በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 123

ለቲኦክራሲያዊ ሥርዓት በታማኝነት መገዛት

ለቲኦክራሲያዊ ሥርዓት በታማኝነት መገዛት

(1 ቆሮንቶስ 14:33)

  1. 1. የይሖዋ ሕዝቦች ስለሚሰብኩ

    የመንግሥቱን እውነት ለሰዎች ሁሉ፣

    ይኖርባቸዋል በኅብረት መሥራት፤

    ለቲኦክራሲያዊው ሥርዓት መገዛት።

    (አዝማች)

    በታማኝነት እንገዛለት፤

    አለብን ውለታ።

    ፍቅሩ፣ ጥበቃው አይለየንም፤

    ታማኝ እንሁን ለጌታ።

  2. 2. በክርስቲያናዊ ጉዞ ’ሚመሩን

    ታማኝ መጋቢና መንፈሱን ሰጠን።

    ስለዚህ እንጽና፤ አምላክ ይደሰት፤

    ታማኝ ሆነን ’ናውጅ የሱን ት’ዛዛት።

    (አዝማች)

    በታማኝነት እንገዛለት፤

    አለብን ውለታ።

    ፍቅሩ፣ ጥበቃው አይለየንም፤

    ታማኝ እንሁን ለጌታ።

(በተጨማሪም ሉቃስ 12:42⁠ን እና ዕብ. 13:7, 17⁠ን ተመልከት።)