በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 135

የይሖዋ ፍቅራዊ ግብዣ፦ ‘ልጄ ሆይ፣ ጥበበኛ ሁን’

የይሖዋ ፍቅራዊ ግብዣ፦ ‘ልጄ ሆይ፣ ጥበበኛ ሁን’

(ምሳሌ 27:11)

  1. 1. እናንተ ወጣቶች

    ስጡኝ ልባችሁን።

    የሚሰድበኝ ጠላት

    አፍሮ ይድፋ ’ንገቱን።

    ሕይወታችሁን ብትሰጡኝ

    በምርጫችሁ፣

    ያኔ ያውቃል ዓለም

    የኔ ’ንደሆናችሁ።

    (አዝማች)

    ወንዶችና ሴቶች ልጆቼ፣

    ጠቢብ ሁኑ አስደስቱኝ።

    ሙሉ ልባችሁንም ስጡኝ፤

    በምርጫችሁ አወድሱኝ።

  2. 2. ምርጣችሁን ስትሰጡኝ

    ደስ ይበላችሁ፤

    ብትወድቁ እንኳ

    አለሁ ከጎናችሁ፣

    ማንም ቢተዋችሁ

    ወይም ቢከዳችሁ፣

    መቼም ቢሆን አልጥላችሁም

    አይዟችሁ።

    (አዝማች)

    ወንዶችና ሴቶች ልጆቼ፣

    ጠቢብ ሁኑ አስደስቱኝ።

    ሙሉ ልባችሁንም ስጡኝ፤

    በምርጫችሁ አወድሱኝ።

(በተጨማሪም ዘዳ. 6:5⁠ን፣ መክ. 11:9⁠ን እና ኢሳ. 41:13⁠ን ተመልከት።)