በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር | በአገልግሎት የምታገኙትን ደስታ አሳድጉ

ለምርምር የሚረዱ መሣሪያዎችን መጠቀም

ለምርምር የሚረዱ መሣሪያዎችን መጠቀም

ይሖዋ፣ ውጤታማ በሆነ መንገድ ለማስተማር የሚያግዙ መሣሪያዎች ሰጥቶናል፤ ለምሳሌ ቪዲዮዎች፣ ትራክቶች፣ መጽሔቶች፣ ብሮሹሮች፣ መጻሕፍትና ዋና መሣሪያችን መጽሐፍ ቅዱስ አሉን። (2ጢሞ 3:16) ጥቅሶችን ለማብራራት የሚረዱን ምርምር ለማድረግ የሚያስችሉ መሣሪያዎችም ሰጥቶናል። ከእነዚህ መካከል ዎችታወር ላይብረሪ (እንግሊዝኛ)፣ JW ላይብረሪ አፕሊኬሽን፣ የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት እና የምርምር መርጃ መሣሪያ ለይሖዋ ምሥክሮች ይገኙበታል።

ሰፊ መረጃ በያዙት በእነዚህ መሣሪያዎች ተጠቅማችሁ መንፈሳዊ ዕንቁዎች ለማግኘት የምታደርጉት ምርምር ደስታ ያስገኝላችኋል። ጥናቶቻችሁን የእነዚህን መሣሪያዎች አጠቃቀም አሠልጥኗቸው። እነዚህን መሣሪያዎች ተጠቅመው በአእምሯቸው ውስጥ ለሚፈጠሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎች በራሳቸው መልስ ሲያገኙ እነሱም ደስታቸው ይጨምራል።

ደቀ መዛሙርት የማድረጉ ሥራ የሚያስገኘውን ደስታ አጣጥሙ—የይሖዋን እርዳታ ተቀበሉ—ለምርምር የሚረዱ መሣሪያዎችን መጠቀም የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • ጄድ ፍጥረትን በተመለከተ ምን የመከራከሪያ ሐሳብ አንስታለች?

  • ኒታ ይህን ርዕሰ ጉዳይ በተመለከተ መረጃ ያገኘችው ከየት ነው?

  • መንፈሳዊ ውድ ሀብቶችን ምርምር አድርጎ ማግኘትና ያን ለሌሎች ማካፈል ደስታ ያስገኛል

    ለጄድ ይበልጥ ጠቃሚ የሆኑትን ነጥቦች ለይታ ማውጣት የቻለችው እንዴት ነው?

  • ኒታ ለምርምር የሚረዱ መሣሪያዎችን መጠቀሟ በእሷ ላይ ምን ስሜት አሳድሯል?