜ የሚሆኑ ብዙ ነገሮች በአካባቢያችን ይከናወናሉ። ይህ አሮጌ ሥርዓት ሃይማኖታዊ ክፍሎቹን ጨምሮ በፍጥነት በመፈራረስ ላይ
ይገኛል። የይሖዋ ሥራ ግን የይሖዋ በረከት ስላለው በአስደናቂ ሁኔታ በመስፋፋት ላይ ይገኛል። ወንድሞችህ በአካባቢህ በመከናወን ላይ ስለሚገኘው ቲኦክራሲያዊ ዕድገት ሲሰሙ በጣም ደስ ይላቸዋል። ምንም ዓይነት ሰው ብትሆን የአንተ ሞቅ ያለና ግላዊ አሳቢነት የተገለጸበት ደብዳቤ ቢደርሳቸው ደስ የሚሰኙ ሰዎች ይኖራሉ። ይህን የመሰለውን ለሌሎች የማሰብ ባሕርይ ማሳየት ደግሞ የአገልግሎታችን ክፍል ነው፤ ምክንያቱም የወንድማማች ፍቅራችን በቦታ ስለተራራቅን ብቻ መቋረጥ አይኖርበትም። ደብዳቤ በመጻጻፍ ሊጠናከር ይችላል።[የአንቀጾቹ ጥያቄዎች]