በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

በአነስተኛ ገቢ መኖር የምትችለው እንዴት ነው?

በአነስተኛ ገቢ መኖር የምትችለው እንዴት ነው?

በአነስተኛ ገቢ መኖር የምትችለው እንዴት ነው?

አነስተኛ ገቢ ለመኖር የታሰበበት ዕቅድ ማውጣት ይጠይቃል። ኢየሱስ የዚህን አስፈላጊነት ጎላ አድርጎ ገልጿል። “ከእናንተ መካከል፣ ግንብ ለመገንባት ፈልጎ ለመጨረስ የሚያስችል በቂ ገንዘብ እንዳለው ለማወቅ በመጀመሪያ ተቀምጦ ወጪውን የማያሰላ ማን ነው?” በማለት ጠይቆ ነበር። (ሉቃስ 14:28, 29) እናንተም ባጀት በማውጣት ይህን መሠረታዊ ሥርዓት ተግባራዊ ካደረጋችሁ ኑሯችሁ ገቢያችሁን ያገናዘበ እንዲሆን ‘ወጪያችሁን ማስላት’ ትችላላችሁ። እንዲህ ማድረግ የምትችሉት እንዴት ነው? እስቲ የሚከተለውን ሞክሩ፦

ደሞዝ ስትቀበሉ አሁንም ሆነ ወደፊት ለምታወጡት ለእያንዳንዱ ወጪ ምን ያህል ገንዘብ ማስቀመጥ እንዳለባችሁ ወስኑ። ( በገጽ 8 ያለውን ሣጥን ተመልከቱ።) ወጪዎቻችሁን ለይታችሁ ካወቃችሁ ገንዘባችሁን ምን ላይ እንደምታውሉት እንዲሁም አስፈላጊ ላልሆኑ ነገሮች ምን ያህል እንደምታወጡ ማወቅ ትችላላችሁ። ይህ ደግሞ የትኛውን ወጪ መቀነስ እንደምትችሉ ለይታችሁ እንድታውቁ ይረዳችኋል።

ለእናንተ የሚሆን ባጀት ለማዘጋጀት የሚከተሉትን ሐሳቦች ተግባራዊ አድርጉ፦

ዕቃ ስትገዙ ዘዴኞች ሁኑ

ራውል ከሥራ ሲፈናቀል ባለቤቱ በርታ ዕቃ የምትሸምትበትን ዘዴ ቀየረች። “ቅናሽ ዋጋ ለማግኘት ስል ኩፖኖችን እጠቀም እንዲሁም ዕቃዎች በቅናሽ የሚሸጡበት ቦታ ሄጄ እገዛ ነበር” በማለት ተናግራለች። ከዚህ በታች አንዳንድ ጠቃሚ ሐሳቦች ቀርበዋል፦

በሳምንቱ ውስጥ የምታዘጋጇቸው የምግብ ዓይነቶች በወቅቱ በርካሽ ዋጋ በሚገኙ ሸቀጦች ላይ የተመሠረቱ እንዲሆኑ አድርጉ።

የተዘጋጁ ምግቦችን ከመግዛት ይልቅ ራሳችሁ አዘጋጁ።

አንዳንድ ዕቃዎች ርካሽ በሚሆኑበት አሊያም እንደልብ በሚገኙበት ጊዜ በርከት አድርጋችሁ ግዙ።

ዕቃዎችን በጅምላ ግዙ፤ ይሁን እንጂ ሲቆዩ የሚበላሹ ነገሮችን በብዛት እንዳትገዙ ተጠንቀቁ።

የተለበሱ ልብሶች ከሚሸጡባቸው ቦታዎች ጥራት ያላቸው ልብሶችን በመግዛት ለልብስ የምታወጡትን ወጪ ቀንሱ።

የመጓጓዣው ወጪ የሚያዋጣ ከሆነ በአነስተኛ ዋጋ ወደሚሸጥባቸው ቦታዎች ሄዳችሁ ግዙ።

ገበያ የምትወጡበትን ጊዜ ቀንሱ። *

በወረቀት ላይ አስፍሩት

ፍሬድ “ባጀት ማውጣት ያስፈልገን ስለነበር ወዲያው መከፈል ያለባቸውን ነገሮችና በወር ውስጥ በእጃችን ሊኖር የሚገባውን ገንዘብ መዘገብኩ” በማለት ይናገራል። ባለቤቱ አዴሌ እንዲህ ብላለች፦ “ገበያ ስወጣ ምን ያህል ገንዘብ ማውጣት እንዳለብኝ በትክክል አውቅ ነበር። አንዳንድ ጊዜ ለልጆቹ ወይም ለቤት የሚሆን ነገር መግዛት ሲያስፈልገኝ ያወጣነውን ባጀት እመለከትና ‘አሁን ልገዛው አልችልም፤ ስለዚህ እስከሚቀጥለው ወር ድረስ መጠበቅ አለብን’ ብዬ አስባለሁ። የረዳን ነገር ባጀታችንን በጽሑፍ ማስፈራችን ነው!”

ከመግዛታችሁ በፊት አስቡ

ራሳችሁን እንዲህ እያላችሁ የመጠየቅ ልማድ ይኑራችሁ፦ ‘ይህ በእርግጥ ያስፈልገኛል? የበፊቱ ዕቃ በእርግጥ አርጅቶ ነው? ወይስ አዲስ ስለፈለግሁ ነው?’ አንድን ዕቃ የምትገለገሉበት አልፎ አልፎ ከሆነ ከመግዛት ይልቅ መከራየት ይሻል ይሆን? ወይም ደግሞ አዘውትራችሁ ልትጠቀሙበት የምታስቡት ከሆነ በጥሩ ይዞታ ላይ የሚገኝ ያገለገለ ዕቃ መግዛቱ ይሻል ይሆን?

ከላይ የተጠቀሱት አንዳንዶቹ ምክሮች ያን ያህል ለውጥ የማያመጡ ቢመስሉም ትልቅ ልዩነት ሊያመጡ ይችላሉ! ቁም ነገሩ በትንንሽ ነገሮች የመቆጠብ ልማድ ካዳበራችሁ ትላልቅ ወጪዎች ሲያጋጥሟችሁም ተመሳሳይ ነገር ማድረጋችሁ ነው።

ቆጣቢ ሁኑ

አስፈላጊ ላልሆኑ ነገሮች የሚወጣውን ወጪ ለመቀነስ ብልሃት ፍጠሩ። ለምሳሌ አዴሌ እንዲህ ብላለች፦ “ሁለት መኪና የነበረን ቢሆንም አንዱን ትተን ሁላችንም በአንድ መኪና መጠቀም ጀመርን፤ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ከሌሎች ጋር ተዳብለን እንሄዳለን። ነዳጅ ለመቆጠብ ስንል በአንድ አካባቢ ልንፈጽማቸው የምንችላቸውን ነገሮች በሙሉ እዚያው ለመጨረስ እቅድ አወጣን። ለሚያስፈልጉን ነገሮች ብቻ ገንዘብ ለማውጣት ቁርጥ ውሳኔ አደረግን።” ቆጣቢ መሆን የምትችሉባቸው አንዳንድ መንገዶች ከዚህ ቀጥሎ ቀርበዋል፦

የጓሮ አትክልት ይኑራችሁ።

ቤት ውስጥ የምትጠቀሙባቸው መሣሪያዎች ዕድሜያቸው እንዲረዝም ፋብሪካው ስለ ጥገናና አጠቃቀም ያዘጋጀውን መመሪያ ተከተሉ።

ጥሩ የሆኑ ልብሶቻችሁን ቤት እንደገባችሁ ቀይሩ፤ እንዲህ ያለ ልማድ ማዳበራችሁ ልብሳችሁ ቶሎ እንዳያረጅ ይረዳችኋል።

ራሳችሁን አታግልሉ!

ከሥራ የተፈናቀሉ ብዙ ሰዎች ከሌሎች በመሸሽ ራሳቸውን ያገልላሉ። ፍሬድ ግን እንዲህ አላደረገም! ትልልቅ ልጆቹን ጨምሮ ቤተሰቡ ከፍተኛ ድጋፍ አድርገውለታል። “እርስ በርስ የመረዳዳትን ጥቅም የተማርን ሲሆን ይህ ደግሞ ይበልጥ እንድንቀራረብ አድርጎናል። ሁላችንም ችግሩ የጋራ እንደሆነ ተሰምቶን ነበር” በማለት ተናግሯል።

በተጨማሪም ፍሬድ በይሖዋ ምሥክሮች የመንግሥት አዳራሽ ዘወትር በሚገኝበት ጊዜ አብረውት ከሚሰበሰቡት የእምነት አጋሮቹ ብርታት አግኝቷል። ፍሬድ እንዲህ ብሏል፦ “ሁልጊዜ ክርስቲያናዊ ስብሰባዎቻችን ሲያበቁ ማበረታቻ እንዳገኘሁ ይሰማኝ ነበር። ሁሉም ሰው ደግና አሳቢ ነው። ከእነሱ እርዳታና ማጽናኛ በማግኘታችን የሚያስቡልን ሰዎች እንዳሉ ተገንዝበናል።”—ዮሐንስ 13:35

እምነት ያለው ጥቅም

በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ከሥራ መፈናቀላቸው ልባቸው በምሬት እንዲሞላና አሠሪዎቻቸው እንደከዷቸው እንዲሰማቸው አድርጓል። ቀደም ሲል የተጠቀሰው ራውል ሁለት ጊዜ ማለትም አንዴ በትውልድ አገሩ በፔሩ በኋላ ደግሞ በኒው ዮርክ ሲቲ በድንገት ከሥራ በመፈናቀሉ ቅስሙ ተሰብሮ ነበር። ራውል ለሁለተኛ ጊዜ ከሥራ ሲባረር “ዛሬ ባለው ዓለም ውስጥ አስተማማኝ የሆነ ምንም ነገር የለም” የሚል መደምደሚያ ላይ ደረሰ። ከዚያም ሥራ ለማግኘት ያደረገው ጥረት ሳይሳካለት ወራት እየተቆጠሩ ሄዱ። ራውል ይህን ሁኔታ ሊቋቋም የቻለው እንዴት ነው? “ከአምላክ ጋር የተቀራረበ ዝምድና መመሥረት የቻልኩ ከመሆኑም ሌላ ሕይወቴ አስተማማኝ እንዲሆን በእሱ ላይ መታመን እንደሚያስፈልገኝ ተገነዘብኩ” በማለት ተናግሯል።

ራውል የይሖዋ ምሥክር በመሆኑ የሚያደርገው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት “ፈጽሞ አልተውህም፣ በምንም ዓይነት አልጥልህም” በማለት ቃል በገባውና በሰማይ በሚኖረው አሳቢ አባት ላይ ጽኑ እምነት እንዲያሳድር ረድቶታል። (ዕብራውያን 13:5) ይህ ሲባል ሁኔታው ቀላል ነበር ማለት አይደለም። “ለኑሮ የሚያስፈልጉንን መሠረታዊ ነገሮች ለማግኘት ሁልጊዜ እንጸልይ የነበረ ሲሆን አምላክ በሰጠን ነገር መደሰትን ተማርን” በማለት ተናግሯል። የራውል ሚስት በርታ አክላ እንዲህ ብላለች፦ “አንዳንድ ጊዜ ራውል ሥራ የማግኘቱ ጉዳይ እያሳሰበኝ በጣም እጨነቅ ነበር። ይሁን እንጂ ይሖዋ በየዕለቱ የሚያስፈልገንን በመስጠት ጸሎታችንን እንደመለሰልን መመልከት ችለናል። ምንም እንኳ እንደ ቀድሞው ብዙ ባይኖረንም ኑሯችን ግን በጣም ቀላል ሆኗል።”

ፍሬድ የይሖዋ ምሥክር በመሆኑ መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናቱ ያጋጠመውን ሁኔታ በሚይዝበት መንገድ ላይ ለውጥ አምጥቷል። እንዲህ ብሏል፦ “አንዳንድ ጊዜ በሥራችን፣ ባለን ቦታ ወይም ባንክ ባለን ገንዘብ እንተማመናለን። ይሁን እንጂ መተማመን የሚገባን በይሖዋ አምላክ ብቻ እንደሆነና ከእሱ ጋር ያለን ወዳጅነት እውነተኛ የደኅንነት ስሜት እንደሚያስገኝልን ተማርኩ።” *

[የግርጌ ማስታወሻዎች]

^ አን.13 አንድ ጥናት እንዳመለከተው ሰዎች ገበያ ወጥተው ከሚገዟቸው ዕቃዎች ውስጥ ወደ 60 በመቶ የሚሆኑት አስቀድሞ ያልታሰበባቸው ናቸው።

^ አን.30 የገንዘብ አያያዝን በተመለከተ ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት የነሐሴ 1, 2009 መጠበቂያ ግንብ ከገጽ 10-12 ተመልከት።

[በገጽ 9 ላይ የሚገኝ የተቀነጨበ ሐሳብ]

“ለኑሮ የሚያስፈልጉንን መሠረታዊ ነገሮች ለማግኘት ሁልጊዜ እንጸልይ የነበረ ሲሆን አምላክ በሰጠን ነገር መደሰትን ተማርን”

[በገጽ 8 ላይ የሚገኝ ሣጥን/ሰንጠረዥ]

 ባጀት ማውጣት የሚቻልበት መንገድ

(1) መሠረታዊ የሆኑ ወርሃዊ ወጪዎቻችሁን በጽሑፍ አስፍሩ። በአንድ ወር ውስጥ ለቀለብ፣ ለቤት (ለኪራይ ወይም ለባንክ ዕዳ)፣ ለውኃ፣ ለኤሌክትሪክና ለስልክ፣ ከመኪና ጋር ለተያያዙ ወጪዎችና ለመሳሰሉት የምታወጡትን ያጠቃልላል። በዓመት አንዴ የምትከፍሏቸውን ክፍያዎች በወር ምን ያህል እንደሚሆን ለማወቅ ለ12 አካፍሉት።

(2) ወጪዎቻችሁን እንደሚከተለው ብላችሁ ከፋፍሏቸው። ለምሳሌ ለቀለብ፣ ለቤት፣ ለመኪና፣ ለመጓጓዣና ወዘተ።

(3) ለእያንዳንዱ የወጪ ዓይነት በየወሩ ምን ያህል ማስቀመጥ እንዳለባችሁ እወቁ። በዓመት አንዴ ለሚከፈሉ ክፍያዎች በወር ምን ያህል ማስቀመጥ እንዳለባችሁ “ማስላት” ይኖርባችኋል።

(4) የቤተሰባችሁ አባላት የገቢን ግብር ሳይጨምር በወር የሚያገኘውን አጠቃላይ የተጣራ የገቢ መጠን ጻፉ። ይህን የገቢ መጠን ከወጪያችሁ ጋር አስተያዩት።

(5) ለእያንዳንዱ የወጪ ዓይነት በየወሩ የሚያስፈልገውን ገንዘብ ለይታችሁ አስቀምጡ። ለዚህ ቀላሉ መንገድ ፖስታ አዘጋጅቶ በፖስታው ላይ እያንዳንዱን የወጪ ዓይነት መጻፍ ነው። ከዚያም ወጪዎቹን ለመሸፈን የሚያስፈልገውን የገንዘብ መጠን በየጊዜው በፖስታ ውስጥ አስቀምጡ።

ልትጠነቀቁበት የሚገባ ነገር፦ ክሬዲት ካርድ የምትጠቀሙ ወይም ዱቤ የምትወስዱ ከሆነ ጠንቃቆች ሁኑ! ብዙ ሰዎች ‘አሁን ውሰድ በኋላ ክፈል’ በሚለው ስሜት ስለሚሸነፉ ያወጡት ባጀት ይቃወሳል።

[ሰንጠረዥ]

(መልክ ባለው መንገድ የተቀናበረውን ለማየት ጽሑፉን ተመልከት)

የተጣራ ወርሃዊ ገቢ

የተጣራ ወርሃዊ ደሞዝ ብር․․․․․ ሌላ ብር․․․․․

የቤተሰቡ አባላት

የተጣራ ደሞዝ ብር․․․․․ አጠቃላይ የተጣራ ገቢ

ብር․․․․․

ባጀት የተያዘላቸው ትክክለኛ

ወርሃዊ ወጪዎች ወርሃዊ ወጪዎች

ብር․․․․․ ለቤት ኪራይ ወይም ለባንክ የሚከፈል ብር․․․․․

ብር․․․․․ ኢንሹራንስ/ግብር ብር․․․․․

ብር․․․․․ ለውኃና ለኤሌክትሪክ ብር․․․․․

ብር․․․․․ ለመኪና ብር․․․․․

ብር․․․․․ ለመዝናኛ/ለጉዞ ብር․․․․․

ብር․․․․․ ለስልክ ብር․․․․․

ብር․․․․․ ለቀለብ ብር․․․․․

ብር․․․․․ ሌላ ብር․․․․․

አጠቃላይ በጀት አጠቃላይ ትክክለኛ ወጪ

ብር․․․․․ ብር․․․․․

ገቢና ወጪ ሲነጻጸር

የተጣራ ወርሃዊ ገቢ ብር․․․․․

ሲቀነስ− ከወጪ ቀሪ

ወርሃዊ ወጪዎች ብር․․․․․ ብር․․․․․