በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ወንድና ሴት—አንዳቸው ለሌላው ተፈጥረዋል

ወንድና ሴት—አንዳቸው ለሌላው ተፈጥረዋል

ወንድና ሴት—አንዳቸው ለሌላው ተፈጥረዋል

ወንድና ሴት ሁልጊዜም አብረው የመሆን ከፍተኛ ፍላጎት አላቸው። ይህን ፍላጎት የሰጣቸው አምላክ ነው። ይሖዋ፣ የመጀመሪያው ሰው አዳም ብቻውን መሆኑ መልካም እንዳልሆነ ተመልክቶ ለአዳም “የሚስማማውን [“ማሟያ የምትሆንለትን፣” NW] ረዳት” ፈጠረለት።

ይሖዋ፣ አዳም ከባድ እንቅልፍ እንዲወስደው ካደረገ በኋላ ከጎድኑ ላይ አንድ አጥንት ወሰደ። ከዚያም “የወሰዳትን ዐጥንት ሴት አድርጎ ሠራት፤ ወደ አዳምም አመጣት።” አዳም ውብ በሆነችው የይሖዋ ፍጥረት በጣም ስለተደሰተ “ይህች ዐጥንት ከዐጥንቴ፣ ሥጋም ከሥጋዬ ናት” አለ። የሴትነት ባሕርይ ያላትና ፍጹም የሆነችው ሔዋን በእርግጥም የምትወደድ ነበረች። ግርማ ሞገስ ያለውና የወንድነት ባሕርይ የሚታይበት ፍጹሙ አዳምም አክብሮት ይገባው ነበር። አንዳቸው ለሌላው የተፈጠሩ ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ “ስለዚህ ሰው ከአባቱና ከእናቱ ተለይቶ ከሚስቱ ጋር ይጣመራል፤ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ” ይላል።—ዘፍጥረት 2:18-24

ይሁንና በዛሬው ጊዜ ቤተሰቦች እየፈራረሱ ናቸው። በተጨማሪም በወንድና በሴት መካከል ያለው ግንኙነት በአብዛኛው የተመሠረተው በራስ ወዳድነት ላይ ሲሆን አንዳቸው በሌላው ላይ አካላዊና ስሜታዊ ጥቃት ሲሰነዝሩ ይታያል። በሁለቱ ጾታዎች መካከል ያለው የፉክክር መንፈስ ላለመግባባት አስተዋጽኦ አድርጓል። ይህ ሁሉ አምላክ ለወንድና ለሴት ካለው ዓላማ ጋር የሚጋጭ ነው። ወንድ የተፈጠረው በምድር ላይ ልዩ ኃላፊነት እንዲያከናውን ተደርጎ ሲሆን ሴት ደግሞ ከእርሱ ጎን የመሰለፍ ልዩና ክብራማ ቦታ ተሰጥቷታል። በመሆኑም ተስማምተው መሥራት ነበረባቸው። የሰው ልጅ ከተፈጠረበት ጊዜ አንስቶ የነበሩ ፈሪሃ አምላክ ያላቸው ወንዶችና ሴቶች ከይሖዋ የተቀበሉትን ኃላፊነት በታማኝነት ለመወጣት ሲጥሩ ቆይተዋል። ይህም እርካታና ደስታ አምጥቶላቸዋል። አምላክ ለወንድና ለሴት የሰጠው ቦታ ምንድን ነው? እኛስ በተሰጠን ቦታ ኃላፊነታችንን መወጣት የምንችለው እንዴት ነው?

[በገጽ 3 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

ወንድና ሴት በአምላክ ዓላማ ውስጥ የተከበረ ቦታ ተሰጥቷቸዋል