በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ሐቀኝነት ጠፍቷል!

ሐቀኝነት ጠፍቷል!

ሐቀኝነት ጠፍቷል!

ዳኒ * በሆንግ ኮንግ በሚገኝ አንድ ትልቅ የንግድ ኩባንያ ውስጥ ተቀጥሮ ይሠራል። ለኩባንያቸው ዕቃ አቅራቢ መሆን የሚችልን ፋብሪካ በሚጎበኝበት ጊዜ ፋብሪካው፣ ኩባንያቸው የሚፈልገውን የጥራት ደረጃ ማሟላት መቻሉ እንደሚያጠራጥረው ገለጸ። በኋላ ላይ ከፋብሪካው ሥራ አስኪያጅ ጋር አብረው እየተመገቡ ሳለ ግለሰቡ ለዳኒ አንድ ፖስታ ሰጠው። በፖስታው ውስጥ በአሥር ሺዎች የሚቆጠር የአሜሪካ ዶላር ነበር፤ የፋብሪካው ባለቤት የሰጠው ጉቦ ከዳኒ የዓመት ገቢ ጋር የሚመጣጠን ነበር።

● ዳኒ ያጋጠመው ነገር በጣም የተለመደ ነው። በመላው ዓለም በየትኛውም መስክ ማጭበርበር እንደ ወረርሽኝ ተዛምቷል። ለምሳሌ ያህል፣ ከ2001 እስከ 2007 ባሉት ዓመታት ውስጥ አንድ ትልቅ የጀርመን ድርጅት ኮንትራቶችን ለመውሰድ ሲል 1.4 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በጉቦ መልክ እንደከፈለ የፍርድ ቤት መዝገቦች ያሳያሉ።

በቅርቡ ትላልቅ ድርጅቶች ከማጭበርበር ጋር በተያያዘ ቅሌት ውስጥ በመውደቃቸው አንዳንድ ማሻሻያዎች ቢደረጉም በጥቅሉ ሲታይ ግን ሁኔታው እየተባባሰ ይመስላል። ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል የተባለው ድርጅት በ2010 ያደረገው ጥናት እንዳሳየው በመላው ዓለም “ባለፉት ሦስት ዓመታት ውስጥ ሙስና ጨምሯል።”

ሐቀኝነት የጠፋው ለምንድን ነው? ሐቀኛ መሆን የሚቻል ነገር ነው? ከሆነስ እንዴት? በዚህ ረገድ መጽሐፍ ቅዱስ ሊረዳን ይችላል?

[የግርጌ ማስታወሻ]

^ አን.2 በእነዚህ ተከታታይ ርዕሶች ውስጥ የተጠቀሱት አንዳንዶቹ ስሞች ተቀይረዋል።