ዓለም አቀፋዊ ዜና

ቪክቶር ስታሺቭስኪ ከመጋቢት 2021 አንስቶ ክራይሚያ ውስጥ ታስሯል

በእምነታቸው ምክንያት የታሰሩ የይሖዋ ምሥክሮች—በአገር

በእምነታቸው ምክንያት የታሰሩ የይሖዋ ምሥክሮች—በአገር

እስከ ሚያዝያ 2026 ባለን መረጃ መሠረት በዓለም ዙሪያ ከ279 በላይ የይሖዋ ምሥክሮች በእምነታቸው ምክንያት ታስረዋል።

በዓለም አቀፍ የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ስምምነት ላይ አንቀጽ 18 የማሰብ፣ የሕሊና እና የሃይማኖት ነፃነትን ይደነግጋል። ይሁንና በአንዳንድ አገሮች ውስጥ የይሖዋ ምሥክሮች ይህን መብት ተነፍገዋል፤ በሃይማኖታዊ እንቅስቃሴዎች በመሳተፋቸው ወይም በሕሊናቸው ምክንያት ወታደራዊ አገልግሎት ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው የተነሳ ያለአግባብ እየታሰሩና እንግልት እየደረሰባቸው ነው።

“በእስር ላይ ያሉትን ከእነሱ ጋር ታስራችሁ እንዳላችሁ አድርጋችሁ በማሰብ ሁልጊዜ አስታውሷቸው።”—ዕብራውያን 13:3