በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የክርስቶስ መምጣት ሊያስፈራን ይገባል?

የክርስቶስ መምጣት ሊያስፈራን ይገባል?

የክርስቶስ መምጣት ሊያስፈራን ይገባል?

ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ መምጣት ስታስብ በዓይነ ሕሊናህ የሚታይህ ምንድን ነው? እልቂት፣ ጥፋትና በሰው ልጆች ላይ የሚደርስ የቅጣት ፍርድ ነው? ወይስ ችግሮቻችንን ሁሉ ያስወግድልናል ብለህ ትጠብቃለህ? የክርስቶስ መምጣት ሊያስፈራን ይገባል? ወይስ በጉጉት የምንጠባበቀው ነገር መሆን አለበት?

መጽሐፍ ቅዱስ የክርስቶስን መምጣት አስመልክቶ “እነሆ፤ በደመና ይመጣል፤ . . . ዐይን ሁሉ ያየዋል፤ የምድርም ሕዝቦች ሁሉ ከእርሱ የተነሣ ዋይ ዋይ ይላሉ” ይላል። (ራእይ 1:7) ይህ መምጣት፣ ኢየሱስ ጻድቃንን ለመባረክና ክፉ ሰዎችን ለመቅጣት ወደፊት በሚገለጥበት ጊዜ የሚኖረውን ሁኔታ ያመለክታል።

ሐዋርያው ዮሐንስ የክርስቶስን መምጣት ከመፍራት ይልቅ በጉጉት ይጠባበቅ ነበር። ዮሐንስ ስለ ክርስቶስ መምጣትና በምድር ላይ ስለሚያስከትለው ውጤት በራእይ ከተመለከተ በኋላ “ጌታ ኢየሱስ ሆይ፤ ና” ሲል ከልብ በመነጨ ስሜት ጸልዮአል። (ራእይ 22:20) ታዲያ ‘የምድር ሕዝቦች ሁሉ ከእርሱ የተነሣ ዋይ ዋይ የሚሉት’ ለምንድን ነው? “ዐይን ሁሉ” የሚያየውስ በምን መንገድ ነው? የክርስቶስ መምጣት ምን ያከናውናል? በክርስቶስ መምጣት ላይ እምነት ማሳደራችን የሚጠቅመን እንዴት ነው? የሚቀጥለው ርዕስ ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል።