ለተሰሎንቄ ሰዎች የተጻፈ የመጀመሪያው ደብዳቤ 1:1-10
1 ከጳውሎስ፣ ከስልዋኖስና*+ ከጢሞቴዎስ፤+ አባት ከሆነው አምላክና ከጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር አንድነት ላለው የተሰሎንቄ ሰዎች ጉባኤ፦
የአምላክ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።
2 ሁላችሁንም በጸሎታችን+ በጠቀስን ቁጥር ሁልጊዜ አምላክን እናመሰግናለን፤
3 የእምነት ሥራችሁን፣ ከፍቅር የመነጨ ድካማችሁንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ተስፋ በማድረጋችሁ+ የተነሳ የምታሳዩትን ጽናት በአምላካችንና በአባታችን ፊት ዘወትር እናስባለን።
4 አምላክ የሚወዳችሁ ወንድሞች፣ እሱ እንደመረጣችሁ እናውቃለን፤
5 ምክንያቱም የሰበክንላችሁ ምሥራች ወደ እናንተ የመጣው በቃል ብቻ ሳይሆን በኃይልና በመንፈስ ቅዱስ እንዲሁም በጠንካራ እምነት ነው። ደግሞም ለእናንተ ስንል በመካከላችሁ ምን ዓይነት ሰዎች ሆነን እንደኖርን ታውቃላችሁ።
6 ብዙ መከራ ቢደርስባችሁም+ ቃሉን ከመንፈስ ቅዱስ በሚገኝ ደስታ ስለተቀበላችሁ የእኛንም+ ሆነ የጌታን+ አርዓያ ተከትላችኋል፤
7 በመሆኑም በመቄዶንያና በአካይያ ለሚገኙ አማኞች ሁሉ ምሳሌ ሆናችኋል።
8 የይሖዋ* ቃል ከእናንተ ወጥቶ የተሰማው በመቄዶንያና በአካይያ ብቻ አይደለም፤ ከዚህ ይልቅ በአምላክ ላይ ያላችሁ እምነት በሌሎች ቦታዎችም ሁሉ ተሰራጭቷል፤+ ስለዚህ እኛ ምንም መናገር አያስፈልገንም።
9 ምክንያቱም መጀመሪያ ከእናንተ ጋር እንዴት እንደተገናኘን እንዲሁም ሕያው የሆነውንና እውነተኛውን አምላክ ለማገልገል ጣዖቶቻችሁን በመተው+ እንዴት ወደ አምላክ እንደተመለሳችሁ እነሱ ራሳቸው ሁልጊዜ ይናገራሉ፤
10 በተጨማሪም ወደ አምላክ የተመለሳችሁት ከሞት ያስነሳውንና ከሚመጣው ቁጣ+ የሚታደገንን የልጁን ይኸውም የኢየሱስን ከሰማይ መምጣት ለመጠባበቅ ነው።+