ንቁ! ሰኔ 2014 | ጥሩ ጓደኛ የሚባለው ምን ዓይነት ሰው ነው?

የሚያሳዝነው ብዙ ሰዎች እውነተኛ ጓደኛ የላቸውም። ይሁንና እውነተኛ ጓደኛ ማግኘት ይቻላል? ዘላቂ ጓደኝነት ለመመሥረት ምን ያስፈልጋል? መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠውን ጠቃሚ ምክር ተመልከት።

ከዓለም አካባቢ

ከርዕሰ ጉዳዮቹ መካከል፦ በካናዳ ያሉ የሥነ ተዋልዶ ጤና ክሊኒኮች ያጋጠማቸው ግራ የሚያጋባ ሁኔታ፣ ሥጋን የሚተካ ለየት ያለ አማራጭ መገኘቱ እና በአየርላንድ አምላክ የለሽ የሆኑ ሰዎችን ለማጋባት የተደረገ አዲስ ዝግጅት።

የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ

ጥሩ ጓደኛ የሚባለው ምን ዓይነት ሰው ነው?

ብዙ ሰዎች ጥሩ ጓደኛ ማግኘት አስፈላጊ እንደሆነ ያምናሉ። ጥሩ ጓደኛ መሆን የምትችለው እንዴት ነው? ይህ ርዕስ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙ አራት መመሪያዎችን ያብራራል።

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

ሞት

ስንሞት ምን እንሆናለን? በሞት የተለዩንን የቤተሰባችንን አባላት በድጋሚ ማግኘት እንችላለን? መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ሞት ለሚነሱ ጥያቄዎች የሚያጽናና መልስ ይሰጣል።

የታሪክ መስኮት

ጆሴፍ ፕሪስትሊ

ጆሴፍ ፕሪስትሊ ለእውነትና ለሐቅ ለመቆም ሲል መሠረት የሌላቸው ጽንሰ ሐሳቦችንና ሲወርድ ሲዋረድ የመጡ ወጎችን ይቃወም ነበር። ግኝቶቹና የሥነ ጽሑፍ ሥራዎቹ በሰዎች አስተሳሰብ ላይ ተጽዕኖ ያሳደሩት እንዴት እንደሆነ አንብብ።

የድድ በሽታ—አንተን ያሰጋህ ይሆን?

የድድ በሽታ በዓለም ላይ ካሉ በጣም የተለመዱ የአፍ በሽታዎች አንዱ ነው። መንስኤው ምንድን ነው? በሽታው እንዳለብህ ማወቅ የምትችለው እንዴት ነው? በዚህ በሽታ የመያዝ አጋጣሚህን መቀነስ የምትችለው እንዴት ነው?

ለቤተሰብ

ወጪን መቆጣጠር

ወጪያችሁን መቆጣጠር መጀመር ያለባችሁ ገንዘብ ሲያልቅባችሁ አይደለም። ታዲያ ይህን ማድረግ የምትችሉት እንዴት ነው?

ንድፍ አውጪ አለው?

እበት ለቃሚው ጥንዚዛ ያለው አቅጣጫ የማወቅ ችሎታ

እበት ለቃሚ ጥንዚዛ አቅጣጫ የሚያውቀው እንዴት ነው? ሰዎች ከዚህ ጥንዚዛ ምን ሊማሩ ይችላሉ?

በተጨማሪም . . .

ወጣቶች ስለ ሞባይል ስልክ ምን ይላሉ?

ብዙ ወጣቶች ያለ ሞባይል ስልክ መኖር እንደማይችሉ ይሰማቸዋል። ሞባይል ስልክ ምን ጥቅሞችና ጉዳቶች አሉት?

ሙሴ በግብፅ አደገ

ሙሴ በልጅነቱ በግብፅ ካሳለፈው ሕይወት ምን እንማራለን? እነዚህን መልመጃዎች በማውረድ በቤተሰብ ተወያዩባቸው።