በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

የይሖዋ ምሥክሮች በኢየሱስ ያምናሉ?

የይሖዋ ምሥክሮች በኢየሱስ ያምናሉ?

 በሚገባ። በኢየሱስ እናምናለን፤ እንዲያውም እሱ ራሱ እንዲህ ብሏል፦ “እኔ መንገድ፣ እውነትና ሕይወት ነኝ። በእኔ በኩል ካልሆነ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።” (ዮሐንስ 14:6) ኢየሱስ ወደ ምድር የመጣው ከሰማይ እንደሆነና ፍጹም ሕይወቱን ቤዛዊ መሥዋዕት አድርጎ መስጠቱን እናምናለን። (ማቴዎስ 20:28) መሞቱና ከሞት መነሳቱ በእሱ እንደሚያምኑ በተግባር ለሚያሳዩ ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲያገኙ በር ከፍቷል። (ዮሐንስ 3:16) በተጨማሪም ኢየሱስ በአሁኑ ጊዜ በሰማይ የሚገኘው የአምላክ መንግሥት ንጉሥ ሆኖ በመግዛት ላይ እንዳለና ይህ መንግሥት በቅርቡ በመላው ምድር ላይ ሰላም እንዲሰፍን የሚያደርግ መሆኑን እናምናለን። (ራእይ 11:15) ይሁንና ለኢየሱስ የምንሰጠው ቦታ እሱ ራሱ “አብ ከእኔ ይበልጣል” ያለውን መሠረት ያደረገ ነው። (ዮሐንስ 14:28) በመሆኑም ኢየሱስ ሁሉን ቻይ አምላክ እንደሆነ ስለማናምን ለእሱ አምልኮ አናቀርብም።