ጥቅምት 18, 2024 | የታደሰው፦ ነሐሴ 4, 2025
ሩሲያ
ወቅታዊ መረጃ—እህት ተፈረደባት | ‘ይሖዋ ይክሰኛል’
ሐምሌ 31, 2025 በክራስኖዳር ግዛት የሚገኘው የቭይሴልኮቭስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት፣ እህት ቫሲሊና ፕዬንስካያ ጥፋተኛ ናት በማለት የሁለት ዓመት የገደብ እስራት በይኖባታል። አሁን ወህኒ ቤት አትገባም።
አጭር መግለጫ
ይሖዋ፣ ስደትን እየተጋፈጠ ያለ እያንዳንዱን አገልጋዩን እንደሚመለከተውና ‘ሥራው ወሮታ እንዳለው’ እንደሚያረጋግጥለት በማወቃችን አመስጋኞች ነን።—ኤርምያስ 31:16
የክሱ ሂደት
የካቲት 13, 2022
ቤቷ ተፈተሸ
ግንቦት 23, 2023
የክስ ፋይል ተከፈተባት። የተወነጀለችው ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ከሌሎች ጋር በመወያየቷና የይሖዋ ምሥክሮች በሚያደርጓቸው ሰላማዊ ሃይማኖታዊ ስብሰባዎች ላይ በመሳተፏ ነው። የባንክ ሒሳቧ ታገደ
ሐምሌ 18, 2023
የጉዞ ገደብ ተጣለባት
ጥር 31, 2024
ክሷ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ

